Blog,  Video Posts,  እብራውያን,  ዕብራውያን

ውርደቱን ተሸክመን፣ ከሰፈር ውጪ እንውጣ (ዕብ 13.7-10)

 

I.  መግቢያ: ተልዕኮን ለመወጣት ከሰፈር መውጣት

መቼም ራሳችንን እንደ ግለሰብ፣ እንደ ክርስቲያናዊ ኅብረት፣ እንደ ቤተሰብ ልንጠይቅ የሚገቡ ነገሮች አሉ።

  • አላማችን ምንድር ነው? ተልዕኮአችን ምንድር ነው? ተልዕኮአችንስ ማንነታችንን እየቀረጸ ነው?
  • ቁ. 10 ላይ ‘መሠዊያ አለን”ይላል ይኽም እዚህ ቅጥር ግቢ ውስጥ መኖር የማይገባቸው ነገሮች አሉ። ከጥሪያችን ጋር የማይገጥም ጥላቻ፣ እኔ-ተኮርነት፣ ለወገኔ-ይጠቅማልነት እናያለን
    • 13:1-3 የወንድማማች መዋደድ ይኑር።
    • 13:4 መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን
    • 13፡5 አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ
    • 13፡7 አስቡ. ተመልከቱ፣ ምሰሉ
      • በከናፍርታችን ያሉ ቃሎች ምን ይመስላሉ (ቁ. 15)
      • በእጃችን ላይ ስላለው ሥነ ምግባር? (ቁ. 16)
      • የእግሮቻችን አካሔድ ምን ይምሰል? (ቁ. 13)
      • አይኖቻችን ምን ይመልከቱ (ቁ. 14)
  • ይህ መሰዊያችን ባለ አራት ቅጥር ይመስላል፦
    • የክርስቶስ ትምህርት የሚባል የሚጠበቅ በር አለ፣ ጠብቁ
    • የመልካም-ሥራ መስዋዕት የሚባል በር አለ፤ ጠብቁት
    • የአንድነት በር የሚባል አለ፣ በትብብር መንፈስ ጠብቁት
    • የተልዕኮ የሚባል በር አለ፣ ከሰፈር ለመውጣት አትፍሩ።

ቤተ ክርስቲያን የተጸነሰችው፣ የተወለደችው፣ የምትኖረውም ለዚህ ተልዕኮ ነው።

በተልዕኮ የዳነ ሕዝቦች ነን፦

እንደ አዲስ ኪዳን ምስክርነት ከሆነ፣ ቤተክርስቲያን የተጸነሰችውም ይሁን የተወለደችው በተልዕኮ ነው። ኢየሱስ ከአብ ዘንድ በተልዕኮ ነበር የመጣው። ተልዕኮውም ስለ ሃጢአታችን ቤዝዎት ለመሆን ነው።

  • ተልኮ የመጣ ልጅ ነው – “እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው” (3:17
  • ሥራው የተልዕኮው ውጤት ነበር – “አባት ሆይ፤ ጊዜው ደርሶአል….የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር አከበርሁህ (Jn 17:4)
  • ትምህርቱ የተዕኮው ውጤት ነበር – “49እኔ ከራሴ አልተናገርሁም፤ ነገር ግን የላከኝ አብ ምን እንደምናገርና እንዴት እንደምናገር አዘዘኝ። 50የእርሱ ትእዛዝ ወደ ዘላለም ሕይወት እንደሚያደርስ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም የምለው ሁሉ አብ እንድናገረው የነገረኝን ብቻ ነው።” 12:49-50

የምንኖረው ለተልዕኮ ነው። ሚስዮናዊነት ሐልዎታችን ነው።

  • ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው። 22ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” Jn 20:21–22.
  • 17ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው ። 18አንተ ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እኔም ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ። 19እነርሱ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ፣ ራሴን ስለ እነርሱ ቀድሻለሁ”
  • 15ከእንግዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ አገልጋይ ጌታው የሚሠራውን አያውቅምና፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጽሁላችሁ ወዳጆች ብያችኋለሁ”

