-
የዐደራ ኑዛዜ ክፍል አንድ፡ በወንጌል ዙሪያ የተደራጀ ሕይወትና ማንነት
2 ጢሞቴዎስ ሕይወትን የሚቃኝና ሕይወታችንን በቅደም ተከተል የሚያደራጅ መልዕክት ነው። መጽሐፉ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጥ መልዕክት ነው። ለግራጫ ሥፍራ የለውም። “የሚቃኝ” ስንል ወደ ዋነኛ ጥሪያችን እንድንመለስ፣ ትኩረታችንን እንድናስተካክል፣ ዋነኛውን ዋነኛ እንድናደርግ፣ የከበረውን ከተዋረደው እንድንለይ የሚያደርገን መልዕክት ነው ማለታችን ነው። ዴማስ ወደ ተሰሎንቄ ምን ሊሰራ እንደሄደ አልተነገረንም። በአንድ ወቅት ግን እንደ ጢሞቴዎስ አብሮ የወንጌል ሰራተኛ ነበር (ቆላ 4፡14; ፊል…
-
የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ
ማቴዎስ የፍጻሜ መጽሐፍ ነው። ማቴዎስ ኢየሱስን የእሥራኤልን ጥሪ፣ ተሥፋና ተልዕኮ ተላበሶ እንደ ተወለደ ያቀርብልናል። ስለዚህ ኢየሱስ እውነተኛ እሥራኤል ነው። የእሥራኤልን መሢሃዊ ዘር ወርሷል፣ የተለያዩ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችንና ጥብብቆሽን ወደ ፍጻሜ አድርሷል። ይኽም፣ ማቴዎስ “እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ” የሚለውን ቀመር 11 ጊዜ በመደጋገም የወንጌሉን ትኩረት ያሳየናል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ ነው (2:2)፣ የተሰቀለውም የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ ነው (27፡54)። ሲወለድ፣ ሲጠመቅና በክብር…
-
ኢየሱስና የቅዱሳት መጻሕፍት ትራኬ
This is part of a half day long teaching series conducted with my students, based on the redemptive historical narrative of the old testament, paying attention to the development of the royal seed promises of God, culminating on King Jesus as the exalted Messiah-Lord, resulting on worldwide blessing and judgement. በሚከተሉት ትምህርቶች መሲሃዊ ተስፋ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ-መለኮት አንጻር ቀርቧል።
-
የመምሰል ጥሪ! (Virtue Formation)
-
የምጋቤ መልእክታት አጠቃላይ ጭብጦች
-
«በእኔ ኑሩ፣ በፍቅሬ ኑሩ!» (ዮሐ. 15:9-17)
በቨርጂንያ በምትገኘዋ ‘የቃል ኪዳን ወንጌል ቤተ ክርስቲያን’ በዘመን መለወጫ ዋዜማ (12/31/2020) የተካፈልኩት ቃል ነው። በዚህ በያዝነው ዓመት የቤተ ክርስቲያን ልሳን የፍቅር እንዲሆን፣ የእርሱን ፍቅር ተረድተን ከግንዱ ጋር የምንጣበቅበት፣ ብዙ የምናፈራበት ይሁንልን። ከግንዱ ጋር የተጣበቀ እንጂ «ከውጪ ተለጣፊ ቅርንጫፍ» ፍሬ አያፈራም። ይህንን አብ ይቆርጠዋል። ግን በእርሱ የሚኖሩትን ፍሬ እንዲያፈሩ አብ ይገርዛቸዋል። ውድ ወዳጆቼ፣ ከእርሱ ጋር እንጣበቅ፣ በእርሱ እንኑር። እናፈራለንና። አሊያ “ያለ…
-
ኦሪትና ሥነ-አፈታታዊ መርሆው
-
እግዚአብሔርና ኪዳናቱ
-
ውርደቱን ተሸክመን፣ ከሰፈር ውጪ እንውጣ (ዕብ 13.7-10)
-
ባሪያዬ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል
“እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።” (ኢሳያስ 52:13) አብዛኛውን ጊዜ ስለ ጌታ ባሪያ ሥቃይና መከራ ስናስብ የምንጠቅሰው ኢሳ 53:1-12 ነው። ሆኖም ግን ኢሳ 53 መጀመር የነበረበት በ53:1 ላይ ሳይሆን 52:13 ላይ ነበር። ይህን ማስተዋል ምን ፋይዳ አለው? ፋይዳው፣ በብሉይ ኪዳን ላይ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤና ዕርገት በግልጽ ፍርጥ አድርገው ከሚናገሩ ጥቂት ክፍሎች መካከል (ከመዝ 110:1 ቀጥሎ)…
-
መስቀልና አስተርዕዮተ-እግዚአብሔር
▶️ በስቅለቱ ዋዜማ ስለ መገለጥ በጥቂቱ (Few words on Theological Methodology) ከሁለት ዓመት በፊት፣ በዚሁ በሕማማቱ ሰሞን፣ መስቀልና ዙፋን በሚል ርዕስ ተከታታይ የሆነ ጽሑፎች አቅርቤ ነበር። መስቀሉ ከመንግሥቱ ጋር ያለውን መስተጋብር፣ ድካም ከኃይል ጋር ወዘተ…ለመዳሰስ ተሞክሯል። በደሙ መንግሥቱ ተመርቃለች። ባለፈው ዓመት እንዲሁ፣ “መስቀልና ኪዳን” በሚል በተከታታይ፣ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን እንደመረቀ፣ መስቀሉን ከኪዳን አንጻር ተመልክተናል። በደሙ ኪዳን ተመረቀ። በዚህ…
-
ቁጣው ተወግዶልሻልና ተነሺ! – ክፍል አንድ
ይህ ልጠፋዬ፣ በክፍል ሁለት ላይ ለምለጥፈው፣ በኢሳ 51:17-23 ላይ ላተኮረው ሐቲት፣ መግቢያና መንደርደሪያ እንዲሆን ነው። የምንባቡን ይዘት በጥልቀት ለመረዳት እንዲያስችል፣ ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ‹አጠቃላይ ምንባባዊና ጽሑፋዊ አውድ› በመስጠት ላይ ነው። ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም። እነዚህ ሁለት…
-
የተሰቀለ-ክርስቶስ፡ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ በመልዕክታችን ይኑር
የአንደኛ ቆሮንቶስ 1:10 – 2:5 ሐቲት ኢየሱስን እንደ “ክርስቶስ” መቀበል እና እንደ “ተሰቀለ-ክርስቶስ” መቀበል ይለያያሉ። እኛ የምንሰብከው “የክርስቶስ መስቀል” ከሌሎች መስቀሎች እንዲለይ ያደረገው፤ “መሰቀል” የሚባለው እውነታ አይደለም (በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ወጣቶች ተሰቅለው ነበር – በተለይ በ4 ዓ.ዓ. አካባቢ ላይ)፤ ክርስቶስም የሚለው ቃል አይደለም (ብዙ መሲህ-ነኝ ባዮች ከኢየሱስ በፊት እንደ ስምዖን ወልደ-ጊዮራ ያሉ፣ በኋላም እንደ ስምዖን ወልደ-ኮኸባ ተነስተው ነበር) ይልቁንም…
-
ተወለደ!
‹ለምን ተወለደ?› የሚለው ጥያቄ የሕይወት ጥያቄ ነው። ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን ላይ «ተወለደ» የሚለው ቃል ወልድ ፍጹም ሰው ስለ መሆኑ (ስለ ነገረ-ትሥጉት) ከሚነግሩን አገላለጾች አንዱና ዋነኛው ይሁን እንጂ “ብቸኛ” ግን አይደለም። በአዲስ ኪዳን የትሥጉት ነገረ-መለኮት በብዙ ቃላት ያሸበረቀ ነው። «ተወለደ» በሚለው እሳቤ ላይ በተጨማሪ፣ በአዲስ ኪዳን ላይ እኩል አጽንዖት ተሰጥቷቸው የምናገኛቸው ተጨማሪ ነገረ መለኮታዊና ሙያዊ የሆኑ ቃላት አሉ። በእነዚህ ቃላት…
-
ልደቱና የእግዚአብሔር ተስፋ ቃሎች (ኪዳንና ትሥጉት)
ሐዋሪያው ጳውሎስ “እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና” ይለናል (2 ቆሮ. 1:20)። ያለ ኢየሱስ የተስፋ-ፍጻሜ የለም። ማንም ኢየሱስን ዘሎ በቀጥታ የእግዚአብሔርን ተስፋ የሚወርስ ፈጽሞ ሊኖር አይችልም። ያለ ኢየሱስ የሚጠብቀን “ፍርድና ርግማን” ብቻ ነው። በብሉይ የተሰጡትን ተስፋዎች ሁሉ አንድ አማኝ የሚቀበለው “በክርስቶስ” ውስጥ ነው። ይህንን ለማስረዳት፣ በምናባችን “ማጥለያ” እናስብ። ከላይ የሚጨመረው ዘይት ወደ ጠርሙሱ ጠሎ የሚገባው በማጥለያው ጠባብ…