-
የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ
ማቴዎስ የፍጻሜ መጽሐፍ ነው። ማቴዎስ ኢየሱስን የእሥራኤልን ጥሪ፣ ተሥፋና ተልዕኮ ተላበሶ እንደ ተወለደ ያቀርብልናል። ስለዚህ ኢየሱስ እውነተኛ እሥራኤል ነው። የእሥራኤልን መሢሃዊ ዘር ወርሷል፣ የተለያዩ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችንና ጥብብቆሽን ወደ ፍጻሜ አድርሷል። ይኽም፣ ማቴዎስ “እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ” የሚለውን ቀመር 11 ጊዜ በመደጋገም የወንጌሉን ትኩረት ያሳየናል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ ነው (2:2)፣ የተሰቀለውም የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ ነው (27፡54)። ሲወለድ፣ ሲጠመቅና በክብር…
-
ኢየሱስና የቅዱሳት መጻሕፍት ትራኬ
This is part of a half day long teaching series conducted with my students, based on the redemptive historical narrative of the old testament, paying attention to the development of the royal seed promises of God, culminating on King Jesus as the exalted Messiah-Lord, resulting on worldwide blessing and judgement. በሚከተሉት ትምህርቶች መሲሃዊ ተስፋ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ-መለኮት አንጻር ቀርቧል።
-
የብሉይ ነቢያት ጥሪ፣ መልክዕክት እና መጻሕፍት
ይህ ትምህርት ከጥቂት ወራት በፊት “የነቢያት ጥሪ፤ መልዕክት እና መጻሕፍት” በሚል ርዕስ ስለ ብሉይ ትንቢት መጻሕፍት ወደ 4.5 ሰዓት የፈጀ ትምህርት ለዴንቨር የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት LIVE ያስተማርሁት ነበር። አስቀድሜ ይህንን ትምህርት እንዳስተምር የጋበዘኝን ፓስተር ኤርሚያስ አማኑኤልን ከልብ እያመሰገንሁ ሌሎችም ትምህርቱን ማዳመጥ እንዲችሉ በማሰብ እንደገና ተቀድቶ፤ አሁን ከጥናት ጹሑፍ ጋር በአንድ ላይ ተቀናብሯል። ❝እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ…
-
የሕዝቅኤል ትንቢትና ቅዱሳት መጻሕፍት
በእያንዳንዱ ትውልድ መቼም መጪና ሂያጅ፤ እንዲሁም ወቅታዊና ጊዜያዊ፤ የሆኑ አያሌ ጉዳዮች አሉ። በአንድ ወቅት መሠረት አድርገን የያዝነው በሌላ ደግሞ "አይ እርሱማ አሁን አይሰራም" እንባላለን። በዚህ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ጥናት ክፍላችን ላይ ያተኮርነው - "ስለ ሕዝቅኤል መጽሐፍ፤ ከቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ጋር፤ ልናውቅ በሚገባን እና ዘመን መጠቅ በሆኑ በአራት የቅዱሳት መጻህፍት ባህርያት ላይ ነው" እነዚህ በተለይ በዘመናችን ቤተክርስቲያን ትኩረት ልትሰጣቸው የሚገቡ መሠረቶች ናቸው።…
-
የሕዝቅኤል መጽሐፍ ጥናት: የእግዚአብሔርን ክብር ማወቅ
ዕለቱ July 31, 593 ቅ.ዓ. ነው። ምናልባትም ሕዝቅኤል በእግዚአብሔር ፊት ልቡን ለማፍሰስ ወደ ኮቦር ወንዝ ዳር ሔዶ ሊሆን ይችላል። ይህም ይሆን ይህ የምናውቀው ነገር ቢኖር ሕዝቅኤል ካህን ወይም የካህን ልጅ እንደነበር እና ይህ ቀን ደግሞ የካህኑ 30ኛ የልደት ዓመቱ እንደሆን ነው። የካህኑ የቡዝ ልጅ እንደመሆኑ እድሜ ልኩን ለካህንነት ሲገዘጋጅ እንደ ኖረ መገመት አዳጋች አይደለም። ሆኖም ግን ከዓምስት ዓመታት በፊት በ597…