እኛ የተልዕኮው ውጤቶችም፣ የተልዕኮው ወኪሎችም ነን። ሆኖም ግን የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ማስፈጸሚያ እንጂ ፍጽመታችን አይደለም (ultimate goal)

“ተልዕኮ የቤተ ክርስቲያን ፍጻሜ አይደለም። አምልኮ እንጂ። ተልዕኮ ያለው, አምልኮ ስለሌለ ነው። ተልዕኮ ሳይሆን፣ አምልኮ ፍጻሜያችን ነው፣ ምክኒያቱም ፍጻሜያችን ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ስለሆነ። ይህ የአሁኑ ዘመን አብቅቶ፣ ሊቆጠር የማይቻል እልፍ ኧእላፍ ከነገድ ከቋንቋ የተዋጁ በፊታቸው ተደፍተው፣ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ ሲሰግዱ፣ ተልዕኮ ከዚያ ወዲያ የለም። ተልዕኮ የአምልኮ ማስፈጸመያ ነው። ”  Let the Nations be Glad, Piper, 15.

ወደ ዕብራውያን መጽሐፍ ስንመጣ፤ ከዚህ የተለየ አይደለም

  • ተደራስያኑ ቢያንስ በሁለት ነገሮች ተቸግረዋል
    • ማፈግፈግ ወይስ መጋፈጥ
      • ወደ ኋላ መመለስ
        • (ወደ ዘመነ-ሲና፣ ክርስቶስ ከመምጣጡ በፊት ወደ ነበረው ሁናቴና ዘመን። ይህ ከሆነ በሁለቱም ዳር አትርፈዋል። በአንድ እጅ ሙሴአዊነትን የሚያቀነቅን መንፈሳዊነት፣ በሌላ እጅ ክርስቶሳዊነትን የሚያቀነቅን ነገረ መለኮት)
      • ወይስ ኢየሱስ ይልቃል! ብሎ ክርስቶስ ወደ ሄደበት መሄድ
        • “በአደባባይ ለስድብና ለስደት መጋለጥ…አንዳንዴም መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር አብሮ መደመር” (ዕብ 10፡32-34)
      • ጸሐፊው ‘አትመለሱ!” ይላቸዋል። አትሞክሩት። ሞት አለበት። ኢየሱስ ይልቃል! ኢየሱስ በሕግ የተሾመ ሳይሆን፣ በመሃላ የተሾመ መልከጸዴቃዊ ክህንና የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
        • “እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ” Heb 4:14.
        • ኢየሱስ = ታላቅ ሊቀ ካህናት ሆኖ ተሹሟል + የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ተሹሟል
        • ማረጋገጫ = በአብ ቀኝ መቀመጡ
        • እርሱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ አንዱን መስዋዕት አቅርቦ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ሊያነጻቸው የሚችል፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እጅ ወዳልሰራው መቅደስ ገብቷል።
      • አውዳዊ ተዛምዶ
        • ከራስን ምቾት አንጻር ወይም “ለወገኔ ምን ይጠቅም” በሚል ከንቱ አሳብ ውስጥ ገብተን “ወገናዊ” በመሆን “እኛ ሰፈር “ ውስጥ እንቅር፣ ወይስ “ከዚህ ሰፈር ውጡ ሰፈራችሁ አይደለም” ሲሉን ሰፈር ውስጥ ለመቅረት እናላላ?
