-
ባሪያዬ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል
“እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።” (ኢሳያስ 52:13) አብዛኛውን ጊዜ ስለ ጌታ ባሪያ ሥቃይና መከራ ስናስብ የምንጠቅሰው ኢሳ 53:1-12 ነው። ሆኖም ግን ኢሳ 53 መጀመር የነበረበት በ53:1 ላይ ሳይሆን 52:13 ላይ ነበር። ይህን ማስተዋል ምን ፋይዳ አለው? ፋይዳው፣ በብሉይ ኪዳን ላይ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤና ዕርገት በግልጽ ፍርጥ አድርገው ከሚናገሩ ጥቂት ክፍሎች መካከል (ከመዝ 110:1 ቀጥሎ)…
-
ቁጣው ተወግዶልሻልና ተነሺ! – ክፍል አንድ
ይህ ልጠፋዬ፣ በክፍል ሁለት ላይ ለምለጥፈው፣ በኢሳ 51:17-23 ላይ ላተኮረው ሐቲት፣ መግቢያና መንደርደሪያ እንዲሆን ነው። የምንባቡን ይዘት በጥልቀት ለመረዳት እንዲያስችል፣ ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ‹አጠቃላይ ምንባባዊና ጽሑፋዊ አውድ› በመስጠት ላይ ነው። ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም። እነዚህ ሁለት…
-
የብሉይ ነቢያት ጥሪ፣ መልክዕክት እና መጻሕፍት
ይህ ትምህርት ከጥቂት ወራት በፊት “የነቢያት ጥሪ፤ መልዕክት እና መጻሕፍት” በሚል ርዕስ ስለ ብሉይ ትንቢት መጻሕፍት ወደ 4.5 ሰዓት የፈጀ ትምህርት ለዴንቨር የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት LIVE ያስተማርሁት ነበር። አስቀድሜ ይህንን ትምህርት እንዳስተምር የጋበዘኝን ፓስተር ኤርሚያስ አማኑኤልን ከልብ እያመሰገንሁ ሌሎችም ትምህርቱን ማዳመጥ እንዲችሉ በማሰብ እንደገና ተቀድቶ፤ አሁን ከጥናት ጹሑፍ ጋር በአንድ ላይ ተቀናብሯል። ❝እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ…