One Comment

  • kassahuntm

    ለቅዱሳን ወንድሞችና እህቶች፤

    ይህን ትምህርት ደጋግሜ ሳነብና ስሰማ ያለኝ መረዳት ስፋትና ጥልቀቱ እያደገ ሲሄድ አስተዋልኩ። በተልይ ክፍል 07 እጅግ መጣም መሰረታዊ ስለሆነ ደጋግሞ መስማት እንዲሁም በጽሁፍ መልክ የቀረበዉን በመጽሃፍ ቅዱስ በመታገዝ ማንበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ሆኖ አግንቼዋልሁ።
    ዉድ ወገኖች፤ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አምልኮአችንና ጸሎታችንም ከእግዚአብሄር የዉስጥ ህይወት ጋር የተያያዘ ነው። ማለቴም ይህን ትምህርት በሚገባ መረዳት የሁለቱን ኪዳናት ተዛምዶ ለማስተዋል እንድሁም መጽሃፍ ቅዱስን ክርስቶስን ባማከለ መልኩ ለማንበብ ከማስቻሉም በላይ በማን ሃይል፣ በማን ስም ወደማን እንደምንጸልይ ይገባናል። አምልኮአችንም እንዲሁ ይህንኑ የእግዚአብሄርን የዉስጥ ( ሱሉስ ህይወት ግንኙነት) የተከተለ ነዉ። ባለኝ መረዳት ላይ እርማት ካለችሁ በምስጋና እቀበላለሁ። ወንድማችን ሳሚ ደግሞ ይህን ጥልቅ፣ሰፊና ሚስጥር የተሞላ ርእስ በእኛ ደርጃ እንደሚገባን አድርጎ ያስተማረን ከጌታ በሆነለት ተሰጥኦ ስለሆነ ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን፤ በረክት አድርጎ መካከላችን ያስቀመጠዉ ጌታ ስሙ ይባረክ። አገልግሎቱንም ይባርክለት።

    የጌታ ሰላምና ጥበቃ ከእናንተ ጋር ይሁን!

    ካሣሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published.