የብሉይ ኪዳን ሐቲት
Old Testament Exegesis
-
ባሪያዬ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል
“እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።” (ኢሳያስ 52:13) አብዛኛውን ጊዜ ስለ ጌታ ባሪያ ሥቃይና መከራ ስናስብ የምንጠቅሰው ኢሳ 53:1-12 ነው። ሆኖም ግን ኢሳ 53 መጀመር የነበረበት በ53:1 ላይ ሳይሆን 52:13 ላይ ነበር። ይህን ማስተዋል ምን ፋይዳ አለው? ፋይዳው፣ በብሉይ ኪዳን ላይ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤና ዕርገት በግልጽ ፍርጥ አድርገው ከሚናገሩ ጥቂት ክፍሎች መካከል (ከመዝ 110:1 ቀጥሎ)…
-
ቁጣው ተወግዶልሻልና ተነሺ! – ክፍል አንድ
ይህ ልጠፋዬ፣ በክፍል ሁለት ላይ ለምለጥፈው፣ በኢሳ 51:17-23 ላይ ላተኮረው ሐቲት፣ መግቢያና መንደርደሪያ እንዲሆን ነው። የምንባቡን ይዘት በጥልቀት ለመረዳት እንዲያስችል፣ ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ‹አጠቃላይ ምንባባዊና ጽሑፋዊ አውድ› በመስጠት ላይ ነው። ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም። እነዚህ ሁለት…
-
የሕዝቅኤል ትንቢትና ቅዱሳት መጻሕፍት
በእያንዳንዱ ትውልድ መቼም መጪና ሂያጅ፤ እንዲሁም ወቅታዊና ጊዜያዊ፤ የሆኑ አያሌ ጉዳዮች አሉ። በአንድ ወቅት መሠረት አድርገን የያዝነው በሌላ ደግሞ "አይ እርሱማ አሁን አይሰራም" እንባላለን። በዚህ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ጥናት ክፍላችን ላይ ያተኮርነው - "ስለ ሕዝቅኤል መጽሐፍ፤ ከቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ጋር፤ ልናውቅ በሚገባን እና ዘመን መጠቅ በሆኑ በአራት የቅዱሳት መጻህፍት ባህርያት ላይ ነው" እነዚህ በተለይ በዘመናችን ቤተክርስቲያን ትኩረት ልትሰጣቸው የሚገቡ መሠረቶች ናቸው።…
-
የሕዝቅኤል መጽሐፍ ጥናት: የእግዚአብሔርን ክብር ማወቅ
ዕለቱ July 31, 593 ቅ.ዓ. ነው። ምናልባትም ሕዝቅኤል በእግዚአብሔር ፊት ልቡን ለማፍሰስ ወደ ኮቦር ወንዝ ዳር ሔዶ ሊሆን ይችላል። ይህም ይሆን ይህ የምናውቀው ነገር ቢኖር ሕዝቅኤል ካህን ወይም የካህን ልጅ እንደነበር እና ይህ ቀን ደግሞ የካህኑ 30ኛ የልደት ዓመቱ እንደሆን ነው። የካህኑ የቡዝ ልጅ እንደመሆኑ እድሜ ልኩን ለካህንነት ሲገዘጋጅ እንደ ኖረ መገመት አዳጋች አይደለም። ሆኖም ግን ከዓምስት ዓመታት በፊት በ597…
-
Yahweh quenches our thirst
The first invitations, here in Isaiah 55:1 “everyone who thirsts come to the waters” focus on the spiritual condition of those who would come, namely those who are “thirsty”. That means those who think they are satisfied and have everything they need, by definition are those who reject this invitation. Those who are truly thirsty are those who know that…
-
የመንግሥቱ ወንጌል: ጽዮን ሆይ ተነሺ ተነሺ ኃይልሽን ልበሺ!
A sermon preached on April 29, 2012 በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ። ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና። የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ። ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው። በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት። ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ…