Audio Posts,  YHWH,  ሕያው እግዚአብሔር,  ትምህርተ ድነት

009-01: The Person of YHWH:- To know Him is to have Eternal Life

[ap_tab_group type=”horizontal”]
[ap_tab title=”Audio”] [/ap_tab]
[ap_tab title=”Excerpt”]Salvation is a relational knowledge of God. In salvation, we are being elevated from our sinful status to a status of glory. The status of our glory was accomplished by the Son leaving the glory he had with the father eternally, which was intrinsic to his own person. He did this in order to do his father’s bidding to a lowly/ impoverished status that was foreign to his own person (John 17:19, Phil 2:9-11) and having accomplished His mission through the ignominious death on the cross, he was glorified in order to glorify the father by glorifying us.
In summary salvation is a personal-knowledge of the Triune God, an intimate union with the Father and the Son through his personal word (message) that he left us through the apostles and the personal indwelling presence of the Holy Spirit abiding in us.[/ap_tab]
[ap_tab title=”Scriptural References”]
John 17:3
1 John 4:8–10
John 17:7–8, 26
[/ap_tab]
[/ap_tab_group]

 


እግዚአብሔርን ማወቅ የነገር ሁሉ ግብ ነው


ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት!

“ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።  እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።  እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤  አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ”

በዚህ በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ “ሰዓት” የሚለው ቃል ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ያለ ትኩረትና በዮሐንስ-ነገረ መለኮታዊ ትረካ ውስጥ እያደገ የመጣ ሐሳብ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዓት ከወልድ ተልዕኮ ጋር የተያያዘ ጥልቅ መለኮታዊ እውነትን የሚያንጸባርቅ ቃል ነው። ለምሳሌ ያህል፤ ለማርቆስ የሰዓቱ መድረስ (ማር 1:15) ከነብያት ድምጽ ጋር በማገናኘት (ማር 1፡2-3)፤ በኢየሱስ ማንነትና አገልግሎት (አገልግሎት የሚለውን ቃል ለክርስቶስ ስጠቀም በቃልና በሥራ የተሰጠውን የክርስቶስን መለኮታዊ አስተርዕዮ ማመልከቴ ነው – what some call the ‘Christ-event’) የእሥራኤልን ተሥፋ በሰውነቱ ለብሶ መገለጡን ይገልጻል። ስለዚህ በማርቆስ ወንጌል ሰዓት በክርስቶስ (የዳዊት ልጅ -መዝ 2፡7/ 2ሳሙ 7:14) አገልግሎት (በማንነቱ፤ በቃሉናና በሥራው) አማካይነት የእግዚአብሔር መንግሥት መጥባቱን ያውጃል። እግዚአብሔር የሰጣቸው የማዳን ተስፋዎች ሁሉ አሁን በገሊላ አውራጃ እየተፈጸሙ መሆናቸውን ያውጃል። ይህም የወንጌል መጀመሪያ ነው።

ወንጌላዊው ዮሐንስ ግን የክርስቶስን ማንነት ከድንግል ከመወለዱ (ወይም ከትሥጉት) አንድ እርምጃ ዕምር ብሎ ከሥነ-ፍጥረት መጀመሪያ ይጀምራል። እንደዚሁም የክርስቶስን አገልግሎት ትረካ ከገሊላው አገልግሎት ፈቀቅ አድርጎ ከአንድ የሰርግ በዓል ድግስ ይጀምራል። በዚህ መጽሐፍ ክብር፤ ምልክት፤ የአብ ፈቃድ መፈጸም፤ የወልድ ተልዕኮ፤ መውጣትና መውረድ፤ የመስቀሉ ውርደት፤ የዘላለም ሕይወት ከዚህ አንድ ቃል -ሰዓት- ጋር የተያያዙ ናቸው። ሆኖም ግን ይህች ሰዓት በዮሐንስ የነገረ-መለኮት ትረካ ውስጥ ከሰው ልጅ አገልግሎት መጀመሪያ ጋር ሳይሆን ከሰው ልጅ ታልፎ ከሚሰጥባት ለሊት ጋር የተያያዘች ነች። ለምሳሌ ያህል የመጀመሪያውን ምልክት ሲያደርግና ደቀ መዛሙርቱ በእርሱ ሲያምኑበትና ክብሩን ሲያዩ ይህች ሰዓት ገና አልደረሰችም፡

  • “የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፤ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።  ኢየሱስም፤ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት”  ዮሐ 2:3-4
    • (“οὔπω ἥκει ἡ ὥρα μου” የአዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ሰዓቴ’ ሆራ-ሙ’ ለሚለው የግሪኩ ቃል ይበልጥ ይቀርባል)
  • ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም። ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበትና። ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ካደረጋቸው ምልክቶች ይልቅ ያደርጋልን? አሉ። (John 7:30–31)
  • ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።  ኢየሱስም ደግሞ። እኔ እሄዳለሁ ትፈልጉኛላችሁም በኃጢአታችሁም ትሞታላችሁ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አላቸው። (John 8:20–21)

ሆኖም ግን ይህች ሰዓት መድረሷን አብ ለሚወደው ልጁ “ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን” ብለው በመጡት በግሪክ ሰዎች አመለከተው። ይህም አሕዛብ ወደ ኪዳኑ በረከት መጠጋታቸው ለአብርሃም የተሰጠውን የተሥፋ ቃል አሁን በወልድ የመስቀል ተልዕኮ የሚፈጽምበት ሰዓት መድረሱ ሲያመላክት

  • ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።… አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ? ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።  አባት ሆይ፥ ስምህን አክብረው። ስለዚህም። አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ…አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤  እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።  በምን ዓይነትም ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ። John 23:27–33
  • ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። (John 13:1)

ከዚህ ወደ ጥልቅ ጅረት ከሚወስደን ዋና እንውጣና ወደ ጀመርንበት እምር እንበል። ወልድ ወደ መስቀል ከመውጣቱ በፊት ሲጸልይ (የታላቅ-ሊቀ-ካህናት ጸሎት) መጀመሪያ ከአፉ የወጣው ቃል “አባት ሆይ ሰዓቱ ደርሶአል” ነበር። የዚህች ሰዓት ትልቅነት የተመሰረተው በዚህች ሰዓት ውስጥ የሚከናወነው ሥራ ነው።

  • መለኮታዊ ተልዕኮ ነው፡- ይህ ሥራ አለም ሳይፈጠር አብ ለወልድ የሰጠውና በአገልግሎቱ አብ ሲያሳየው (ዮሐ 5:19-39) ለነበረው ሥራ ጫፍ ነው። በዚህ ተልዕኮ አብ ይከብራል። ይህም የመስቀሉ ተልዕኮ ነው። “የሰው ልጅ ከምድር ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ” የሚለው ሐረግ ዮሐንስ እንደዘወትሮው ድርብ ትእምርትን በመጠቀም የክርስቶስ ውርደት የክብር ጎዳና እንደሆነ ያሳየናል። የሮማውያን ወታደሮች መስቀሉን በገመድ ወደ ላይ ከፍ እያደረጉ ወልድን በአየር ላይ ሲያንጠለጥሉት፤ በዚህ አንድ የውርደት መስቀል ላይ ወልድ የአባቱን ሥራ በፈጸሙ የሚከብርበትም መንገድ ነው። ሥለዚህ መስቀሉ የክብር ጎዳና ነው። በዚህ መንገድ ወልድ ይዋረዳል፤ አብ ይከብራል፤ ወልድን አብ ዓለም ሳይፈጠር በነበረው ክብር መልሶ ያከብረዋል፤ በሰዎች ልጆች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይጎናጸፋል፤ የዚህ ዓለም ገዚ ወደ ውጪ ይጣላል!
  • መለኮታዊ አስተርዕዮ ነው፡- በዚህች ሰዓት በተገለጠው ሥራ ውስጥ እውነተኛው አምላክ አብና የተላከው ወልድ ተገልጠዋል።
  • የዘላለም ሕይወት ነው፡’ ምልክቶቹ የተሰጡበት ዓላማ አንባቢው፡ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ ውጤቱም በስሙ የዘላለምሕይወት ይሆንልን ዘንድ ነው
    • ዘላለማዊ ሕይወት ኢየሱስ ዳግም ሲገለጥ ዕውን የሚሆነው የመጪው ዘመን ሕይወት ማለት (The Life of the age to come, “zoe-aionios”)
    • ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥ 30 አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም/ዘመን የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።31 ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።” ማር 10፡ 30-31
    • እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ”

ከዚህ የተነሳ የዘላለም ሕይወት ከላኪው አብና ከተላኪው ወልድ ጋር የተቆራኘ ነው። ያለ ወልድ ሕይወት የለም። ሆኖም ግን ልንገነዘበው የሚገባው ነገር፤ አብንና ወልድን ማወቅ ያለው ወልድ በሰጠን ቃሎቹና በፈጸማቸው ሥራዎች ውስጥ መሆኑን ነው። ዮሐንስ የአንድያ ልጁ የሆነውን ክብሩን ያየነው በምልክቶቹ (በሥራዎቹ) ውስጥ እንደሆን ያሳየናል። ሰዎች ክብሩን እንዴት አዩ? ወልድ ከባህር አጠገብ በጀልባ ቁጭ ብሎ፤ ታዳሚው አንድ በአንድ በአጠገቡ እያለፉና አፋቸውን በእጃቸው እየጫኑ፤ “አቤት የእግዚአብሔር ልጅ?” እያሉ ነበር? ታስታውሱ እንደሆን ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲሰብሰቡ ማቴዎስ ሲነግረን አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ ትምሕርቱንም ሲጨርስ ሰዎች ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና” ይላል። ስለዚህ ሕይወት ያለው ወልድን በማወቅ ውስጥ ነው። ወልድንም ማወቅ በቃሉና በሥራው ላይ ያነጣጠረ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ አብ የሚወደውንና ወደ ዓለም የላከውን አንድያ ልጁን እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የፈጸመውን ተልዕኮ ማወቅ እንዲሁ ግርድፍ ያለ እውቀትና ቃል ብቻ ሳይሆን ሕይወትን የሚሰጥና ለማዳን የሚችል መለኮታዊ ሐይል ነው።

  • በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። (1 John 4:7–10)

