-
የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ
ማቴዎስ የፍጻሜ መጽሐፍ ነው። ማቴዎስ ኢየሱስን የእሥራኤልን ጥሪ፣ ተሥፋና ተልዕኮ ተላበሶ እንደ ተወለደ ያቀርብልናል። ስለዚህ ኢየሱስ እውነተኛ እሥራኤል ነው። የእሥራኤልን መሢሃዊ ዘር ወርሷል፣ የተለያዩ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችንና ጥብብቆሽን ወደ ፍጻሜ አድርሷል። ይኽም፣ ማቴዎስ “እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ” የሚለውን ቀመር 11 ጊዜ በመደጋገም የወንጌሉን ትኩረት ያሳየናል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ ነው (2:2)፣ የተሰቀለውም የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ ነው (27፡54)። ሲወለድ፣ ሲጠመቅና በክብር…
-
ኦሪትና ሥነ-አፈታታዊ መርሆው
-
ልደቱና የእግዚአብሔር ተስፋ ቃሎች (ኪዳንና ትሥጉት)
ሐዋሪያው ጳውሎስ “እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና” ይለናል (2 ቆሮ. 1:20)። ያለ ኢየሱስ የተስፋ-ፍጻሜ የለም። ማንም ኢየሱስን ዘሎ በቀጥታ የእግዚአብሔርን ተስፋ የሚወርስ ፈጽሞ ሊኖር አይችልም። ያለ ኢየሱስ የሚጠብቀን “ፍርድና ርግማን” ብቻ ነው። በብሉይ የተሰጡትን ተስፋዎች ሁሉ አንድ አማኝ የሚቀበለው “በክርስቶስ” ውስጥ ነው። ይህንን ለማስረዳት፣ በምናባችን “ማጥለያ” እናስብ። ከላይ የሚጨመረው ዘይት ወደ ጠርሙሱ ጠሎ የሚገባው በማጥለያው ጠባብ…
-
በልጅ አንደበት ተናገረን፡ ወንጌልና አስተርዕዮ በእብራውያን መልዕክት (ክፍል-2)
«ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ…በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» (ዕብ 1፡1:1-2) ባለፈው ክፍል፣ እግዚአብሔርን መግለጥ የሚችለው «ራሱ እግዚአብሔር ብቻ» እንደሆን ተመልክተናል። ስለዚህም ያለ አስተርዮ እግዚአብሔርን ማወቅ አንችልም። ስለ ነገረ-አስተርዕዮም (እግዚአብሔር ራሱን እንዴት እንደገለጠ) በቂ ግንዛቤ ካልያዝን ስለ እግዚአብሔር ያለን ግንዛቤ ሊዛባ ይችላል። ሁለቱ የተያያዙ ናቸው። ለምሳሌ በማርቲን ሉተር አስተሳሰብ ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው ነገር፦…
-
በልጅ አንደበት ተናገረን፡ ወንጌልና አስተርዕዮ በእብራውያን መልዕክት (ክፍል-1)
«ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ…በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» (ዕብ 1፡1:1-2) “እግዚአብሔር ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄ በቂ ያልሆነ ወይም የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረን ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱና ተቀዳሚው፤ ስለ ነገረ-አስተርዮ በቂ ያልሆነ ግንዛቤ መጨበጥ ነው። ለምን!? ምክኒያቱም እግዚአብሔርን ማወቅ የምንችለው «እግዚአብሔር ራሱን የገለጠልን እንደሆነ» ብቻ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔርንም መግለጥ የሚችለው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህም ያለ…
-
ነገረ-ክርስቶስ በዕብራውያን መልዕክት: መቅድም
(The Christology of Hebrews: An Introduction) የእብራውያን መጽሐፍ የሹመት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉን ሙሉ ነገረ–መለኮታዊ ክብደት የሚሸከመው «በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ» የሚለው እውነታ ነው (ዕብ 1:3; 1:13; 8:1; 10:12-13; 12:2)። ኢየሱስ ከሁሉ እንደሚልቅ ሰባኪያችን ሲሞግት (ጸሐፊውን የምጠራው ሰባኪው በማለት ነው) የሚያቀርባቸው መሠረታዊ ማስረጃዎች በሙሉ በዚህ ልዕልና እና እውነታ ላይ የተመረኮዙ እንዲሁም የተቃኙ ናቸው። እውነታው «ተቀመጠ» (ኧካቲሰን | ἐκάθισεν)” (1:3) የሚለው ሲሆን፤…
-
የተሾመው መልከ ጼዴቃዊው ካህንና ንጉስ፡ የእብራውያን መጽሐፍ ዳሰሳ
-
መስቀልና ኪዳን፡ የመጨረሻው እራት
[su_quote]እርሱም። ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤ [16] እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው (ሉቃስ 22:15-16)[/su_quote] ይህ እራት እጅግ የከበረ እራት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር ❝ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤ [ግን] ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና❞ ይህ የሚያሳየን ይህ የመጨረሻው እራት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን፣ በመረዳትና ተገቢ በሆነ መንገድ…
-
መስቀልና ኪዳን፡ የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት እንዲሰበስባቸው
“በዚያችም ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ። እናንተ ምንም አታውቁም፤ ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው። ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፥ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፤ ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ። እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው…
-
የተሰቀለ-ክርስቶስ
ዛሬ እንደ ግሪጎሪያን አቆጣጠር የክርስቶስ የስቅለት ቀን ነው። በዚህ ቀን አንድ ጸሎት አለኝ “የዚህ ቀን እውነታ ሳያቋርጥ በዘመናችን እና በትውልዳችን እንዲቀጥል…ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ በመልዕክታችን እንዲኖር! (ገላ 3:1 |፡1 ቆሮ. 2:2-3)” ኢየሱስን እንደ ክርስቶስ መቀበል እና እንደ ተሰቀለ-ክርስቶስ መቀበል ይለያያሉ። እኛ የምንሰብከው “የክርስቶስ መስቀል” ከሌሎች መስቀሎች ልዩ ያደረገው፤ “መሰቀል” የሚባለው እውነታ ሳይሆን (በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ወጣቶች ተሰቅለው ነበር – በተለይ…
-
ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ
❝የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ❞ (ማቴ. 7:15–20) ❝Προσέχετε ἀπὸ τῶν…