        • ወይስ “የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች” መሆናችንን አውቀን፣ የክርስቶስን ውርደት ተሸክመን፣ “ወራዳዎ”ች ቢሉንም ይበሉን ብለን “እነዚያ!” ወደተባሉት፣ ክርስቶስን እንከተል? የቱን እንምረጥ?
      • ይህ ክፍል የእብራውያን መጽሐፍ መደምደሚያና መዝጊያ ክፍል ነው።
        • በአንድ ወቅት ይኖሩ በነበሩ አሁን ግን በተሰበሰቡ (የሞቱ) ታማኝ ባለአደራ በነበሩ መሪዎቻቸው (ቁ. 7) በማሳሰብ ይጀምርና በቁ.17 ላይ ደግሞ አሁን ተደራስያኑን እየመሯቸው ባሉ መሪዎች ይደመድማል። እንደ ክፈፍ።
          • ስለ ቀደሙት መሪዎቻቸው የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን ዐስቡ፤ የኑሮአቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሉአቸው።”
          • ስለ አሁኖች መሪዎቻቸው ደግሞ “ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም”
        • ጸሐፊው ራሱን ከአሁኑ መሪዎች ጋር በመወገን “ለእኔም ጸልዩልኝ” ይላል።
      • በመካከል ያለው ከቁ.10-16 ያለው የዚህ ክፍል ማዕከላዊ መልዕክት ነው። በሦስት ደረጃ ይቀርባል
        • ከቁ.10-12 ላይ የእኛን መሠዊያና የሙሴያውያንን መሠዊያ ያነጻጽራል።
          • ስለ ቀደመው መስዋዕት፣ እንዴት ከሰፈር ውጪ እንደሚቃጠል ከተናገር በኋላ (ቁ. 11)፣ እንዲሁም ኢየሱስ በማለት እንዴት እርሱም ከበር-ውጪ ወጥቶ መከራን እንደተቀበለ ያስረዳል። ይኽም፣ ከሙሴ ሕግ ወደ ክርስቶስ የተደረገውን ሽግግር ያሳየንና
        • በቁ.13-14 ባለው ደግሞ፣ “ስለዚህ እኛም” በማለት ሕይወታችን ከክርስቶስ ጋር ትይዩ እንደሆነች ያሳያል። ይኽም፣ የክርስቶስን ፈለግ ተከትለን ከሰፈር ውጪ መውጣት እንዳለብን ያሳስበናል።
        • ቁ.15-16 ላይ እኛ “መሠዊያ አለን” ሲል፣ ምሥዋዕትም እንዳለ መጦቆሙ ነው።፡የምናቀርበው መሥዋዕት የደም መስዋዕት መሆኑ ቀርቷል። የምናቀርበው የተሻለና እግዚአብሔርን የሚያስደስት መሥዋዕት መሆኑን ያስረዳናል።
      • በቁ.17 ላይ፣ ከቁ. 7 ጋር ትይዩ በሆነ መልኩ፣ ከሠፈር የመውጣቱ ተልዕኮ የሠመረና ስኬታማ እንዲሆን በቤተ ክርስቲያን አንድነት ያስፈልጋል። ይኽም፣ በመሪዎችና በአማኞች መካከል ትብብር ለተል ዕኮ ስምረት አማራጭ የለሽ ነው።

B.   የስብከቱ ጭብጥ

በዚህ ቋሚ ከተማ ስለሌለን የክርስቶስን ትምህርት፤ የሕይወቱን መዓዛ፣ ነቀፌታና ውርደቱን ይዘን፣ መሪዎች እየመሩ፣ ተመሪውም እየተመራ፣ ክርስቶስ ወዳለበት ወደ ሰፈር ውጪ እንውጣ እንጂ፣ «ሰፈርውያን» አንሁን።

 

C.   መሸጋገሪያ

  • ስለዚህ፣ በፊታችን ያለው ተልዕኮ፣ ብዙ የሚሰራ ነገር ያለው ተል ዕኮ ነው፣ ብዙ የሚታጨድ አዝመራ አለ፣ ብዙ የሚታረስ መሬት አለ። ገና አልጨረስንም። በብዙ ነገር የቤት ሥራችን ገና አልተጀመረም። ተቆልሎብናል።
    • እንዴት እንውጣ? ዕብ 13:7-14 ያለው የሚያስተምረን አራት ነገሮች አሉ
  • ስለዚህ የክርስቶስን ተልዕኮ ይዘን ስንወጣ እንዴት እንውጣ?