የብሉይ ኪዳን ራዕየ-መለኮትና የአዲስ ኪዳን የሁለቱ አካላት ተልዕኮ

እዚህ ጋር ነካ አድርጌ ላልፍ የምፈልገው ነገር ቢኖር (እጅግ ሰፋ ያለና የረቀቀ እውነት ቢሆንም በአጭሩ) የወልድ ተልዕኮ ምንም እንኳ የመዋጀት ተልዕኮ ቢሆንም፤ ነገር ግን ይህ አንዱ የውጆት ተልዕኮ እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትም መንገድ እንደሆነ ጭምር ነው። ይህም የወልድ ተልዕኮ የሥሉሱ አምላክ አስተርዕዮ ነው። ለምሳሌ ያህል፤ እሥራኤአውያን ከግብጽ ባርነት ሲዋጁ ያህዌህ ኤሎሂም “ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።” Exodus 6:7። ይህ ማለት በአንዱ የዘጸዓት ትድግና ሥራ ውስጥ (እዚህ ጋር የሙሴን ተልዕኮና የወልድን ተልዕኮ ማነጻጸር ተገቢ ነው) እሥራኤላውያን አምላካቸውን እንደ ያህዌህ ያውቁታል። ምክኒያቱም ከዚህ ቀደም ራሱን ሲገልጥ ያህዌህ ሁሉን እንደሚችል እንደ ኤልሻዳይ እንጂ (እዚህ ጋር ዘፀ 3:14-15 እና ዘፀ 6:2 አወዳድሩ) በቃል ኪዳን ሥሙ አልተገለጠም ነበርና ነው። ይህ ማለት ያህዌህ ሕዝብን ገንዘቡ አድርጎ፤ የሕዝብ አምላክ ሆኖ መገለጡ(የሕዝቡ የቃል ኪዳን ጌታ – in this Exodus narrative, you have here the beginning of sonship language applied to a nation present, unlike the Genesis narrative) የዘጸዓቱ ትድግና የቃል ኪዳን ሥሙን ፍንትው አድርጎ መግለጡን ያስያል። ከዚህ የተነሳ ያህዌህ ለአባቶች (ለአብርሃም፤ ይሥሐቅና ያዕቆብ) ሲገለጥ (ሲናገርና ሲሰራ) በመገለጡ ውስጥ ስለሚያመልኩት አምላክ የሚተላለፍም እውነት አለ። ያህዌህ ለአባቶች ተገለጠ (ዘፍ 17፡1-2፤ 35፡9-13) በሚሉት ሥፍራዎች ላይ እንደ ኤልሻዳይ እንደተገለጠ ጸሐፊው ይነግረናል (ወደ ፊት ሰፋ አድርጌ እገልጸዋለሁ)። የዘጸዓቱ ትድግና ግን ለቅዱሱ ስም ያህዌህ መገለጥ የሚመጥን ሥራ መሆኑን እናያለን። ስለዚህ የእስራኤል መዋጀት ግቡ እስራኤል እግዚአብሔርን ማወቋ ነበር። ትድግናው አስተርእዮ አዝሏል ማለት ነው። (በዘጸዓት መጸሐፍ ስሙን የሕዝብ-አምላክ ከመሆኑ፤ ከአብሮነቱና ከ ‘ያውነቱ’ ያገናኘዋል)። አሁንም ጌታችን ሊፈጽመው ባለው ዳግም-ጸዓት (ሁለተኛ ትድግና) ተልዕኮ ውስጥ የስሉሱ አምላክ መገለጥ ያዘለ ትድግና ነው።

የዘላለም ሕይወት እግዚአብሔርን ማወቅ ነው

የዚህ ቀደሙ ኪዳን ድክመት የተመሰረተው በኪዳኑ መካከል ከቆሙት መልዕክተኞች የተነሳ ነው። በኪዳኑ መካከል የእግዚአብሔር መልአክ እና የቃል ኪዳን መልዕክተኞች ሁሉ ቁንጮ የሆነው ሙሴ ነበሩና ነው። በዚህ ኪዳን መልዕክቱም እንዲሁ አስተርዕዮውም መለኮታዊ ነበሩ። ሆኖም ግን የመገለጡ ተረካቢዎቹና ገላጮቹ ግን መለኮታዊ አይደሉም። ከዚህ የተነሳ በልጁ የተመረቀውን ኪዳን የላቀ ኪዳን እንደሆን የዕብራውያን ጸሐፊ ሲናገር ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።  በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን?” (Hebrews 2:1–2፟) ይለናል። የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ክርስቶስ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ጣቱን ጦቁሞ “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም (John 3:30–32)” ቃሎቹ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው። ሥራዎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ናቸው። እግዚአብሔር ከሰማይ የላከው ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ መንፈሱንም ሲሰጠው አይሰፍርምና! የፊደሉ ሕግ አሁን በመንፈስ ሕግ ተተክቷል። (ይህ ማለት ጨርሶ ትእዛዛት ሥፍራ የላቸውም ማለት ወይም የሕጉን መጽሐፍ አናነብም ማለት አይደለም። ሆኖም ግን ሕግ እንደ ኪዳን (law covenant) ሊፈጽም ያልቻለውን ልጁንና መንፈሱን ልኮ የሕግን አላማ በእኛ በመንፈስ ለምንመራና በክርስቶስ ለምናምን እውን ይሆናል) እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ መልአክ አልላከም። ከላይ እንደተመለከትነው በዚህም አንድ ተልዕኮ ውስጥ አብ ሁለት መልዕክተኞችን ልኳል። “በዘመኑ ፍጻሜ ግን ከሴት የተወለደውን ከሕግ በታች የሆነውን ልጁን ላከ….አባ አባት ብሎ የሚጮሀውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ! ገላ 4:4” እነዚህ ሁለት አካላት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም እንደ ሙሴ ከውጪ ሰምተው እግዚአብሔርን የሚገልጡ ሳይሆኑ፤ መግለጣቸውም መገለጡም ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ነው። ምክኒያቱም ሁለቱም አካላት ከአብ ጋር አንዱ ሕላዌ ገንዘባቸው ስለሆነ ነው። ከዚህ የተነሳ የወልድ ቃል ከብሉይ ሕግና ከነብያት ቃል እጅጉን ይልቃል ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። መጻሕፍትን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?” (John 5:46–47)። ከ11ኛው ክፍለዘመን ቤተክርስቲያን አበው መካከል እንደ ምሶሶ ተደርገው ከሚቆጠሩት መካከል አንዱ የሆነው“ከካንትቤሪ የሆነው አንሰልም” “ለምን አምላክ ሰው ሆነ?-Cur Deus Homo” በተሰኘው መጽሀፉ ከብዕር ጓደኛው ጋር ሲወያይ እንዲህ ብሎ ጻፈ፡ (ለመተርጎም ልሞክር)

“የሰው ልጆች መዋጀት ከራሱ ከእግዚአብሔር በስተቀር በሌላ ሰው አሊያም መልአክ አማካይነት ሊከናወን አይችልም። ከእግዚአብሔር ሌላ የሆነ አካል ሆኖ ቢሆን ከዘላለም ሞት ያዳነን፤ የዳኑት ለዚህ ላዳናቸው አካል (ሰው ወይም መልአክ) አዳኜ ብለው ባርያ በሆኑለት ነበር። ታድያማ ይህ እንዴት መዳን ይባላል! ምክኒያቱም የዳኑት ከእግዚአብሔር ሌላ ለሆነው ባርያ ናቸውና። ይህ አሁን እንደሆነው ማለት ነው…በአየሩ ላይ ላለው አለቃ ሰዎች ይገዛሉና ”

ይህ የቤተ-ክርስቲያን አባት አስምሮ የተናገርው ነገር ምንድር ነው፤ የሰው ልጆች ሐጥያት እምብርት አመጽ ስለሆነ፤ ይህም ለእግዚአብሔር አለመገዛት፤ ከእግዚአብሔር ሥልጣንና አገዛዝ ማፈንገጥ፤ የእግዚአብሔርን ክብር በሌላ በተፈጠሩ ነገሮች እንደዚሁም የእግዚአብሔርን መለኮታዊ እውነት በሐሰት መለወጥ እስከሆነ ድረስ፤ እውነተኛ መዋጀት እነዚህ ነገሮች ያስተካከለ እንደሆን ብቻ ነው። ሰው ወደ እግዚአብሔር ሥልጣን ሲመለስ፤ ተንበርክኮ ይህንን አምላክ አዳኜ ያለ እንደሆን ብቻ ነው። አንሰልም ጥሩ አይቷል። በነብዩ ኢሳያስም ያህዌህ እንዲህ ይላል

  • እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም። እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።  ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።  ስለ እኔም። በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ። የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይባላል” (Isaiah 45:20–25)

ስለዚህ እውነተኛ መዳን ሁለት ነገሮችን ያቅፋል። እነዚህ ሁለት እውነታዎችን በብዙ መንገድ አዲስ ኪዳን ያሰቀምጣቸዋል።  ለግልጽነት እንዲመች ግን ሁለት መደቦችን ልጠቀም። በአንድ እጅ እነዚህን ቃሎች እንያዝ፦ መጽደቅ፤ መዋጀት፤ እርቅ፤ ሰላም፤ መግባት፤ ሥርየት። በሌላ እጅ ደግሞ መክበር፤ ልጅነት፤ ተስፋ፤ ርስት። እነዚህ ሁለት እውነታዎች የሚያንጸባርቁት በአንድ ወገን ከየት እንደመጣን ሲሆን በሌላ እጅ ደግሞ ወዴት እንደምንሔድ ነው። በአንድ ወገን ድነናል በሌላ ወገን ደግሞ ገና በሙላት እንድናለን። መጽሀፍ ቅዱሳዊ ደህንነት ‘ከ’ እና ‘ወደ’ የሚሉትን መስተዋድዶች ገንዘቡ ማድረግ አለበት።

  • እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና (2 Peter 1:9–11)

ክርስቶስ ራሱን መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ ለሐጥያታችን ሥርየት ሲል “ሐጥያታችንን በእንጨት በሰውነቱ ተሸክሞ ከእግዚአብሔር አብ ቁጣ፤ ከሞትና ከሐጥያት አድኖኗል። እዚህ ጋር ግን አያበቃም። ይህ ግማሽ እውነት ነውና። ስለዚህ እውነተኛ ደህንነት ግን “የልጁን መልክ” በመምሰል መክበርን ገንዘቡ ማድረግ አለበት። የመጨረሻ ግባችን ልጆች መሆን ነው (1 ዮሐ 3:1-5) መዳናችንን ከሌሎች ፍጥረታት መዋጀት የሚለየው መዳናችን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስን መምሰላችን ነው። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በመሆን ከመለኮት ባሕርይው እንድንካፈል ተዋጅተናል (2 Pet 1:2; John 1:2-3)። ይህ ከፍ ብዬ ወደ ጀመርኩት ነጥብ ያመራኛል። ይህም የመንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ተልኮ መምጣቱና በልባችን ማደሪያ መሥራቱ አላማው በግል የልጁን መልክ እንድንመስል እንዲሁም እንደ አካል ደግሞ እግዚአብሔር የሚኖርበት ሕያው ቤተ-መቅደስ ሆነን እንድንሰራ ነው (there is an eschatological progression of sonship as well as temple imagery) መንፈሱንም ‘የክርስቶስ መንፈስ’ በማለት የመንፈስ ቅዱስን ተልዕኮና ሥራ ይገልጽልናል። ይህ መንፈስ በስሉሱ አምላክ የውስጥ ሕይወት ውስጥ የሚሰርጽ እንደመሆኑ መጠን ለአካሉ የሚመጥነውን ሥራ ደግሞ በእኛም ሕይወት ይሰራል። ከዚህ የተነሳ መዳናችንን ስሉስ በሆነ መልክ በኤፌሶን ተገልጧል። ይህም የምንቀርብበት መንገዱም ሆነ ፍጻሜያችን በስሉሱ አምላክ የተቀመረ ነው። ስለ አቀራረባችን ሲያሳየን “በእርሱ [በክርስቶስ] ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና (Ephesians 2:18)” የምንቀርበው በአብ ፊት ሲሆን መንገዱ ደግሞ በወልድ ሥራ አማካይነት በአንዱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ነው (depicted in highly in Trinitarian terms but reverse order. THe father revealed himself to us, through Christ, by the holy Spirit. We experience this revelation by the Spirit, through Christ.)

