HEBREWS,  ዕብራውያን,  ዕብራውያን

Jesus Is Better as the Eternal Son of God-The Son as the Full Revelation of the Father’s Identity (Part 5)

ልጁ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው

[su_note note_color=”#efeeee”]

[/su_note]

የአባቱን ክብር ያንጸባርቃል። ክብር ስንል የከበረ ነው። ሆኖም ግን በዚህ ሥፍራ ክብሩን እንዲበራና እንዲገለጥ የሚያደርገው ልጁ ነው። ከዚህ የተነሳ ልጁ የእ/ር አስተርዕዮ/ መገለጥ ነው።

ልጁ የእግዚአብሔር ባሕርይ ምሳሌ ነው

ለልጁ የእግዚአብሔር ሕልውናና ማንነት ገንዘቡ ነው። ከዚህ የተነሳ ልጁ ከአባቱ ጋር በክብርና በሐይል እኩል ነው።

የልጁ የማማከል አገግሎት

እግዚአብሔርን ያማክላል

ልጁ የመለኮት ባህርይ ገንዘቡ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ማንነት ለፍጥረት በማንጸባረቅ ያማክላል

አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤  ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ (1 Timothy 2:5–6)

እንግዲህ ሕግ ምንድር ነው? ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ።  መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። (Galatians 3:19–20)

ነብያት በብሉይ ይህንን ሚና በከፊል ተጫውተው ስለነበር መገለጡ “በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነብያቱ ተናግሮ” በመባል ተገልጧል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን። የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል። አምላክህን እግዚአብሔርን በኮሬብ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን። እንዳልሞት የአምላኬን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አልስማ፥ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አልይ ብለህ እንደ ለመንኸው ሁሉ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ። Deuteronomy 18:13–16

የዚህ የማማከል አገልግሎት የሚካሔደው በመግለጥ ነው (ቃል – the activity of speaking)

ሰዎችን ያማክላል

ልጁ በነገር ሁሉ ፍጹም ሰው ሆኖ ስለተገለጠ ሰዎችን በእግዚአብሔር ፊት ያማክላል

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። Hebrews 2:14–17

በብሉይ ካህናት ደግሞ ሰዎችን ወክለው በሰዎች ነገር ላይ ተሹመው ሰውን ያማክላሉ። ይህ ማማከል የህዝቡን ሐጥያት ለማስተሰረይ መስዋዕትን በማቅረብ ነው።

የልጁ ከአብ ጋር ያለው አንድነት፤ አኩልነትና የአካላት ልዩነት

  1. በአብና በወልድ መካከል ያለውን አንድነት  (unity) ግንዛቤ ውስጥ ያለማስገባት አደጋ (ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው) ይህ ሚዛን ካልተጠበቀ ወደ ሦስት አማልክት ያመራል። አብ የራሱ ማንነት ወልድም የራሱ ማንነት መንፈስ ቅዱስም የራሱ ማንነት አለው ወደ ሚል ስህተት ውስጥ ይዳርጋል። Ditheism/ Tritheism
  2. በአብና በወልድ መካከል ያለውን እኩልነት  (Equality) ግንዛቤ ውስጥ ያለማስገባት አደጋ (ልጁ የባሕርይው ትክክለኛ ምሳሌ ነው)ይህ ሚዛን ካልተጠበቀ ወልድ ከአብ ያነሰ ሁለተኛ አምላክ አሊያም የተፈጠረ ፍጡር ነው ወደ ሚል ስህተት ውስጥ ይዳርጋል። Subordinationism
  3. በአብና በወልድ መካከል ያለውን የአካላት ልዩነት  (personal distinction) ግንዛቤ ውስጥ ያለማስገባት አደጋ:- ይህ ሚዛን ካልተጠበቀ ወልድ ያው አብ ነው በማለት አብ-ወልድ-መንፈስ ቅዱስ የሚሉት ስሞች የአንዱ አካል መግለጦች እንጂ የተለዩ አካላት መሆናቸውን ወደ መካድ አደጋ ውስጥ ይዳርጋል። Modalism/ Manifestation.

hebrews_P4_Board2

Leave a Reply

Your email address will not be published.