II.   የክርስቶስን ትምህርትና መዓዛ በአንድነትና በትብብር መንፈስ ይዘን እንውጣ [13:7-10]

“7የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን ዐስቡ፤ የኑሮአቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሉአቸው። 8ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው። 9በልዩ ልዩ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን የሚጸናው በጸጋ እንጂ የምግብ ሥርዐት በመጠበቅ አይደለም፤ ይህንን ሥርዐት የሚጠብቁት እንኳ በዚህ አልተጠቀሙም። 10 በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን።

A.   ማብራሪያ

  • የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን ዐስቡ፤ የኑሮአቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሉአቸው።
    • እነዚህን ቁ. 7 ላይ አስቧቸው ደግሞ ቁ. 17 ላይ ያሉትን ታዘዟቸው በማለቱ፣ ሁለት የተለያዩ ናቸው።
    • ጥሪው (the call to action) | አስቡ…ተመልከቱ…ምሰሉ
      • አስቡ = የእ/ርን ቃል በተመለከተ; ተመልከቱ = ፍሬያቸውን በተመለከተ; ምሰሉ = እምነታ
    • አስቡ\ተመልከቱ = ልብ በሏቸው። ተቀበሏቸው። ሥፍራ ሥጧቸው – ድርጊት ገላጭ ናቸው
    • ምሰሏቸው = ፈለጋቸውን ተከተሉ፣ ኮርጇቸው
      • በዚህ መጽሐፍ ላይ አትምሰሉ እና ምሰሉ የሚላቸው ምሳሌዎች አሉ
        • አትምሰሉ – ከ3:7 – 4:13 በምድረበዳ የረገፈውን ትውልድ አትምሰሉ; 12:16-17 ኤሳውን አትምሰሉ
        • ምሰሉ – 11:1-40 እምነታቸው የተመሰከረላቸውን ነባር ምሥክሮች፤ 12:1-3 ኢየሱስን ሕያው ምሥክር
      • ምሰሏቸው በሦስት ረገድ
    • ትምህርታቸውን በማሰብ…ምሰሏቸው (ትምህርታቸውን ኮርጁ)-
      • እነዚህ “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯቸው መሪዎች” ናቸው – “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን”
        • ይህ ሐረግ በአዲስ ኪዳን ላይ ለሚስዮናዊ የወንጌል አገልግሎትና ለወንጌል ስብከት ጥቅም ላይ ውሏል “ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ” (ሐዋ 4:31)
        • በእብራውያን ውስጥ ግን በልጁ የተነገረውን (ዕብ 1:2) እና ስለእርሱ የሚመሰክረውን ቃል ነው። Heb 4:12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል”
        • ዕብ 2፡1-3 “ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡል...ስለዚህ ከሰማነው ነገር ስተን እንዳንወድቅ፣ ለሰማነው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባናል…
        • ሉቃስ 1:1-4 የምጽፍልህ ታሪክ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ያስተላለፉልን ነው…4ይህንንም የማደርገው የተማርኸው ነገር እውነተኛ መሆኑን እንድታውቅ ነው።

 