ከዚህ የተነሳ የመንፈስ ቅዱስን ፕሮጄክት ሐዋርያው ሲነገርን “

  • እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። (2 Corinthians 3:18)

በውስጣችን ያለው የልጅነታችን መንፈስ ሊመጣ ላለው ርስት መያዣ መሆኑንም መጽሐፍ ቅዱስ ያሳየናል (በዚህ ምክኒያት ሐዋርያው መንፈስ ቅዱስን የርስታችን መያዣ/አራቦን የሚል ሥያሜ ይሰጠዋል ‘ἀρραβὼν  ኤፌ. 1:14’)

ስለዚህ መጽሀፍ ቅዱስ በልጁ በኩል የተገለጠውን ደህንነት ‘የማስመለጥ’ ተልዕኮ ብቻ ሳይሆን (ምንም እንኳ ይህ ትልቁን ሥፍራ የሚይዝ እውነት ቢሆንም)  ‘የመለወጥ’ ተልዕኮን ይጨምራል። ይህንን ተልዕኮ ወልድ ይዞ ተገልጧል። ለማጠቃለል በዮሐንስ 17 ላይ የወልድ ተልዕኮ፦

  1. የአብን ሕልውና ወልድ ለደ/መዝሙርቱ ገልጧል
    1. ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው ዮሐ 17:6
    2. እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ። John 17:26 (AMHB)
  2. ሕይወትን የሚሰጡ ቃሎች ከአብ ዘንድ ወደ ደቀ/መዛሙርቱ፤ (ከደቀመዛሙርቱ ወደ እኛ ቀርቧል)
    1. ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤ የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ። John 17:7–8 (AMHB)
    2. በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። John 17:17 (AMHB)
  3. ከአብ ዘንድ ያለውን የወልድን ክብር በውስጣችን በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንካፈላለን (የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ሚና ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ ማሰር ነው፤ በዚሁ ወንጌል በዮሐ 14 ላይ ይህንን ሚና አብና ወልድ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከአማኙ ጋር እራት በመብላት ተገልጧል)
    • ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። John 17:20–23 (AMHB)

ስለዚህ መዳን እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔር ሲያድነን ከጠላትነትና ከሃጥያተኛነት ወደ ክብርና ወደ ልጅነት አምጥቶናል። ከአባቱ ጋር የመለኮት ክብር ገንዘቡ ሆኖ ሲኖር ከነበረበት ልዕልና ክብሩን ወደ ማታውቅ ወደዚህች ዓለም በመምጣት ራሱን አዋረደ (John 17:19, Phil 2:9-11) ። የመጣው የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም ነበር። ሆኖም ግን በዚህ በተዋረደ የመስቀል ሞት በኩል የአባቱን ፈቃድ በመፈጸሙ አብን አከበረ። አብ ደግሞ ወልድን ያለልክ አከበረው፤ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጠው፤ ከብሮ እኛንም አከበረን። በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ደግሞ ክብር ገንዘባቸው ሆነ!

  • እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤ አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።

ስለዚህ እኛም በባህሪያችን ሞት የተገባን፤ በሐጥያት የተለወስን ጸያፍ ሰዎች፤ ከልጁ ሕይወት/ደም ክቡርነት የተነሳ ከዚህ ስሉስ ሕይወት እንድንካፈል (በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ) በር ተከፈተልን። መዳን ሕይወት ነው። ሕይወትንም ማግኘት መዳን ነው። መዳን እግዚአብሔርን ማወቅ ነው፡፡ ይህም የዘላለም ሕይወት ነው። ለምን ይሆን ወደ መንግሥቱ ገብተን፤ ከእልፍኙ ውስጥ አብረን ታድመን ከስሉሱ ንጉስ ገበታ የምንጋራው? የማይጠገበውን የልጁን ክብር እናይ ዘንድ ነው። ይህም ክብር ወልድ በአብ መወደዱ ነው። ይህ መወደድ ለወልድ ክብሩ ነው (አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ)። ከዚህ ገበታ የሚፈረፈርውን የፍቅር ፍርፋሪ ብንለቅም አቤት እንዴት ታላቅ ክብር ይሆን!? ነገር ግን አብ ያፈሰሰልንን ፍቅር ተመልከቱ (1ዮሐ 3:1-5)! ልጆች አደረገን። ይህም ልጁ በሚወደድበት ፍቅር ተወደድን! ይህንን ፍቅር ተመልካቾች ብቻ ሳንሆን ነገር ግን ከዚህም ፍቅር ተካፋዮች እንድንሆን አበቃን! (እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ) ፍቅር እንደዚህ ነው! እኛ እንደወደድ ሳይሆን አብ እንደወደደንና  ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከልን ነው። ለምን ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት ይናፍቀናል? አንዳንዶች እንደሚሉት ወርቅ ስላለ ነው? እረፍት ስላለ ነው? ወይስ ለመዘመር ነው? የመጠቀ ዕይታ አለን፤ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ብሎናል፡-

  • የሰጠኸኝ ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።

ማራናታ እንበል! ወደ መዳናችን ለመግባት እንዘጋጅ። ስንሔድ የልጁን ክብር እናያለንና! መዳን ማለት ስሉሱን አምላክ በማወቅ ወደ ሚገኝ ፍጹም አንድነት መድረስ ነው። ይህንን ዳርቻ በልጅነት ይገልጸዋል። ልጆች ሆነን እንከብራለን። ሆኖም ግን ያ ክብር አሁን በውስጣችን እንዲኖር ከሰጠን በመንፈሱና በሐዋርያቱ አማካይነት ትቶልን በሔደው ቃሎቹ መቅመስ ጀምረናል።

የሚቀጥለው ርዕስ፡ ሦስት ገጽታ ያለው መዳናችን

 



ሦስት ገጽታ ያለው መዳናችን


ከላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድነት ሁለት እይታዎችን ገንዘቡ እንዳደረገ በፈረስ ግልቢያ ይመስል ፈጠን ፈጠን ብለን አይተናል። እነዚህም፤ ከእኛ ዕይታ አንጻር፤ መዳን እንደ ሁለት ጫፎች መስለነው ‘ከየትና ወዴት’ ብለናቸዋል። በጉዞ ላይ እንዳለ የእሥራኤል ሕዝብ፤ ለቀውት የመጡት ግብጽ ከኋላቸው፤ ከፊታቸው ደግሞ ሊገቡባት ያለችው ማርና ወተት የምታፈሰው የተስፋይቱ ምድር እንደነበረች፤ እኛም መዳናችን ከኋላ የተረፍንበት፤ ደግሞም ከፊት የምንወርሰው ሐብታችን ነው። ይህም መዳናችን አሉታዊና አዎንታዊ ገጽታ አለው ማለት ነው። አሉታዊ ያልነው መዳን መትረፍን ያመለክታልና ነው፤ ለሐጥያታችን ቅን ፍርድ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቁጣ የተረፍን ሕዝቦች ነንና (ትሩፋን)። እግዚአብሔር አምላካችን እዚህ ጋር ቢተወን ኖሮ ጻድቅ፤ መልካምነቱም ወደር የለሽ በሆን ነበር። ምክኒያቱም ዝም ቢለን ኖሮ እንደ ሶዶምና እንደ ጎሞራ የምንሆነውን እኛን በጸጋው አንድያ ልጁን በመላክ አተረፈን። ግን የአምላካችንና የአዳኛችን ታላቅ ምህረት ሲገለጥ አትርፎ ቢተወን ኖሮ የሚበቃንን እኛን ‘ልጆቹ እንሆን ዘንድ አስቦ ወለደን። ይህንን ነው ‘ወዴት በሚለው ያካተትነው። ይህንን ታላቅ እውነት ቀለል አድርጎ ለማስተዋወቅ ያህል ብቻ እንጂ መዳን ሌላ ሦስተኛ ገጽታም አለው።

መዳን ሁሉን የሚዳሥ ሠፊ ፕሮጄክት ነው


መጽሀፍ ቅዱስ ስለመዳናችን ሲናገር አንድቀን በሕይወታችን የተጠናቀቀ ፕሮጀክት እንደሆን አያቀርበውም። ለምሳሌ ያህል አማኞች ብዙውን ጊዜ እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። በተለይ ደግሞ ይህንን ስህተት መስራት የማይገባን አገልጋዮችን ጨምሮ “አሁን ስለሚያደርግልኝ ከማመሰገነው ይልቅ፤ ከሁሉ በላይ ስለመዳኔ አመሰግነዋለሁ” ስንል እንደመጣለን! በግርድፉ ስታዩት እውነት ይመስላል “የቀን ውሎ ሥራ…የደሞዝ ጭማሬ…ልጆች…ትዳር…ሐዘኔ..ደስታዬ…መከራዬ..ስኬቴ.. ከመዳኔ ጋር ምን አገኛነው?” ስለዚህ ይህ አባብል “ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ስለመዳኔ ተመስገን” ባይ ይመስላል። በርግጥ ይህ አባባል ሊበረታታ የሚገባና እውነት ነው። እውነትነቱ ግን በከፊል ብቻ ነው። በተጨማሪ ግን እንደምታው ያልታሰበ ጎጂ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ መዘዝ አለው። ይህ አነጋገር በመጀመሪያ መዳን ያኔ ያመንን ቀን ብቻ የሆነ ክዋኔ እደሆን የአማኙን መረዳት ያሳያል።  ሁለተኛ አሁን በአማኙ የሚሆነው ከፍታና ዝቅታ ከመዳኑ ጋር እንብዛ ግኙነት እንዳለውም አያሳይም። አማኙ ከእግዚአብሔር የሚቀበለው ደስታ ይሁን መከራ ከመዳኑ ጋር ምንም ግንኙነት አለው? የአሁኑ ገጠመኝ፤ የሥራ በር መከፈት…ወዘተ…ከመዳናችን ጋር ግንኙነት የለውም? ስለዚህ ይህ አነጋገር ጠለቅ ብለን ስናየው የቅርቡን ብቻ የሚያይ ይመስላል። ሦስተኛ፤ በአንድ ቀን መዳናችንና በአሁን የለውጥ ሒደታችን መካከል ረጅም ገደል በአማኙ ሐሳብ ውስጥ እንዳለም ይጦቁማል። ከዚህ ቀጥሎ እንደምንመለከተው ይህ አነጋገር መዳናችን በጣም ተራ በሚመስሉ ነገሮች ውስጥ ዕለት ዕለት እየሰራ መሆኑን አያስተውልም። እዚህ ጋር ይህችን ነገር-ቀመስ አነጋገሬን ልተውና ሁልጊዜም እንደማደርገው ወደ ቅዱስ ቃል ትንታኔ ውስጥ እንግባ። ከዚያ ወደዚህ ወደ ጀመርነው ሐሳብ እነመለስና እንዳኛለን።

ድነናል፤ እንድናለን ደግሞ እየዳንን ነው!

