-
የዐደራ ኑዛዜ ክፍል አንድ፡ በወንጌል ዙሪያ የተደራጀ ሕይወትና ማንነት
2 ጢሞቴዎስ ሕይወትን የሚቃኝና ሕይወታችንን በቅደም ተከተል የሚያደራጅ መልዕክት ነው። መጽሐፉ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጥ መልዕክት ነው። ለግራጫ ሥፍራ የለውም። “የሚቃኝ” ስንል ወደ ዋነኛ ጥሪያችን እንድንመለስ፣ ትኩረታችንን እንድናስተካክል፣ ዋነኛውን ዋነኛ እንድናደርግ፣ የከበረውን ከተዋረደው እንድንለይ የሚያደርገን መልዕክት ነው ማለታችን ነው። ዴማስ ወደ ተሰሎንቄ ምን ሊሰራ እንደሄደ አልተነገረንም። በአንድ ወቅት ግን እንደ ጢሞቴዎስ አብሮ የወንጌል ሰራተኛ ነበር (ቆላ 4፡14; ፊል…
-
ባሪያዬ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል
“እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።” (ኢሳያስ 52:13) አብዛኛውን ጊዜ ስለ ጌታ ባሪያ ሥቃይና መከራ ስናስብ የምንጠቅሰው ኢሳ 53:1-12 ነው። ሆኖም ግን ኢሳ 53 መጀመር የነበረበት በ53:1 ላይ ሳይሆን 52:13 ላይ ነበር። ይህን ማስተዋል ምን ፋይዳ አለው? ፋይዳው፣ በብሉይ ኪዳን ላይ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤና ዕርገት በግልጽ ፍርጥ አድርገው ከሚናገሩ ጥቂት ክፍሎች መካከል (ከመዝ 110:1 ቀጥሎ)…
-
መስቀልና አስተርዕዮተ-እግዚአብሔር
▶️ በስቅለቱ ዋዜማ ስለ መገለጥ በጥቂቱ (Few words on Theological Methodology) ከሁለት ዓመት በፊት፣ በዚሁ በሕማማቱ ሰሞን፣ መስቀልና ዙፋን በሚል ርዕስ ተከታታይ የሆነ ጽሑፎች አቅርቤ ነበር። መስቀሉ ከመንግሥቱ ጋር ያለውን መስተጋብር፣ ድካም ከኃይል ጋር ወዘተ…ለመዳሰስ ተሞክሯል። በደሙ መንግሥቱ ተመርቃለች። ባለፈው ዓመት እንዲሁ፣ “መስቀልና ኪዳን” በሚል በተከታታይ፣ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን እንደመረቀ፣ መስቀሉን ከኪዳን አንጻር ተመልክተናል። በደሙ ኪዳን ተመረቀ። በዚህ…
-
ቁጣው ተወግዶልሻልና ተነሺ! – ክፍል አንድ
ይህ ልጠፋዬ፣ በክፍል ሁለት ላይ ለምለጥፈው፣ በኢሳ 51:17-23 ላይ ላተኮረው ሐቲት፣ መግቢያና መንደርደሪያ እንዲሆን ነው። የምንባቡን ይዘት በጥልቀት ለመረዳት እንዲያስችል፣ ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ‹አጠቃላይ ምንባባዊና ጽሑፋዊ አውድ› በመስጠት ላይ ነው። ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም። እነዚህ ሁለት…
-
የተሰቀለ-ክርስቶስ፡ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ በመልዕክታችን ይኑር
የአንደኛ ቆሮንቶስ 1:10 – 2:5 ሐቲት ኢየሱስን እንደ “ክርስቶስ” መቀበል እና እንደ “ተሰቀለ-ክርስቶስ” መቀበል ይለያያሉ። እኛ የምንሰብከው “የክርስቶስ መስቀል” ከሌሎች መስቀሎች እንዲለይ ያደረገው፤ “መሰቀል” የሚባለው እውነታ አይደለም (በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ወጣቶች ተሰቅለው ነበር – በተለይ በ4 ዓ.ዓ. አካባቢ ላይ)፤ ክርስቶስም የሚለው ቃል አይደለም (ብዙ መሲህ-ነኝ ባዮች ከኢየሱስ በፊት እንደ ስምዖን ወልደ-ጊዮራ ያሉ፣ በኋላም እንደ ስምዖን ወልደ-ኮኸባ ተነስተው ነበር) ይልቁንም…
-
ተወለደ!