  • የኑሮአቸውን ፍሬ በመመልከት…ምሰሏቸው
    • እንዴት? የኑሮአቸውን ፍሬ በመመልከት
      • አዲሱ መደበኛው ትርጉም ሦስት በራሳቸው የሚቆሙ ዓ/ነገር አድርጓቸዋል። (አባ ሮሜ ‘አይታችሁ’; ነባሩ ትርጉም = ‘የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ’
      • መመልከት (ναθεωροντες) = የቃሉ ስሜት ደግሞ ደጋግሞ መመልከት። Role model! ፊታችን ያደረግነው ነው እርሱን/ሷን እንመስላለን። ፊታችን ምን አለ?
      • የአካሔዳቸውን ‘ትሩፋቶችን’ በማጤን። Outcome of their conduct (sum total)\τὴν ἔκβασιν τῆς ἀναστροφῆς
        • “ያካሔዳቸውንም ፍጻሜ አይታችሁ” አባ ሮሜ ትርጉም
      • ፍሬ አይኮረጅም። ፍሬ የሚፈራ ነገር እንጂ።
      • ስለዚህ፦ ፍሬያማ ሆነው አልፈው፣ ዛሬ በፊታቸው ቋሚ ምስክሮች ሆነዋል። ምሰሏቸው።
    • ምናቸውን እንመሰል? በእምነታቸው ምሰሉአቸው
      1. ምክንያቱም የተኖረ-እምነት ነው።
        1. በእምነታቸው ምሰሏቸው የሚለው ምክኒያቱም የሕይወታቸው መለወጥ ምንጭ እምነታቸው በመሆኑ ነው።
        2. ስለዚህ የእምነት ጉዳይ ለዚህ መጽሐፍ እንግዳ አይደለም። የብሉይ ምሳሌዎች (11:1-40); የምድረበዳው ትውልድ ባለማመን ጠንቅ ጠፍቷል (3:12, 19; 4:2-3)
      2. ዋናው ነጥብ፦ ምንም እንኳ ዛሬ የሞቱ ቢሆንም የተለውጠ ሕይወታቸውንና የተኖረ-እምነታቸው፣ እንዲሁም አስተምረው ያለፉትን እምነት ምሰሉ። ለምን? ቁ. 8 ያብራራዋል።
    • [8] ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።
      1. በአንድ ዘመን አገልግለው ያለፉ መሪዎችን ለምን እንመሰል? ሕይወታቸውን ለምን እንከተል? ትምህርታቸውን ሙጭጭ እንበል? ምክኒያቱም ኢየሱስ አልተቀየረም። እነርሱ ሞቱ፣ ነገር ግን በሕይወታችው ኖረው የገለጹትና አስተምረውት ያለፉት ኢየሱስ አልተለወጠም። በዙፋኑ ላይ ነው።
        1. ትናንትና እና ዛሬ የሚለው – እስከ አሁን የሚል ትርጓሜ አለው (ዛሬ ተብሎ እስካለ ድረስ 3:7)
        2. ዘላለማዊ – ክህነቱ ዘላለማዊ ነው (5:6; 6:20; 7:17, 21, 28); ያስገኘው ድነት ዘላለማዊ ነው (5:9; 9:12; 7:24-25)
      2. የተደራስያኑ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል፤ በአንድ ወቅት በስደት አሁን ለጥቂት ጊዜ በሰላም ላይ አሉ። ሁኔታ ቢለዋወጥ፣ ኢየሱስ ግን አይለወጥም። ያን ጊዜ መሪዎች እያሉ እውን የነበረው ሀልዎተ-ክርስቶስ፣ አሁንም እውን ነው። ዛሬም ታማኝነት ለኢየሱስ።፡ዛሬም ታማኝነት ለትምህርቱ።
    • [9] በልዩ ልዩ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን የሚጸናው በጸጋ እንጂ የምግብ ሥርዐት በመጠበቅ አይደለም፤ ይህንን ሥርዐት የሚጠብቁት እንኳ በዚህ አልተጠቀሙም።
      1. እናስ? አትወሰዱ [[አትንገዋለሉ\ አትወላውሉ]]
        1. በብዙ ቁጥር ትምህርቶች ሲል ከአንዱ የክርስቶስትምህርት (በነጠላ) ጋር እያነጻጸረ ነው (6:1 ‘አስተምህሮተ-ክርስቶስ’)።
        2. እንግዳ በማለቱ ደግሞ በአይን ምስክሮቹ ያልተሰበከ ት/ት፣ ጸጉረ ልውጥ ት/ት መሆኑን እያሳየን ነው።
  • ይህ ትምህርት የጸና ቃል እንጂ በየዘመናቱ የሚፈለሰፍ አይደለም።