ከዚህ ቀጥሎ እባካችሁ “መዳን” የሚለውን ቃል አጠቃቀም አንባቢዬ እንዲያስተውሉ እመክራለሁ፦

  • ድነናል (ኤፌ 2፡ 8-10)፦ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤  ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።  እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”

ይህ ክፍል የሚያስገነዝበን መዳናችን አንድቀን የተከናወነ ነው። ሃላፊ ግስ ነው። ያድናችኋል ወይም እያዳናችሁ አይልም ሆኖም ግን አድኗችኋል። (ነገር ግን አንባቢው ቀጥሎ ያለውን ያንብብ። ይህ አንድ ቀን የተከናወነው መዳን በአዲስ ፍጥረት በመምሰል- መመላለስ በሚለው ቃል ሒደታዊ እንደሆነም ይጦቁመናል)

  • እንድናለን (ሮሜ  5:8–10.)፦ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።  ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን  ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን  

የሚገርመው እዚህ ጋር ሐዋርያው ስለ መታረቃችን ሲጽፍ እንታረቃለን አይልም። ክርስቶስ የተሰቀለ ዕለት በጥቅልና ያመንን ዕለት በግል ታርቀናል። ሰላምን ተቀብለናል። ወደ ቆምንበት ጸጋ መቅረብ ችለናል። ሆኖም ግን ሐዋርያው መዳናችን ገና ያልተጠናቀቀ ፕሮጄክት እንደሆን ሲጦቁመን ሁለት ጊዜ ደጋግሞ “ከቁጣው እንድናለንበሕይወቱ እንድናለን” ይለናል። ። ስለዚህ አሁን ብንታረቅም፤ አሁን ብንድንም ነገርን ገና በሙላት እንድናለን። (ተጨማሪ፡ 1ተሰ 5:6-8፤ 1ጴጥ 1:3-5) በተለይ ጴጥሮስ መዳናችንን “በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ” በማለት መዳናችን ወደ ፊት የሚከናወን ጭምር እንደሆን ያስረዳናል።

  • እየዳንን ነው (1ቆሮ 1:18)፡የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን (በቁሙ ብተሮጉመው ‘ግን እየዳንን ላለን ለእኛ’τοῖς δὲ σῳζομένοις ἡμῖν δύναμις θεοῦ ἐστιν) ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና
    • እዚህ ጋር ሐዋርያው ለዳኑት ግን የእግዚአብሔር ሃይል ነው ቢል በርግጥ እውነት ነበር። ነገር ግን ለማያምኑ (አሁን የመስቀሉ ቃል) ሞኝነት እንደሆነ አሁን ደግሞ እየዳኑ ላሉት ግን ሐይል ነው። ንፅፅሩ አሁን በማያምኑና አሁን በሚያምኑ ሰዎች መካከል ነው። እነዚህ የሚያምኑትን ሰዎች ጳውሎስ ‘ለሚድኑት’ ይላቸዋል። እዚህ ጋር በተጨማሪ ልናስተውል የሚገባው ነገር የመዳናችንም ሂደት ያ ያዳነን የመስቀሉ ቃል እንደሆነም ጭምር ነው። ያዳነን የወንጌል ቃል፤ አሁን የሚያድነን ደግሞም አንድ ቀን የሚያድነን ቃል ነው። ይህንን በ ዚሁ መጽሀፍ መጨረሻ ላይ በ 1ቆሮ 15፡1 ላይ (ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን (σῴζεσθε -እየዳናችሁበት ያለውን) ወንጌል አሳስባችኋለሁ)። ያመንን ዕለት የዳነው በወንጌል እንደሆነ ሁሉ፤ ዛሬንም ዕለት ዕለት በመዳናችን የምናድገው በወንጌል ሲሆን አንድ ቀን ደግሞ በፊት ታላቅ መዳናችን ውስጥ የሚያስገባን ይሀው የወንጌል ቃል ነው። የመድዳን ፕሮጀችት አንድ ወጥ ነው። ሒደቱም ሆነ ፍጻሜው በወንጌል የሚካሔድ ነው

ከብዙ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል እንደ ናሙና አድርጌ ከላይ የጠቀስኳቸው ጥቅሶች እንደሚያመልከቱን መዳን የሚለውን ቃል በሦስት ግዜያቶች (ግሦች) ያቀርበዋል። ከዚህ የተነሳ እነዚህ ሶስቱም እውነቶች ናቸው “በክርስቶስ ያመንን ቀን ድነናል፤ አሁን እለት እለት እየዳንን ነው፤ አንድ ቀን በሙላት እንድናለን”  በእነዚህ ሶስት ገጽታዎች መካከል አበይት የሆኑ ቃሎችና ይህ የመዳን ሒደት ቀጣይነት እንዲኖረው ያደረጉት የወንጌሉ ቃልና መንፈስ ቅዱስ ናቸው። የወንጌል ቃል አድኖናል ደግሞ እያዳነን ነው። ባመንን ቀን በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል ደግሞ አሁን እለት እለት መንፈስ ከሆነ ጌታ የልጁን መልክ እንድንመስል አሁን ከክብር ወደ ክብር ይለውጠናል። አሁን መንፈሱ የክርስቶስን ሙሽራ  እያዘጋጃት ነው፤ ሆኖም ግን አንድ ቀን ክርስቶስ ሲመለስ ይህ መዳን ይፈጸማል።

እዚህ ጋር ትልቅ ማስጠንቀቂያ በፊታችን አለ! ይህም ወንጌልን ገንዘቡ ያላደረገ ለውጥ የመዳን ለውጥ አለመሆኑን ነው፤፡ አንዳንድ ጊዜ ቅዱሳንና መሪዎች እንዲህ ስንል እንደመጣለን “መዳናችን ጥሩ ነው…አሁን ግን የምንናገረው ስለመለወጥ ነው…” ይህ አባባል መዳንና መለወጥ ሁለት የተለያዩ ፕሮጀክቶች አድርጓቸዋል። ለማለት የተፈለገው ነገር ምድር ነው፤ እውነት ነው ብዙኋኑ ወንጌልን ሰምቷል። እሁድ እሁድ የሚታደመው ህዝብ ወንጌልን ሰምቷል፤ ግን መለወጥ የሚባለው የሕልም እንጀራ ሆኖብናል። ምን ብናደርግ ነው ሕዝባችን የለውጥ ሕይወት የሚለማመደው?” ስለዚህ ለለውጥ ሕይወት 10 መርሆች…የተዋጣ የቤተሰብነት መርሆች…የገንዘብ አያያዝና ብልጽግና መንገዶች፤ የሓይል መንገዶች፤ አራት የፍቅር መንገዶች…የጸሎት ህይወት መርህ…የቅድስና ህይወት መርህ…ወዘተ…እነዚህ ሁሉ መልካም ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ከወንጌል የተነሳ የተደረጉ ለውጥ ካልሆኑ፤ ትልቅ የቆላስያስ ቤተክርስቲያንን መሰል-ስህተት ፈጽመናል። ወንጌል ሥር ሲሰድ የተገኘ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር ክርስቲያናዊ ለውጥ አይደለም። (ስለዚህ ጉዳይ በወንጌል ማዕከላዊነት በጻፍሁት መጣጥፎች ላይ በሰፊው ዘርዝሬአለሁ። ለምሳሌ፡ ወንጌል በመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ሕይወት፡ የወንጌልን ንጽሕናና ቀዳሚነት አጥብቆ መያዝ) የሕይወት ለውጥ ያለው የመለኮት ሁሉ ሙላት በእርሱ ዘንድ  ይኖር ዘንድ በወደደው በልጁ ውስጥ ብቻ ነው። ይህንን አባባል ሐዋርያው “የመለኮት ሁሉ ሙላት…ወይም እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን…በሚሉ ቃላት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያዘጋጀው ሙላት በልጁ ውስጥ ብቻ መኖሩንና ያለ ልጁ መሰበክና መታወቅ እነዚህ የአማኙ ገንዘብ ሊሆኑ እንደማይችሉ ያሳያል- ኤፌ 3፡14-21። ለዚህማ ብዙ ጠቃሚ ይህንን ዓለም የማይሻገሩ ምክሮችንና በሰውን ሕይወት ላይ ተጸዕኖ የሚያመጡ ነገሮችማ አለምም እኮ አላት። ነገር ግን የአብ አላማ በውድ ልጁ፤ ልጁን እንድንመስል ነው። ይህ ነው እውነተኛ ለውጥ፦ ክርስቶስን መምሰል። ይህ ደግሞ የወንጌል ፍሬ ነው። ወንጌልን አማኙ ሲረዳና በሕይወቱ ሥር ሲሰድ የሚገለጥ ፍሬ ነው። ከዚህ የተነሳ እኛ ለውጥ የምንለው ሁሉ የወንጌል ፍሬዎች እንደሆን ለናሙና ያህል እነመልከት-፡

  • እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥  ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ”  (ኤፌ. 5:1–2) ይህ ማለት በወንጌል የተገለጠው የክርስቶስ ተልዕኮ ለመዳናችንም ደግሞም በመዳናችን ከሕይወቱ ተካፋዮች እንድንሆን ምሳሌንም ሊተውልን ጭምር ነው። ይህንን ምሳሌ መከተል ልክ ልጅ አባቱን እንደሚመስል መለወጥ ነው። ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ ክርስቶስን መምሰል ውጤቱ ምን ይመስላል?
    • ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ (ቁ.3)
    • የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ፥ (4)
    • የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥9-11
    • እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ
    • በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።
    • ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤
    • ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።  ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።
    • ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።
    • ባሪያዎች ሆይ፥ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤  የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ።
    • እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፥ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንዳያደላ ታውቃላችሁና።
    • በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።

ወንጌል በአማኙ ሕይወት ሥር ሲሰድ ከላይ እንደተመከትነው የሚዳሥሠው የሰውን ሁለንተና ነው። ከነዚህ መካከል (ከኤፌ 5:1-6፡12) ሥነ-ምግባራዊ ለውጥን ገንዘቡ ያደረገ ነው፤ በጥበብ መመላለስን፤ በመዝሙርና በቅኔ ማወደስን ገንዘቡ ያደረገ ነው፤ የባልና የሚስት፤ የ ወላጆችና የልጆችን፤ የአሠሪና የሰራተኞችን ግንኙነት ይዳስሳል። የምለው ይህንን ነው፤ እነዚህ ለውጦች ግን “ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ” የሚለው የወንጌል እውነት ይከተላሉ እንጂ አይቀድሙም። አማኙ የመረዳት ብልጽግና በመንፈስ ቅዱስ ሲያገኝ የሚሆኑ ነገሮች ናቸው። (በተጨማሪ እነዚህን ለናሙና ያንብቡ ፊል 2፡ 2-8፤ ሮሜ 15፡ 2-7) ስለዚህ የምንም ለውጥ ሒደት ብንናገር በመጀመሪያ የወንጌል እውነት ሥር ከተመሰረተ በኋላ መሆን አለበት። በርግጥ ለውጥ ማለት ክርስቶስ ስለ እኛ የሆነውን መምሰል ነው (there is a mirroring of relationship) ካልሆነ አትንካ አትቅመስ የሚል ከንቱ የሰው ሥርዓቶች ብቻ ናቸው፡፤ እነዚህም በተግባር ሲደረጉ የሚጠፉና ለሥጋ ልቅነት አንዳች ፋይዳ የሌላቸው መርሆች ናቸው። ይህ በተለይ ለእኛ ለሰባኪዎች ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው። የለውጥ ስብከት በፊት መቅደም ያለበት የወንጌል እውነት ነው። ኢየሱስ ማነው? ተልዕኮውስ ማንድር ነው? የስውን ልጅ ማን ይሊታል? ከዚህ አንጻር ስንመለከት የለውጥ ሕይወት የወንጌል እንደምታ ነው። ወንጌል የሐይል ቃል እንጂ ባድ ንግግር አይደለም፡፤ ሐይል ከሆነ ዘንዳ በአማኙ ውስጥ ሰርጾ መስራት የሚችል ጉልበት ነው።