‹ለምን ተወለደ?› የሚለው ጥያቄ የሕይወት ጥያቄ ነው። ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን ላይ «ተወለደ» የሚለው ቃል ወልድ ፍጹም ሰው ስለ መሆኑ (ስለ ነገረ-ትሥጉት) ከሚነግሩን አገላለጾች አንዱና ዋነኛው ይሁን እንጂ “ብቸኛ” ግን አይደለም። በአዲስ ኪዳን የትሥጉት ነገረ-መለኮት በብዙ ቃላት ያሸበረቀ ነው። «ተወለደ» በሚለው እሳቤ ላይ በተጨማሪ፣ በአዲስ ኪዳን ላይ እኩል አጽንዖት ተሰጥቷቸው የምናገኛቸው ተጨማሪ ነገረ መለኮታዊና ሙያዊ የሆኑ ቃላት አሉ። በእነዚህ ቃላት…
-
ልደቱና የእግዚአብሔር ተስፋ ቃሎች (ኪዳንና ትሥጉት)
ሐዋሪያው ጳውሎስ “እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና” ይለናል (2 ቆሮ. 1:20)። ያለ ኢየሱስ የተስፋ-ፍጻሜ የለም። ማንም ኢየሱስን ዘሎ በቀጥታ የእግዚአብሔርን ተስፋ የሚወርስ ፈጽሞ ሊኖር አይችልም። ያለ ኢየሱስ የሚጠብቀን “ፍርድና ርግማን” ብቻ ነው። በብሉይ የተሰጡትን ተስፋዎች ሁሉ አንድ አማኝ የሚቀበለው “በክርስቶስ” ውስጥ ነው። ይህንን ለማስረዳት፣ በምናባችን “ማጥለያ” እናስብ። ከላይ የሚጨመረው ዘይት ወደ ጠርሙሱ ጠሎ የሚገባው በማጥለያው ጠባብ…
-
በልጅ አንደበት ተናገረን፡ ወንጌልና አስተርዕዮ በእብራውያን መልዕክት (ክፍል-2)
«ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ…በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» (ዕብ 1፡1:1-2) ባለፈው ክፍል፣ እግዚአብሔርን መግለጥ የሚችለው «ራሱ እግዚአብሔር ብቻ» እንደሆን ተመልክተናል። ስለዚህም ያለ አስተርዮ እግዚአብሔርን ማወቅ አንችልም። ስለ ነገረ-አስተርዕዮም (እግዚአብሔር ራሱን እንዴት እንደገለጠ) በቂ ግንዛቤ ካልያዝን ስለ እግዚአብሔር ያለን ግንዛቤ ሊዛባ ይችላል። ሁለቱ የተያያዙ ናቸው። ለምሳሌ በማርቲን ሉተር አስተሳሰብ ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው ነገር፦…
-
ነገረ-ክርስቶስ በዕብራውያን መልዕክት: መቅድም
(The Christology of Hebrews: An Introduction) የእብራውያን መጽሐፍ የሹመት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉን ሙሉ ነገረ–መለኮታዊ ክብደት የሚሸከመው «በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ» የሚለው እውነታ ነው (ዕብ 1:3; 1:13; 8:1; 10:12-13; 12:2)። ኢየሱስ ከሁሉ እንደሚልቅ ሰባኪያችን ሲሞግት (ጸሐፊውን የምጠራው ሰባኪው በማለት ነው) የሚያቀርባቸው መሠረታዊ ማስረጃዎች በሙሉ በዚህ ልዕልና እና እውነታ ላይ የተመረኮዙ እንዲሁም የተቃኙ ናቸው። እውነታው «ተቀመጠ» (ኧካቲሰን | ἐκάθισεν)” (1:3) የሚለው ሲሆን፤…
-
ስለ አፈታት ጥቂት፡ ከምንባቡ ይዘት ጋር በቅርበት መተዋወቅ
ለአንዳንዶች ይጠቅም ስለሚችል፤ በአንድ ምንባብ ላይ ያተኮረ ትምህርት/ስብከት ሳዘጋጅ ወይም ጽሑፋዊ ሐቲት ስጽፍ፣ ጽሑፋዊ ዓውዱን ለማግኘት የምከተለው ቅደም ተከተል ከሞላጎደል በጥቂቱ እነሆኝ። መጠነኛ የቋንቋ ስልጠና ለወሰዱ ደግሞ አንዳንድ ይጠቅማሉ ብዬ ያሰብኳቸውን መርጃ መጻሕፍቶችንም እጠቁማለሁ ።ከዚህ ቀጥሎ የማሰፍረው በተከታታይ አለፍ አለፍ እያልኩ ስለ ምንባብ አተታተት የማቀርበው ይሆናል። የሚከተለው የመጀመሪያው መርህ ነው። #አንደኛ፡ ከምንባቡ ይዘት ጋር በቅርበት መተዋወቅ ወፍ በረር ትውውቅ (Big…
-
የይሁዳ መልክት – መንደርደሪያ ነጥቦች
[su_note note_color=”#f4f4f3″]► QUESTION: ሳሚየ እቺ እስቲ ኣስረዳኝ- “ከረጅም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኵሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው” ይሁዳ 4 “ምን ማለት ነዉ ከረጅም ጊዜ በፊት ለዙህ ፍርድ የተጻፉ ሲል? ጸጋ ብርኩሰት መለወጥስ? የጌታ የሱስ ጌትነት መካድ እንዴት ነዉ?” (Azeb Berhane)[/su_note]…
-
I AM WHO I AM: Appropriate and Inappropriate Languages about God and Christ
Earlier generations of Christians used to put a lot of effort to discern and talk about the nature of what it is that they believe. That is to say, for them, knowing “what it is” that they believe precedes from what it is they are to “practice and experience.” Worship is Learning the Language of God’s self-Revelation. Worship is only…
-
Confessing Jesus as the Son of God: In Christian and Muslim Context
This is my summary and brief response to a workshop I attended in 2013, taught by Dr. Donald A. Carson on the subject of the Sonship of Christ in Christian and Muslim context. Dr. Carson mentions three objectives. (1) It is important to try to find how one moves from exegesis to doctrinal confessions. Some systematic theologies assume the bible…
-
For the Son of Man came to seek and to save the lost
Amazing grace, how sweet the sound, that saved a wretch like me. I once was lost, but now am found, Was blind but now I see. You probably have seen the movie Amazing Grace. There we see John Newton confessing “I am a great sinner, and Christ is a great savior” This was a man who knew God’s forgiveness. When…
-
GOD IS OUR PROBLEM AND GOD IS OUR SALVATION
Humanities’ big problem in the first instance is not Economic, it is not Social, it is not Political, and it definitely is neither the Republican party nor the Democrats. Even though, all of these areas are real issues that need resolutions. We need to work hard to fight poverty, social injustices and political turmoils. No doubt. However, these are secondary…