    1. Παραφέρεσθε [አትንገዋለሉ] ኤፌ 4:14-16 “ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን [περιφέρω] ሕፃናት አንሆንም። ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፤
  1. ስለዚህ፦ ከኢየሱስ ወደ ሐዋሪያቱ እና ወደ ታማኝ የቃሉ አገልጋዮቹ የተላለፈው መልዕክት እንደ ችንካር ይትከላችሁ። የቃሉ አገልጋዮች በታማኝነት በሰበኩት ትምህርት ጽኑ፣ ኢየሱስ ትናንትና ዛሬም ለዘላለም ያው ነውና።
  1. እናስ? ልባችን በጸጋ ይጽና
    1. እንግዳ ትምህርትን ከማሳደድ ይልቅ በጸጋ ጽኑ! ይልና ትኩረቱ ልብ ላይ ነው። በቀደመው ኪዳን ሥር የነበሩ፣ ልባቸው ሁል ጊዜም ይስት ነበር (3:10)። በአዲስ ኪዳንም ተሓድሶ ያገኘው ልባችን ነው (10:16)
      1. ትኩረቱ ምግብ ላይ ሲሆን፣ የብሉይን የአመጋገብ ሥርዓት ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ከእንዲህ ምግብ ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም።
      2. 8:8 “ነገር ግን ምግብ ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላ የሚጐድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር አይኖርም።”
    2. ዋናው ነጥብ፦ የእግዚአብሔር ጸጋ ዛሬ የሚማከለው በክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ነው። በመስቀል ሞቱ፣ ባፈሰሰው ደሙ፣ በቂ ከበቂም በላይ የሆነ ጸጋ ተሰጥቶናል።በመብል፣ መገረዝ፣ የቀናት አከባበር ተሽሯል። “ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ ስለማይችል ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መጥቶአል” (7:19)
  • ስለዚህ፣ የልባችን አንቴና ይረፍ! 6:1 ላይ እንደሚያስረዳን፣ በክርስቶስ ትምህርት ጀምረን ሥር እየሰደድን ወደ ብሰለት እንሔዳለን እንጂ፣ ከክርስቶስ ትምህርት እየተፈነጠርን ወደ እንግዳ ትምህርትና ልምምድ አንገባም። የክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የጎዷት፣ «እናውቅላታለን» ከሚሏት እኩል፣ «ክፍት እንሁንላት» በሚሏትም ጭምር ነው። እንግዳ ትምህርትና እንግዳ ልምምድ የምናግበሰብስባት አይደለችም። ልባችን በመለኮታዊ ጸጋው ይረፍ። እነርሱን ታማኝ ያደረገና በሕይወታቸው ፍሬ እንዲያፈሩ የረዳ ጸጋ ዛሬም አለ። ኢየሱስ ትናንትና ዛሬም ለዘላለም ያው ነውና። “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” ይልቁንስ እርስ በርሳችን “15ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት” እንተያየ።(12:15)
  1. ቁ. 10 መሠዊያ አለን። ያለ ክርስቶስ ከዚህ ማዕድ የሚቋደስ ማንም የለም – በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን።
    1. መሠዊያ አለን ሲል ከብሉይ ኪዳን ሥር ዓቶች ጋር ለማነጻጸር እንጂ፣ እኛ መሠዊያ ሥፍራ አለን እያለ አይደለም።
    2. ንፅፅሩ “በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ” ጋር ነው
  • ከመቼውም ጊዜ በላይ፣ ወደ መሠዊያችንን የምናቀርባቸውን ሰዎች አጥብቀን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል። አቅልለነዋል!