 የወንጌሉ እውነት

(The description of the Gospel)

የወንጌል እንደምታ/ትዕዛዝ

( the Implication/ Imperative of the Gospel)

 ገላትያ ምዕራፍ 1 እስከ  4 ወንድሞች ሆይ ፣ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ሰው ሰራሽ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። (1፥11)   ገላትያ ምዕራፍ 5  እና 6 ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ ፤ ዳግመኛ በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። 
 ኤፌሶን ምዕራፍ 1 እስከ 3 በሰማያዊ ስፍራ፣ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤  ኤፌሶን ምዕራፍ4 እስከ6 1 እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣  ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋሁ።
 ቆላስይስ ምዕራፍ 1 እስከ 2 እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ እኛም እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ማቅረብ እንችል ዘንድ፣ ሰውን ሁሉ በጥበብ ሁሉ እየመከርንና እያስተማርን እርሱን እንሰብካለን ፤  እኔም በብርታት በውስጤ በሚሰራው በእርሱ ኃይል ሁሉ እታገላለሁ፤ ለዚህ ዐላማ እጥራለሁ።  ቆላስይስ ምዕራፍ 3 እስከ 4 እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ፣
 1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 1 እስከ 2የመስቀሉ ኃይል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድነው ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው ፤   1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3 እና ከዚአ በህዋላ ያሉት ፣ጳውሎስ የቆሮንጦስ ሰዎች የጻፉለትን ጥያቄዎችና ጉዳዮች ሁሉ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች በአቀረበው ወንጌል መሠረት መመለስና መፍታት ይጀምራል  
 ሮሜ 1፥16 -11በሮም ለምትኖሩ ፣ ለእናንተም ወንጌልን ለመስበክ የምጓጓው ለዚህ ነው። በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኃይልነው፤ በመጀመሪያ ለአይሁድ ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።  ሮሜ 12 -16እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ ፤ ይሕም እንደባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኮአችሁ ነው። 

 

በልማድ መዳን የሚለውን ቃል ስንጠቀም በጠባቡና በመጀመሪያው ገጽታ ነው። ይህም ባመንን ዕለት አንድ ቀን የተከናወነ ነው። ሆኖም ግን ሊሰመርበት የሚገባው ይህ ባመንን እለት የሆነው የመዳን ሙሉ ገጽታ አይደለም። እውነት ነው፤ የማይደገሙ አንድ ጊዜ የሆነ በመዳን ሥር የሚካተቱ ክንዋኔዎች ተፈጽመዋል። ሆኖም ግን እነዚህ መዳን የሚለውን እውነታ ሙሉ በሙሉ መግለጫዎች አይደሉም። ባመንን እለት ምን ሆነ? እግዚአብሔር ይመስገን አዳነን! መዳናችን ግን በዙ ገጽታ ባላቸውና ብዙ እውነታዎችን በሚያንጸባርቁ ዘይቤያዊ አነጋገሮች ተገልጦአል። ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹ ይህንን ይመስላሉ፦ መጽደቅ፤ ጥሪ፤ ቅድስና፤ ዳግም ልደት፤ ልጅነት፤ ዕርቅ፤ ትድግና፤ መዋጀት፤ ቤዛነት፤ ሥርየት፤ ሰላም፤ መግባት፤ መክበር ወዘተ… እነዚህ ሁሉና እነዚህን የመሳሰሉ የአንዱ መዳን ለሚለው እውነታ ገጽታዎች እንጂ ምትኮች አይደሉም። ሐዋርያው ጳውሎስ ለምሳሌ እነዚህ የአንዱ መዳን ገጽታዎች እንደሆኑ ሲያሳየን ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤  አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው በተጨማሪ ያህል ከእነዚህ የአንዱ መዳን ገጽታዎች ከሆኑት ብዙ ዘይቤያዊ አነጋገሮች መካከል እንደ ናሙና አድርጌ “የጽድቅን ብያኔ ስለመቀበል” (justification) እንመልከት፡-

  • የጽድቅን ብያኔ ተቀበልን (Justification)፡- በእኛ ላይ የነበረው ክስ፤ ኩነኔና ፍርድ ተሠረዘ ማለታችን ነው። በሕያው እግዚአብሔር ፊት ወንጀለኛ የሚል ሥያሜ ተነሳልን። የሰውን ፊት አይቶ በማያዳላው፤ በጻድቅ ፈራጅ፤ በዓለሙ ሁሉ አምላክና ዳኛ ፍርድ ቤት ውስጥ ጉዳያችን በንጉስ ማህተብ ተዘጋ። ከእንግዲህ ወዲህ ይህ የንጉሰ ነገስት ፍርድ ቤት በልጁ ደም ስርየት ምክኒያት ወንጀልህ እንዳልነበረ ተሰርዟል። በአንተ(ቺ)(እርሶ) ላይ ያለው ሰነድ ስለ በደል የሚናገረው ጉዳይ የለም። (criminal record in this country can be cleared if proven innocence of the crime)። ይህ ባመንን እለት እግዚብሔር አብ በእኛ ፈንታ ከፈሰሰው ከክርስቶስ ደም የተነሳ የተቀበልነው ብያኔ ነው። (ከሐጥያታችን የተነሳ በቁጣው ፍርድ ምክኒያት የእኛ ደም መፍሰስ ቅን ፍርድ ሆኖ ሳለ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሳ የእርሱ ንጹህ ደም ፈስሶ እኛ በነጻ ተለቀቅን) ይህ የመዳናችን አንድ ገጽታ ነው። ለምሳሌ
    • እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን  በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤  2 በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።
    • እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው (የጽድቅ ብያኔ ነው) ልዩነት የለምና፤  ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤  በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ(የጽድቅ ብያኔ ይቀበላሉ)  እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ Ro 3:22–25.
    • ተጨማሪ፦ Rom. 5:17; Rom 3:21; 9:30; 10:3–10; 2 Cor. 5:21; Phil. 3:9

ስለዚህ መዳን ማለት ሁሉን የሚጠቀልል፤ እግዚአብሔር በልጁ አምሳል ዳግም ለፈጠራቸውና ለጥቅል ፍጥረቱ የተዘጋጀው ታላቅ ፕሮጀችት ነው ማለት ነው። ሆኖም ግን ምንም እንኳ መዳናችን አሁን እየሰራና ወደ ፊት የሚገልጥ ቢሆንም አንዳንድ የመዳን በረከቶች ግን ዳግም ላይደገሙ የተከናወኑ ናቸው። ለምሳሌ ያህል ሲያድነን ከጨለማ ወደ ብርሃን፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል። በዚህ ገጽታው ከሆነ መዳናችን እለት እለት እየሆነ አይደለም። ጌታን በየሳምንቱ አንቀበልም። አንድ ቀን አምነን የጌታ ሆነናል። ይህንን ነው በመግቢያዬ ላይ የገለጥኩት። ብዙ ጊዜ አማኞች መዳን የሚለውን በዚህ ብቻ ወስነው በጠባቡ ይመለከቱታል። ሆኖም ግን መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን በሥራ ላይ ነው። ሁሉ ነገር ተያይዞ (ሁሉ ነገር!) የሚሰራው ለአንድ ግብ ነው። የልጁን መልክ እንድንመስል እየተሰራን ነው። ይህም ሒደት መጽሀፍ ቅዱሳችን መዳን በሚለው ሰፊ ፕሮጀክት ላይ ያጠቃልለዋል እንጂ ሌላ ተጨማሪ ተልዕኮ አይደለም። ይህ ሒደት (process of sanctification) ከመጽደቃችንና ከመታረቃችን የቀጠለ እንጂ ሌላ አዲስ ሥራ አይደለም። ግባችንም በሙላት ልጆች መሆን ነው፤ ይህንን ዓላማ ክብር ይለዋል። ወደ ክብሩ ተጠርተናል፡ ልክ ለወልድ በአባቱ መወደዱ ክብሩ እንደሆን ክብራችንም ልጆች መሆን ነው።

 

ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ


በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤  በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን። ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤  እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል። Ephesians 1:3–14

ሐዋርያው ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ የተጠቀመበትን ቋንቋ አንባቢ የሆናችሁ ይህንን ማስተዋል ትችላላችሁ። በምዕራፍ አንድ  ከቁጥር 3-14 ሲጽፍ ትንፋሽ አልወሰደም። በመሃከል ነጠላ ሰረዝ፤ ሁለት ነጥብ፤ አራት ነጥብ አልተጠቀመም። ይህ ማለት ከቁጥር ሦስት ጀምሮ እስከ ቁጥር አሥራ አራት ድረስ አንድ ረጅም ዓረፍተ-ነገር ነው። ሐዋርያው እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል የገለጠልንን መዳን ታላቅ መሆኑን በማስገንዘብ ልባዊ ምሥጋናውን ሲገልጥ እረፍት ሊያደርግ አልወደደም።

