-
የዐደራ ኑዛዜ ክፍል አንድ፡ በወንጌል ዙሪያ የተደራጀ ሕይወትና ማንነት
2 ጢሞቴዎስ ሕይወትን የሚቃኝና ሕይወታችንን በቅደም ተከተል የሚያደራጅ መልዕክት ነው። መጽሐፉ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጥ መልዕክት ነው። ለግራጫ ሥፍራ የለውም። “የሚቃኝ” ስንል ወደ ዋነኛ ጥሪያችን እንድንመለስ፣ ትኩረታችንን እንድናስተካክል፣ ዋነኛውን ዋነኛ እንድናደርግ፣ የከበረውን ከተዋረደው እንድንለይ የሚያደርገን መልዕክት ነው ማለታችን ነው። ዴማስ ወደ ተሰሎንቄ ምን ሊሰራ እንደሄደ አልተነገረንም። በአንድ ወቅት ግን እንደ ጢሞቴዎስ አብሮ የወንጌል ሰራተኛ ነበር (ቆላ 4፡14; ፊል…
-
የምጋቤ መልእክታት አጠቃላይ ጭብጦች