B.  ምሳሌ

የሩዋንዳ ምሳሌ – James Engle in his published article on Christianity today in August 11, 2000, titled: “Beyond the Numbers Game” – “ከቁጥር ጨዋታ ስናልፍ”

ከዓለም ሕዝቡ ሁሉ የተወጣጣ የተወካዮች ጉባዔ በተሰበሰበት በዚያ ታላቅ አዳራሽ ላይ፣ ቢድላም የተሰኘው የተወካዮቹ አፈ-ጉባዔ ድምጹን ከፍ አድርጎ “የአዝመራችንን ፍጻሜ በመጨረሻ ማየት ቻልን!” አለ…ታዳሚውም ሆታና ጭብጨባውን አቀለጠው…ይህ ሲሆን ሳለ፣ አንድ አጠር ያለች ሴት ወደ ድምጽ ማጉሊያው ቀረብ አለች። የአፍሪካ ተዋካይ ነበረች። ጉባኤው ድንገት ረጭ አለ። የአፍሪካዊቱም ፊት በሐዘን ይከብድ ጀመር። “እኔ የመጣሁባት አገር፣ በብዙዎቻችሁ ሚስዮናውያን ዘንድ ‘ታላቅ ስኬት’ ከተባለች አገር ነው” እያለች ጀመረች። እንዴት ከ100 ዓመታት በፊት ወንጌል የትውልድ አገሯ እንደገባ፤ ዛሬ ወደ 85% በላይ የሚጠጉ ዜጎች ‘ክርስቲያን ነን’ የሚሉባት ምድር ሆናለች። ከ25% በላይ የሆነው እድገት የመነጨው ከወንጌላውያን እና ከጴንጤቆስጣውያን አብያት ክርስቲያናት እንቅስቃሴ እንደሆነ ዘርዝራ መናገር ቀጠለች። በተለይ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት እንቅስቃሴ በአገሪቱ ላይ እንደተስፋፋ ስትገልጽ፣ በጉባዔው መካከል አድናቆት ይንሸራሸር ጀመር። ግን ጉባኤውን አንድ ጥያቄ ጠየቀች “በነገራችን ላይ እኔ ከየትኛው አገር እንደሆንሁ የሚያውቅ አለ?” አያሌ መላምቶች ተሰነዘሩ። አንዱም ልክ አልነበረም። በመጨረሻም ይህች አፍሪካዊት “እኔ ከሩዋንዳ ነኝ! አዎ ያቺ ሩዋንዳ! ያች በ1994 ዓ.ም. ላይ 600ሺህ ቱትሲዎች እና 400ሺህ ሑቱዎች በቆንጨራ የጨፈጨፈችው ሩዋንዳ!” “አዎን፣ ለወንጌል መስፋፋት ካላችሁ ቅናት የተነሳ፣ ምድራችን ድረስ መጥታችሁ ክርስቶስን አመጣችሁልን። ‹ግን እንዴት መኖር እናዳለብን› አላስተማራችሁንም። አጠመቃችሁን፣ ግን እንዴት ክርስቶስን እንደምንኖር አላስተማራችሁንም። ‹ተልዕኮ ተፈጸመ› የምትሉኝ ከሆነ፣ ለዚህም በዚህ አዳራሽ መሰብሰባችን ምሥክር ነው፤ እስኪ ሩዋንዳን አስረዱኝ። እንዲሁም ‘የክርስቲያን ምድር’ የተሰኙትን ግን ቁሳዊነት የነገሱባቸውን፣ ያልታደሉ ድሆች የሚጮኹባቸውን ‘የክርስቲያን ምድሮች’፣ የሥነ-ምግባር መላሸቅ የተንሰራፉባቸው ‘የክርስቲያን ምድሮች’። እስኪ አስረዱኝ። መቼም ‘እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው’ ብሎ ጌታችን ሲናገር፣ እንደ ሩዋንዳ ያሉትን አፍሩ ማለቱ እንዳልሆነ በርግጠኝነት መናገር እንችላለን። ፍቀዱልኝና ልድፈር «አጨድን የምንለው መኸራችን፣ በውስጡ ትልቅ ችግር አለበት» «To put it bluntly, something has gone wrong with the harvest»