  • የተባረክነው በሚወደው ልጁ በክርስቶስ ነው፦ በዚህች አጭር አረፍተ ነገር ውስጥ ከ 11 ጊዜ በላይ በመደጋገም ሁሉን ነገር የተቀበልነው “በክርስቶስ/ በእርሱ/በሚወደው” መሆኑን ይነግረናል። ይህም መዳናችን ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆናችን ነው። እርሱ ሐጥያታችንን በመሸከም እኛን መሰለ፤ እኛ ደግሞ የሐጥያትን ሥርየት ካስገኘልን በኋላ እርሱን እንመስል ዘንድ።
  • የባረከን የክርስቶስ አባት ነው፦ እዚህ ጋር አሁን አባት ብለን የምንጠራው አምላካችን በመጀመሪያ ደረጃ የወልድ አባት መሆኑን ያሳየናል። ለዚህ ነው ስለ ክርስቶስ ሲናገር “በሚወደው ልጁ” ሲል ስለ እኛ ግን “ለእርሱ ልጆች እንሆን ዘንድ አስቀድሞ ወሰነን” የሚለን። ክርስቶስ የዘላለም ልጅ ሲሆን እኛ ግን ልጆች እንሆን ዘንድ የተቀበለን ልጆች ነን (adopted sons)። ይህ የሐዋርያው የባረከንን የሚባርክበት ታላቅ ምክኒያት ነው። ከመዝሙረኛው ዳዊት አንሥቶ እስከ ክርስቶስ ዘመን የነበሩ አይሁዳውያን እንደጸሎት ቀመር አድርገው የሚጠቀሙበት ሐረግ አለ። ለምሳሌ ዳዊት የባረከውን አምላክ እየባረከ ሲዘምር የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይባረክ…ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአሔር ይባረክመዝ. 28፡ 6 ፤ 31፡ 21፤ 41፡13፤ 119፡12 በተጨማሪ “ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን ባረከ፤ ዳዊትም አለ። አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ተባረክ” 1ዜና 29:10። ክርስቶስ በተገለጠበትም ዘመን አይሁድ፤ ከዚህ ተከትለው በዘወትር ጸሎታቸው መጀመሪያ “ባሩክ አታህ አዶናይ ኤሎሔኑ…ብሩክ ነህ አንተ ጌታ አምላካችን….” በማለት ባርኮታቸውን መዘርዘር ይጀምራሉ። ጳውሎስም ክርስቶስን በደማስቆ መንገድ ላይ ከመገናኘቱ በፊት ብዙ ጊዜ እንዲህ ብሎ ይጸልይ እንደነበር መገመት አዳጋች አይደለም። እዚህ ጋር ግን ሐዋርያው ጳውሎስ በልማዱ ላይ ሠበር ቃል ይከታል። ይህም ያ የአባቱ የአብርሃም አምላክ አዳናይ-ኤሎሔኑ (ጌታ-አምላክ) አሁን የሚታወቀውና በጸሎት የሚጠራው “አምላክ የጌታችን የክርስቶስ ኢየሱስ አባት ተብሎ ነው!” እዚህ ጋር ብዙ መሠረታዊና ጥልቅ እውነታዎች ተንጸባርቀዋል። በመጀመሪያ ዳዊትና አይሁድ ‘ጌታ’ ብለው ያህዌህን እንደጠሩት አሁን ይህንኑ ስም (ጌታ) ለኢየሱስ በማጎናጸፍ ክርስቶስ ከአባቱ ጋር በማዕረግ አንድ መሆኑን ያሳየናል (ከዘዳ 6:4 ጋር ያጣቅሱ)። ሁለተኛ በክርስቶስና በአብ መካከል ያለውን ግኑኝነት ያጎላል። ክርስቶስ የአብ ልጅ ነው። መዳን ማለት ደግሞ በሚወደው ልጅ አማካይነት ልጅ መሆን ነው።
  • የተባረክነው በመንፈሳዊ በረከቶች ነው፡- እዚህ ጋር ሐዋርያው መንፈሳዊ ሲል ከቁሳዊ ነገር ጋር እያቃረነ እንዳለሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህም የመዳን በረከት ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊ አድርጎ ማቅረብ ማለት ነው። ሆኖም ግን ይህ አስተሳሰብ የግሪኮች መንትያ አስተሳሰብ (dualism) እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብ አይደለም። ሐዋርያው ግን መንፈሳዊ ሲል፤ የበረከታችንን ምንጭ ለማመልከት ነው። ይህም ያገኘናቸው በረከቶች ከአሮጌው ሥርዓት የፈነጠቁ ሳይሆኑ ሁሉን ሊጠቀልል በወደደበት በልጁና የርስታችን መያዣ አድርጎ በሰጠን በመንፈሱ የታቀፈ በረከት እንደሆን ለማመልከት ነው። (እዚህ ጋር ወደ ረቀቀ የቃል አጠቃቀም ትንታኔ ውስጥ መግባት ለምትፈልጉ መንፈሳዊ ተብሎ የተተረጎመው ቃል ‘ፕኑሟቲካስ/πνευματικός ነው)
  • የተባረክነው በመንፈሳዊ ሥፍራ ነው፦ ሲል አሁንም እነዚህን በረከቶች የተቀበልንበትን ልዕልና ለማመልከት እንጂ እነዚህ በረከቶቹ በመንፈሳዊ ዓለም ብቻ የተወሰኑ እንደሆን ለማመልከት አይደለም። ይህ ሥፍራ ጌታችን ወደ አባቱ ዘንድ ሲመለስ ጌታና ክርስቶስ ሆኖ የተሾመት ሥፍራ ነው። ስለዚህ ይህ ቃል የክርስቶስን ሹመት፤ በርሱ በኩል ወደ ተመረቀው አዲስ ሥርዓትና መሲሐዊ ዘመን መፈንጠቅ ያመለክታል (Inaugurated Eschatology)። ክርስቶስ አንድ ቀን የምንሆነውን ሁሉ አሁን በአብ ቀኝ እኛን ወክሎ ይዞልናል። እኛም መንፈሱን ስለተቀበልን ከክርስቶስ ጋር አንድ እንድንሆን ተጠምቀናል ያም በረከት ከመንፈሱ የተነሳ በመጠን መካፈል ጀምረናል። ያህዌህ በዘመን ፍጻሜ ሊያደርግ የወደደው አሁን ተመርቋል፤ ምንም እንኳ ይጠናቀቅ ዘንድ ግን ዳግም-ምጽዓቱን ገና ቢጠብቅም። ስለዚህ ይህ እውነታ (በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ) መዳናችን አሁን እውን እንደሆን ነገር ግን ገና ወደ ፊት ደግሞ በሙላት እንደሚገለጥ ያሳየናል።
    • “በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።”
  • የተባረክነው በሥሉሱ አምላክ አሰራር ነው፡- ከላይ እንዳየነው በዚህ ወጥ ረጅም ዓረፍተ-ነገር ውስጥ አዝማች መሰል ሐረጎችን ሶስት ጊዜ በመደጋገም ሐዋርያው በመዳናችን ውስጥ የእያንዳንዱን የስላሴ አካል ሚናና ዓላማ ይነግረናል (ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ…ቁ 6፤ 11ና 14 ላይ)። መዳናችን በስሉስ አምላክ አካላት የተቀመረ፤ የተቀነባበረና የሥሉሱን አምላክ ክብር የሚያንጸባርቅ ነው። በስሉስ አካላት መዳፍ የተቀረጽን ነን። አንዱ አምላክ አብ በወልድና በመንፈሱ የተዳሰሰ ስጦታ ተሰጥቶናል። ስለዚህ ስጦታው አምላካችንን እንድናውቅ ያደርገናል።
    • አብ፦ ልጁን የሚመስሉ ንፁሃን ልጆች እንሆን ዘንድ እንደ በጎ አቀደ
      • ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።
      • በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። “በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ
  • ወልድ፡ በዘመን ፍጻሜ
    • የሓጥያትን ይቅርታ የሚያስገኝ ቤዛነት፡ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
    • በወልድ አማካይነት የሐሳቡ ሚስጢር ተገለጠ፦  ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። 9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
    • እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።
    • ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።
  • መንፈስ ቅዱስ፡ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥(እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ )
    • በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
    • እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ “ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል
  • የልጅነታችን ሦስት ገጻዎች፡
    • በዘላለም (አብ)፦ ልጆች እንሆን ዘንድ ወደደ (አላማውም ቅዱሳን (ለእግዚአብሔር የተለየ)ና ነውር አልባ (በብሉይ ለመስዋእት የሚቀርቡ እንሥሣትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል)፟
    • በዘመን መጨረሻ (ወልድ)፡ ልጆች የሚያደርግን ሥራ ስላከናወነ በደሙ የልጅነት በር ተከፈተ።
    • በወንጌል ቃል መስማት አማካይነት ባመንን ጊዜ (በመንፈስ ቅዱስ)፦ በመንፈስ ቅዱስ ማህተም በመታተትም ደግሞ ልጅነታችን እውን ሆነ። አባ አባት ብሎ የሚጮህ መንፈስን ተቀብለናል።

በአጭሩ የመዳናችን ግብ የእግዚአብሔርን ቤተሰቦች እንድንሆን ነው፤ ይህም ልጅነታችን ነው። ለመከለስ ያህል መዳናችን ሁለት ጫፎችና ሦስት ገጽታዎች እንዳሉት አይተናል። መዳናችን ከየትና ወዴት የሚሉ ጫፎች አሉት። ከዬት የሚለው ጥያቄ የሚያሳየን ባመንን ጊዜ አሮጌው ሰው ከነ ፍርዱ ተሽሮ አዲሱን ሰው መልበሳችንን (ይህም እግዚአብሔር አብ በወልድ ሥራ አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ ማሕተም አትሞን የሓጥያትን ይቅርታ መቀበላችን) ሲሆን ወዴት የሚለው ደግሞ በዚሁ በአንዱ መንፈስ አማካይነት ዳግም ክርስቶስ ሁሉን ሊጠቀልል በሚገለጥበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ እውን ወደ ሚሆነው ልጅነታችን ላይ ያነጣጥራል። ከዚህ የተንሳ መዳን ሦስት ገጽታ አለው። በአንድ ገጽታ ድነናል። በሌላ ገጽታ አሁን ዕለት ዕለት እየዳንን ነው። ደግሞ አንድ ቀን ልጁ ሲገልጥ በሙላት እንድናለን። ክብር ሁሉ ለሉሱ ጌታ ይሁን!

የሚቀጥለው ርዕስ፡ የመዳናችን ገጽታ በሁለት ዘመናት (ድነናል፤ ግን ገን ደግሞ እንድናለን – The already but not yet dimension)



በሁለት እውነታዎች ተወጥሮ የተቃኘ መዳናችን


መዳናችን አሁን ተገልጧል…መዳናችን ገና በሙላት ይገለጣል!

ከዚህ ቀደም ከወንጌላዊው ዮሐንስ ነገረ-ትረካ ወስደን፤ ወልድ ተልዕኮውን የሚፈጽምበት ሰዓት አይተናል፤ ይህም የመስቀሉ ሥራ ነው። ይህ ተልዕኮ ታላቅን መዳንን ገልጧል። በዚህ ተልዕኮ ውስጥ እውነተኛው አብና የተላከው ወልድ ተገለጠዋል። ይህንን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ነው። ይህንን ተመልክተናል። ሆኖም ግን ይህንን ታላቅ መዳን በሌላ ገጽታ ደግሞ ሦስቱ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፤ ማርቆስና ሉቃስ) በእግዚአብሔር መንግሥት ዙሪያ በተቃኘ ዕይታቸው ሲተርኩ የነብያትን ድምጽ ሊፈጽም በዳዊት ቤት ክርስቶስ ሆኖ፤ መንግሥትን ይዞ፤ በመገለጡ ላይ በማነጣጠር ፤መዳን የእግዚአብሔር መንግሥት አሰራር እንደሆን ያሳዩናል (ማር 1:15)። ልክ በዮሐንስ ወንጌል መስቀልና የዘላለም ሕይወት የማይለያዩ ገጽታዎች እንደሆኑ፤ ሦስቱም ወንጌላውያን መስቀልና ዙፋን እነደማይለያዩ ይነግሩናል። ስለዚህ መዳን የእግዚአብሔርን መንግሥት ባሕርይ የተጎናጸፈ እንደሆን እንመለከታለን።
ከዚህ የተነሳ የመዳናችን ሌላው ገጽታና ሊሰመርበት የሚገባ እውነታ፤ አሁን በእውነት ድነናል! መዳንን ተጎናጽፈናል፤ መዳን አሁን ገንዘባችን ሆኗል፤ ቃል ኪዳን ውስጥ ታስረናል፤ ሆኖም ግን መዳናችን ክርስቶስ በግርማው ከመላዕክቱ ጋር መንግስቱን ይዞ ዳግም እስኪገለጥ ድረስ ቀና ብለን አንጋጠን የምንጠብቀውም እውነታ ነው!” ስለዚህ ልክ የእግዚአብሔር መንግስት በመጀመሪያ መምጣቱና በዳግም ምጻአቱ መካከል በሁለት ዘመናት እነደተወጠረ እንዳየን (ክፍል 008-06 እስከ 008-08ን ያድምጡ) መዳናችንም የመንግሥቱ አሰራር በረከት ከመሆኑ የተነሳ በነዚህ ውጥረቶች ውስጥ አለን። ድነናል…ገና ደግሞ እንድናለን። የጌታ ነን…ደግሞ አንድ ቀን የጌታ እንሆናለን። አሁን አንድ ቀን የምንሆነውን ሆነናል…በሌላ እጅ ደግሞ ተዘርግተን ወደ ፊት አሁን ገንዘባችን የሆነውን በሙላት እንወርሳለን።
“በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ” 1 Pe 1:3–5.
“የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል” 1 Pe 1:8–9.
ሁለቱም አሁን በዘመን መጨረሻ (በመጀመሪያ መምጣቱና በዳግም ምጻአቱ መካከል) ላለን አማኞች እውነት ነው። መዳናችን ገና የሚገለጥ ነው…መዳናችን አሁን የምንቀበለው ነው። ይህ እወነታ የተመሰረተው ግን ከእግዚአብሔር መንግሥት አገላለጥ አንጻር ነው። ይህንን ነው ጌታ የመንግሥተ ሰማያት ሚስጢር ብሎ ያስተማረው። አሁን በዚህ በጨለማው ዓለም ውስጥ ሰርጾ ልጁን በመበላክ መንግሥቱ ተመርቃለች፤ ሆኖም ግን መንግሥቱ ሁሉን ልትጠቀልል ገና ትገለጣለች። ይህንን ለምሳሌ፡
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጦሙ ነበር። መጥተውም። የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጦሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት። 19 ኢየሱስም አላቸው። ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም። 20 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ወራትም ይጦማሉ። 21 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። 22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ (Mark 2:18–22)
 
