08_00_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ_መግቢያ (Audio)
ሙሉዉን የማጥኛ ጽሑፍ: የዚህን ጥናት ማብራሪያ ጹሑፍ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ Kingdom and Sovereignty
እግዚአብሔር; ቃሉና ባሕሪው- ልዑል ንጉስ – ክፍል 2
[su_note note_color=”#efeeee”][/su_note]
መግቢያ
በብሉይ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር መንግሥት ባይብራራም ነገር ግን የእግዚአብሔር አገዛዝ በፍጥረት; በሰማይና በምድር ባሉ ተቀሳቃሽ ፍጡራን; በዚህ ዓለም ላይ ባሉ መንግሥታትና ነገስታት ላይ እንደዚሁም ደግሞ በተለየ መልኩ በራሱ ፍጹም ነጻ የጸጋ አነሳሽነት ጠርቶና ዋጅቶ ገንዘቡ ባደረገው ሕዝቡ ላይ መንገሱ በይፋ ግልጽ ሆኖ የሚታይ ክስተት ነበር። ይህም የአንዱ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ መንግሥት ነው!
[column-group][column]የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት (ጌትነንትና ገዢነት) በሁለት መልኩ ተገልጧል። ሉዓላዊ ጌትነት እግዚአብሔር ራሱን ለፍጥረቱ የሚገልጥበት መንገድ ነው። እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ በመፍጠር; በመመገብ; በመቤዠት ሆነ በመፍረድ እንደሚሰራ ተመልክተናል። እነዚህንም ሥራዎች ሲሰራ ለፍጥረቱ ጌትነቱን ለመግለጽ ነው።
- ማሳሰቢያ፡ ጌትነት የእግዚአብሔር የውስጥ ሕይወት ወደውጪ መንጸባረቁን ያመለክታል እንጂ በክበበ-ሥላሴ የውስጥ እርስበርስ ሕይወት የጌታና የሎሌ ግንኙነት የለውም። ይህ ግንኙነት “ሁሉን የፈጠረው የሥሉሱ እግዚአብሔር” እና “የፍጥረቱ ግንኙነት ነው።”
- ይህም ጌትነት/ልዕልና በሁለት መልኩ ይገለጻል።
- የሁሉ ጌታ፡ ወሰን-መጠቅ/ሉዓላዊ ጌትነት (Universal/Providential Kingdom) ሲሆን፡ ይህ መንግስት ሰማይንና ምድርን ያካለለ ነው; አገዛዙም ፍጥረቱን ሁሉ የሚሞላ ልዕልና ነው። በመንፈሱም በፍጥረቱ ወዲህና ወዲያ እየተንቀሳቀሰ ያስተዳድራል!
- የሕዝቡ ጌታ፡ ታዳጊ/ ኪዳናዊ ጌትነት (Particular/Redemptive Kingdom) ሲሆን ግዛቱ ገንዘቡ የሆነ ሕዝቡ ሲሆን; በሕላዌነቱ በመካከላቸው በመረጠው ሥፍራ አብሯአቸው ይኖራል! በኤደን ለመጀመሪያውቹ ሰዎች ለአዳምና ለሔዋን; በመገናኛው ድንኳን ለእሥራኤል በምድረበዳ ; በጽዮን በቤተ-መቅደሱ ሥፍራ; በኢየሱስ ሰውነት ከመስቀል በፊት; ከተነሳ በኋላ ደግሞ በምድር በቤተክርስቲያን; በሰማይ “በአዲሲቱ ኢየስሩሳሌም/ ጽዮን ተራራ” በመጨረሻ ከሰማይ ወደምድር በምትወርደው አዲሲቱ ሰማይና አዲስቱ ምድር እግዚአብሔር እጅ ባልሰራው መቅደስ ከሕዝቡ ጋር ለዘላለም ይኖራል!
- ሁለቱም የሚገልጹት የአንዱ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሁለት ገጽታዎች ናቸው። እግዚአብሔር ለፈጠርው ፍጥረት ጌትነቱን ሲገልጽ ልዕልናውን በነዚህ በሁለት መልኮች ይገልጣል ማለታችን ነው።
እ/ር በትድግና ጌትነቱን ለሕዝቡ ሲገልጥ አላማው ጌትነቱን ለምድርና ለሰማይ ለመግለጥ ነው። ስለዚህ አጥብበን ያየነው የእግዚአብሔር አገዛዝ አላማው ጌትነቱን ለምድር ሁሉ ለመግለጥ ነው።[/column][column]
በመጀመሪያ የእግዚአብሔር መንግስት ሥንል ታድያ ምን ማለታችን ነው?
- ሥልጣን ማለት የመግዛት መብት ማለት ነው (ምሳ፡ Luke 19፡ 11-12)
-
ሰማይና ምድር፡ ይህ አገላለጽ በተለያዩ አገባቦች የተለያዩ ትርጉሞች አሉት፡ ለምሳሌ
-
ሰማይ በመጽሀፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፍጹም ሥልጣን መመንጫ ሆኖ ወክሎ ሲገባ; ምድር ደግሞ ሥልጣኑ የሚገለጥበትን ክልል ይወክላል።
ኢሳ 66፡ 1-2፡እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት; የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? 2 እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር;
-
ሰማይና ምድር፡ ጠቅላላ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ይገልጻል
ዘፍ 1:1 “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ”
- በአዲስ ኪዳን ሰማይ ኢየሱስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደአባቱ የሁሉ ጌታ ይሆን ዘንድ ሲያርግ በግርማው ቀኝ የተቀመጠበት ሥፍራ ነው። እስኪመለስ ድረስ በዚያ ሆኖ ይቆያል። በዚህ ሥፍራ አሁን ቤተክርስቲያንን ራስ ሆኖ የሚያስተዳድርበት የሽግግር መንግሥት ነው። (ሐዋ 3፡ 21;)
-
Ephesians 1:20–23 ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል; 22 ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። 23 እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።
[/column][/column-group]