C.           ተዛምዶ

እዚህ ጋር ቆም ብለን ራሳችንን መጠየቅ ያለን ነገር አለ።

ይህንን ጽሑፍ ምንም እንኳ James Engle የዛሬ 20 ዓመታት በፊት ቢጽፍም፣ ከመቼም ጊዜ በላይ በኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ዘንድ ይህ ሐቅ ሆኗል።

ወደ ውጪ ስንወጣ ይዘን ስለምነወጣው ነገር ልንጠነወው ያስፈልጋል።

  • የክርስቶስን ትምህርት ይዘናል? ሕይወታችንስ የትምህርቱን መዓዛ ይሸታል? ለዚህ መቼስ የዴንቨር ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ምሳሌ ናት።
  • ፍሬያችን ምን ይመስላል?
  • ልምምዳችን ምን ይመስላል? መበረታታት ስንፈልግ የት እንሔዳለን? ወገኖቼ፣ ወደ መስቀሉ ሥር? ወይስ ወዴት? መነቃቃት ስትፈልጉ መነቃቃትን የት ትፈልጓታልችሁ?
    • አንዳንድ ጊዜ ለመንፈሳዊ ነገር ያለን ናፍቆት፣ ለእግዚአብሔር ያለን ጥማት፣ በክርስቶስ ትምህርት ላይ ካልተመሰረተ፣ ወይም ጥማችንን የሚቆርጠው የመስቀሉን ቃል ስናዳምጥ ካልሆን፣ ቆም እንበል። አደጋ ላይ ነን።
    • ለዕብራውያን ሰዎች፣ የጢስ ነገር፣ ደመና፣ እሳት፣ የሚንቀለቀል ሲና፣ አቤት የእግዚአብሔር ክብር እንዳይሉ “ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤ ወደ መለከት ድምፅ፣ ወይም ቃልን ወደ ሚያሰማ ድምፅ አልመጣችሁም” … እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል፤ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል። የሚናገረውን እርሱን እምቢ እንዳትሉት ተጠንቀቁ። እነዚያ ከምድር ሆኖ ሲያስጠነ ቅቃቸው የነበረውን እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፣ እኛ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅ ቀን ከእርሱ ብንርቅ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?”
    • ለተደራስያኑ፣ ወደ ሲና መመለስ (እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ሰጠው መንገድ) መዘዙ ታላቅ ከሆነ፣ እኛ ከክርስቶስ ትምህርት ብንሔድ ምን ያህል ታላቅ ይሁን?
  • በጸጋ እንጽና።
    • በጸጋ ጀምረን ሳናውቅ ወደ ኋላ እንዳንመለስ። አሊያ መውጣታችን ለሌሎች ሕይወት አይሆንም።
    • ለእግዚአብሔር ቃል ልብ እንስጥ፣ ለሕይወታችንና ለአረማመዳችን እንጠንቀቅ።
    • ከክርስቶስ ሰምተው ያሰሙንን ሰዎች ትምህርታቸውን፣ የኖሯቸውን ፍሬ፣ እምነታቸውን እንምሰል። ምክንያቱም ያ የሰበኩት ኢየሱስ ትናንትም፣ ዛሬም እስከዘላለም ያው ነው።
  • እንዴት እንውጣ? የክርስቶስን ትምህርትና መዓዛ ይዘን እንውጣ [13:7-9]

 

 

 

2 Comments

  • Gutema

    ከልብ አመሰግናለሁ በቀረው ጥናቱን ከእናንተ ጋር መቀጠል ፈልካለወ። ከ ኮንሶ

  • Gutema kusse

    በጣም አርፈ ስለእናንተ ጌታን አመሰክናለዉ እጅግ አርገ አመሰግናለው

Leave a Reply to Gutema Cancel reply

Your email address will not be published.