ክርስቶስ በምድር ሳለ የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ በሐይል ተገልጣ ነበር። ከዚህ የተነሳ መሲሐዊ ዘመን ፈነጠቀ። ነብያት ይሆናል ያሉት መፈጸም ጀመረ ሆኖም ግን የፍርድን ሥራ አልገለጠም (here you have fulfillment without consummation)። የኢየሱስ ደ/መዛሙርት በአዲሱ መሲሃዊ ዘመን ውስጥ ናቸው። መንግሥቱ በዙሪያው ላሉ ሁሉ ሠፍኗል። መብላትና መጠጣት የመሲሃዊ ግብዣ ምሳሌ በመሆኑ ንጉሱ እያለ ጾም ተገቢ አይደለም። ሆኖም ግን አሮጌው የሙሴ ኪዳን አልፎ አዲስ ኪዳን ስለሚመረቅ፤ አሮጌው የሕግ ሥርዓት ስለሚሻርና አዲሱ የመንፈስ ሕግ ስለሚደነገግ፤ እንደ ድሮው ሥርዓት መመላለስ አይችሉም። አሁን ንጉሱ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር እያለ መጦም አያስፈልጋቸውም። ሆኖም  ግን አንድ ቀን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ወራትም ይጦማሉ ይህ ማለት ክርስቶስ፤ ሙሽራው ከመካከላቸው ሲወሰድ ከዚህ ቀደም ወዳልነበረ እውነታ ውስጥ ስለሚገቡ መጦም ይጀምራሉ። ይህ እውነታ ሙሽራው ክርስቶስ መጥቷል ደግሞም ለሁለተኛ ጊዜ ይመጣል የሚል ነው…ይህን እውነታ ነው በውጥረት መያዝ ያለብን ያልኩት። ይህ ጾም በዚህ ምድራዊ ድንኳን ከብዶብን ማራናታ የሚል ጾም ነው። አዳኛችን ተመለስ…መድኅናችን ተገለጥና መዳናችንን ፈጽም የሚል ጩሀት ነው። ይህንን ዘመን ነው የመጨረሻ ዘመን የሚለው። ይህ ልጁ የተገለጠበት ዘመን ነው። እግዚአብሔር በብዙ መንገድ በብዙ ጎዳና በነብያቱ የተናገረበት ዘመን ሳይሆን፤ ይህ አሁን በልጁ የተናገረበት የመጨረሻ ዘመን ነው። መንፈሱ የተላከበትና ከነገድ ከቋንቋ አሕዛብ እየተቀደሱ በእምነት ወደሆነ መታዛዝ የሚቀደሱበት ዘመን ነው። መዳናችን በተሰጠን መያዣ እናረጋግጣለን፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ይሄው መንፈስ ለቤዛ ቀን የታተምነበትም መንፈስ በሆኑ ፍጻሜ ገንዘቡ የሆንን ሕዝቦች ነን። አዲስ ኪዳን ይህንን እውነታ በብዙ ዓይነት ዘይቤያዊ አነጋገሮች ይገልጥልናል። አንድን ምሳሌ እስኪ እንመልከት

እጮኛ…ሙሽራ…ታዳሚ!

“በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና” (2 ቆሮ 11:2)

“ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” (ኤፌ 5:31–32)

 

በአይሁድ አስተሳሰብ እጮኝነት የዝግጅት ጊዜ እንጂ በአሁን ዘመን አስተሳስብ እንደሆነው ተጋቢዎቹ ለትዳር ምቹ እንደሆኑ እርስ በእርስ የሚተያዩበት መንገድ አልነበረም (ይህ ማለት ግን በዘመኑ አሰራር ላይ ተመርኩዞ መለኮታዊውን ሐሳብ ለማንጸባረቅ እንጂ ይህ እ/ር ለተጋቢዎች ያለውን ፈቃድ ማንጸባረቁ አይደለም) ከእጮኝነት ወደ ጋብቻ ያለው ወቅት ሙሽራው ቤት የሚሰራበት፤ እርሻውን የሚያርስበት፤ ከአባቱ የልጅነት ድርሻውን የሚረከብበት…በአጭር ቃል ሦስት ጉልቻ የሚመሰርትበት ወቅት ነበር። ስለዚህ ቤተክርስቲያንን የክርስቶስ እጮኛ አድርጎ በዘይቤያዊ አነጋገር ሲመስላት አሁን ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ብትሆንም ሆኖም ግን አንድቀን በሙላት የክርስቶስ የምትሆንበትም ቀን እንዳለ ማመልከቱ ነው። ልክ እጮይቱ በዚህ ወቅት ለሌላ ወንድ መታጨት የትዳር ኪዳንን በማጣረስ ምንዝርና እንደፈጸመች እንደሚቆጠር እንደነበር (ማርያም ፀንሳ ስትገኝ ዮሴፍ በስውር ሊተዋት መፈለጉ ከዚህ የተነሳ ነበር) አሁንም የክርስቶስ አካል የክርስቶስ ናት። ልቧ የሁለት ወዳጆች ሊሆን አይችልም። ሆኖም ግን ይህ የዝግጅት ወቅት አልፎ ሙሽራው ወደ ሙሽራይቱ የሚመለስበት ቀን አለ።
ከዚህ በኋላ ቀን ተወስኖ ድግስ ይጀምራል። በዚህ በምዕራቡ ዓለም ደጋሽ የሙሽራይቱ ቤተሰብ በመሆኑ ብዙውን ውሳኔ የሚያደርጉት (ሥፍራውን፤ የታዳሚውን ቁጥር..ወዘተ)ና የራት ድግሱን የሚጥሉትም እነርሱ ናቸው። በክርስቶስ ዘመን ግን ወንድ ሙሽራው ነበር ይህንን ሐላፊነት የሚወጣው (ግርምቢጥ ማለት ይህ ነው)። በተጨማሪም በኛ ዘመን “እነሆ ሙሽራይቱ…here comes the bride እስኪባል ድረስ የታዳሚው ልብና ዓይን የሚንጠለጠለው በሙሽራይቱ ወደ አዳራሹ መግባት ላይ ነው። በሠርጋችን ዕለት ላይ እኔ ሙሽራው ወደ አዳራሹ ስገባ ከጥቂት ጭብጨባና “ጎበዝ የኔ ልጅ” የሚሉኝ ይመስል ከአውራ ጣትና ከራስ ንቅነቃ በስተቀር ብዙ አልደመቀም ነበር። ነገር ግን ይህ ቅናቴ ብዙውም ሥፍራ አልነበረውም ምክኒያቱም የምወዳት ሙሽራ ለጥቂት ደቂቃ ዘገየችና ነው። በሩ አልተከፈተም። የእጇን አበባ አቀብሉኝ እያለች ያልተረዱላት አስተናጋጆቿዋ ሲይሯሯጡ ደቂቃ በደቂቃ ሲጨምር መዘግየቷ፤ ኋላ ብቅ ስትል ለእርሷ እልልታውን ለእኔም እፎይታውን አደመቀልን። አሁንም በክርስቶስ ዘመን የድግሱ ጭፈራና የታዳሚው ግፊያ ያለው በሙሽራው ቤት ነበር። በሌላ አነጋገር “here comes the groom” (እውነቶትን ነው ግርምቢጥ ማለት ይህ ነው)። ስለዚህ ሙሽራው ወደ ሙሽራይቱ ቤት በቀን ይመጣና የመጀመሪያውን መጠነኛ የምሣ ድግስ በሴቲቱ ቤት ይካሔዳል። ከዚያ በኋላ እንደ ሙሽራው ቤት መንገድ ርዝማኔ የምሣው ድግስ አጠር ይላል። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ምን እንደሚገጥም ስለማይታወቅ በሙሽራው ቤት ያሉት ሚዜዎችና ታዳሚ እንግዶች ቁጭ ብለው መጠባበቅ ምርጫ አልነበራቸውም። እንደ አሁኑ ዘመን የእጅ ስልክ በሌለበት ዘመን ቀጠሮ አክባሪነት ትግሥትን ይጠይቃል። በዚህ መንፈስ እስኪ ይህንን የክርስቶስን ምሳሌ አድምጡ፡
በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።  2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።  3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤  4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።  5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።  6 እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።  7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።  8 ሰነፎቹም ልባሞቹን። መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።  9 ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።  10 ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።  11 በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።  12 እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።  13 ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። Mt 25:1–13
የዚህ ምሳሌ ዓላማ ጌታችን የመንግሥቱን አገላለጥ ሚስጢር በምሳሌ ለማስተማር ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት ባሕርይ ይህንን ይመስላል….እንደ አንድ ሠርግ ድግስ። ሆኖም ግን የዚህ ምስሌ ዋና እምብርት “ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ” የሚለው ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት ትወሰዳለች (ይህም የክርስቶስ ሞት ነው )…ከዚህ የተነሳ ዳግም እስኪመለስ ድረስ የምትዘገይ ትመስላለች። መጠባበቅ የሞላባት ናት። ይህ ነው የምሳሌው ዋና እምብርት (ስለዚህ ጉዳይ ምሳሌዎችን፤ ወንጌላትን…እንዴት ላንብብ በሚለው ትምህርት ሥር እንነጋገራለን)። ሚዜዎቹ መተኛታቸው ስህተት አልነበረም። ሁለቱም ዓይነት ሚዜዎች፤ ልባሞችና ሰነፎች፤ ተኝተዋል። ሆኖም ግን ልባሞቹ ተዘጋጅተው ሲተኙ ሰነፎች ግን ሳይዘጋጁ ተኙ።ግን አንድ ቀን “ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ” ይሆናል።  ስለዚህ በዚህ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሱት መብራት፤ ዘይት፤ ማሰሮ፤ ቆነጃጅት፤ አሥር ሚዜዎች መሆናቸው….ልዩ ትጉም የላቸው። እነዚህ ለትረካው ቀጣይነት መረማመጃ ይሆኑ ዘንድ ና የትረካው ዋና መልእክት እንዲደርስ ከአይሁድ እለት ሕይወት ጋር የሚዛመዱ ማጀቢያዎች ናቸው። ለምሳሌ በዚህ ምሳሌ እንቅልፍ አልተተቸም። (በአንጻሩ ግን ለሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 13፡ ላይ አሁን የምንተኛበት የእንቅልፍ ጊዜ አይደለም ሲል ጌታ እስኪገለጥ ድረስ በዝግጅት መጠባበቅ እንዳለብን ይነግረናል። ምንም እንኳ የሁለቱም ዝይቤያዊ አነጋገሮች ዋና ነጥብ “በንቃት መጠበቅ” ቢሆንም ማቴዎስ የክርስቶስን ምሳሌ “ተዘጋጅቶ መጠበቅ” ላይ ሲያተኩር ሐዋርያው ግን ምሳሌውን “ከእንቅልፍ ነቅቶ መጠበቅ” ላይ ያተኩራል ማለቴ ነው)።
ስለዚህ በዚህ የሰርግ ምሳሌ መዳናችን በሁለት መንገዶች ተገልጾልናል። በአንድ ወገን አሁን የጌታ ነን። በሌላ ወገን ደግሞ ሙሽራውን በዝግጅት ገና እየተጠባበቅነው ነው። አንድ ቀን ግን ሁላችን ወደ በጉ ዕራት እንታደማለን። ይህንን ግብ የራዕይ መጽሐፍ “የበጉ እራት” ብሎ ይጠራዋል። በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ታላቁ የነገሥታት ንጉሥ ዳግም ሲመለስ ሁለት እራቶች እንዳሉ ያሳየናል። እነዚህም፡ የበጉ ዕራትና የታላቁ የእግዚአብሔር እራት ናቸው
“እርሱም። ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ። ደግሞም። ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ” Re 19:9
በበጉ ደም ለበጉ ክብር ይሆኑ ዝንድ ከነገድና ከቋንቋ የተዋጁት እነዚህ ወደ በጉ ሠርግ ገበታ ይታደማሉ። ይህም የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ህዝብ መዳን ምሳሌ ነው። አንድ ቀን ከጌታ ጋር እንሆናለን። ይህም በምድራዊ ቋንቋ ለመግለጽ ቢሞከር በድንግዝግዝ ታላቅ የሠርግን ቀን ይመስላል። ሆኖም ግን ደግሞ ሌላ ዕራት አለ።፡ይህ እራት ግን አሰቃቂና የሚያስፈራ እራት ነው።
“አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።  በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት። የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።  አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ። መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።” Re 19:15–18.
እዚህ ጋር “በብረት በትር ይገዛቸዋል” የሚለው ከመዝ 2:7-9 የተወሰደ ነው “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁ፤ ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ነገስታት ለግዛትህ እሰጥሃለሁ አንተም በብረት በትር ትገዛቸዋለህ በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ” ከዚህ ቀደም የዳዊትን ኪዳን በሰፊው ተነጋግረናል። ከዳዊት ጋር ያህዌህ የገባው ኪዳን በአብርሃም ተስፋ መሰረት ላይ ተመርኩዞ “በአንተ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ…” ሲሆን በዚህ ኪዳን ለአህዛብ በረከትና ለምድር ሁሉ የእግዚአብሔርን ፍርድ ይገልጣል። ለዚህ ነው በወንጌላት ላይ የእግዚአብሔር መንግሥት በእራት የተመሰለው። ወደ እራቱ የተጠሩት ማለት የዳኑት ሲሆኑ ጥሪውን ንቀው ውጪ የቀሩት ግን ጥርስ ወደ ማፏጨት ይሔዳሉ። ጌታችን ኢየሱስ በላተኛና የሐጥያተኞች ጓደኛ የተባለው በዚህ ምክንያት ነው። የአገር ስሜታዊነት የገዛ ልባቸውን ዓመጽ የሸፈነባቸው (በሥጋ ብቻ የአብርሃም ልጆች የሆኑ) አይሁዳውያን፤ ይህ ታላቅ አዳኝ መሲህ ሲመጣ፤ ሐጥያተኞችንን፤ ቀራጮችንና ሮማውያንን ይበቀልልናል ብለው ሲጠብቁ፤ እርሱ ግን ሐጥያተኞችን ወደ ገበታው ጠራ። አብሯቸው በላ። ተቀበላቸው። የመንግስቱ ተካፋዮች ሆኑ። የእስራኤል፡ጥሪም ሆነ የያህዌህን ጽድቅ ካለማወቅ የራሳቸውን ጽድቅ ሊመሰርቱ የተገበዙት ግን ውጪ ቀሩ። ወደ ታላቁ ንጉስ እራት አህዛብ ይመጣሉ “እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤  የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል (Mt 8:11–12) በስሞዖን ቤት ግብዣም ላይ ይህንን መመልከት ትችላላችሁ።
በተጨማሪ በዮሐንስ ራዕይ ሑለት እራት እንዳለ ሁሉ፤ ሁለት ሴቶችና ሁለት ከተሞች አሉ። አንዷ የበጉ ሙሽራ ስትሆን ሌላኛይቱ ደግሞ ታላቂቷ ጋለሞታ ነች።
  • ከዚህ በኋላ በሰማይ። ሃሌ ሉያ፤ በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ። Re 19:1–2.
  • እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውኃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሃሌ ሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።  የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።  ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።  እርሱም። ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ። ደግሞም። ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ። Re 19:6–9.
ሆኖም ግን ባለራዕዩ ዘይቤውን ይቀይጠዋል። ይህም ወደ በጉ ዕራት የተጠሩ ብጹዓን ናቸው…በማለት ይህ እራት በአንድ ወገን የክርስቶስና የቤተክርስቲያን (በጥቅሉ) ሠርግ ሲሆን፤ በነጠላ ደግሞ አማኞች በዚያው ሠርግ ላይ የተጠሩ ታዳሚዎችም እንደሆኑ ተመስሏል። ይህንን ነው ቅይጥ ዘይቤ ያልኩት። አንድ እውነታ ነገር ግን ድርብ ዘይቤ (ይህ አማኞች በነፍስ ወከፍ ይህ የሙሽርነት ዘይቤ አይመለከታቸውም ምክኒያቱም ጋብቻው በጥቅል በእ/ር ሕዝብና በክርስቶስ መካከል ሲሆን…ሆኖም ግን ደግሞ ይህ ዘይቤ የሚያመላክተው ጥልቅ አንድነት በረከት ተካፋዮች ናቸው) በተጨማሪ ልክ አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት ከአምላካቸው ጋር በከፊል አንድነት ይኖሩ እንደነበር፤ የእግዚአብሔርም ሕዝብ ከሰማይ በምትወርደው በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ሰማይ ከምድር ጋር ይጋባል። የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ይዘረጋል። የእ/ር ማደሪያ ከሰው ማደሪያ አይለይም። ፊት ለፊት እያየን፤ ክብሩ እንደ ጸሐይ እይበራልን የምንኖርበት እውን አለም ይህም የመዳናችን ሌላ አገላለጽ ነው። እነደዚሁ ሁለተኛ ከተማ ደግሞ አለች፤ ይህችም ታላቂቱ ባቢሎን ናት።
  • “በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም። ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።  ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ” ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።  2 በብርቱም ድምፅ። ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤  3 አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።  4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል። ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም
  • አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።  2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።  3 ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤  4 እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።  5 በዙፋንም የተቀመጠው። እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።  6 አለኝም። ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።  ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል Re 21:1–7
ስለዚህ በእግዚአብሔር ሕዝብ አንድ ቀን መዋጀትና በአሁኑ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ይህንን ታላቅ መዳን እየተጠባበቅን እንኖራለን። ይህ መጠባበቅ ግን የሕይወት ተሐድሶን ገንዘቡ ያደረገ እንጂ፤ እጅንና እግርን አጣጥፎ መቀመጥን አያሳየንም። ያንን እራት እያሰብን አሁን የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆንን የጌታን እራት እንቋደሳለን። እንደገና አሁንም ይህ መስቀልና ዙፋን አብረው እደሚሰሩ እናያለን። የጌታ እራት በአንድ መንገድ ጌታ ስለ መዳናችን ደሙን ማፍሰሱንና ሥጋውን መቁረሱን ስናስብ፤ በሌላ መንገድ ደግሞ በእ/ር መንግሥት አንድ ቀን የምንካፈለውን ታላቅ መዳን መጠባበቃችንን ይሳያል ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም። ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት፤  18እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም አለ (Lk 22:17–18)”
አሁን ድነናል ደግሞ በሙላት እንድናለን (this is because when Christ was personal present on earth, he inaugurated both the Kingdom and the new covenant in their real sense but not in their consummated sense)። ከዚህ የተነሳ መዳናችን በነዚህ ሁለት እውነታዎች መካከል ተወጥሮ የተቃኘ ነው። ሥጋዊ ሞትን ገና እንሞታለን ሆኖም ግን ሞትን አሁን አሸንፈናል፤ በርግጥ ከሞት ወደ ሕይወት አሁን ተሸጋግረናል (John 5:24; 3:18 11:24; 1 Cor. 15:52)። በእርሱ የሚያምኑትም የማያምኑትም ገና ዙፋን ተዘርግቶ የምንዳኝበት ቀን ወደ ፊት ነው፤ ሆኖም ግን አሁን እኛ ያመንን ከኩነኔ አምለጠናል (John 3:18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል)። አሁን ሐጥያት አይገዛንም (ሮሜ 6፡14) ከሐጥያት ሐይል ነጻ ሆነናል። ሆኖም ግን ገና ሐጥያት ከህይወታችን ሙሉ በሙሉ የሚወገድበት ቀን ይመጣል (ራዕ 21፡4-5)፤ እስከዚያ ድረስ ከሐጥያት ጋር እንጋደላለን (1 ዮሐ 1:8-10፤ ዕብ 12:4)፤ ከሥጋ ጋር ጠብ አለን (ሮሜ 8:13)
 

የተመረቀች መንግሥት፤ የተመረቀ ኪዳንና የተመረቀ መዳን!

ከላይ እንዳየነው “ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣልይህ ነው ይህንን ውጥረት የወለደው። በክርስቶስ መጀመሪያ መምጣትና ዳግም መምጣት መካከል ያለው ልዩነት የተመረቀ ኪዳን/ መንግሥት ነው። ንጉሳችን ከምድር የተወሰደበት  ወራት ውስጥ ብንሆንም፤ አዲስ ኪዳን ግን ይህንን ልዩ አስደናቂ እውነት ያውጅልናል። 
  • “ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ…” መዝ 110:1
  • እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ 6 እንደዚህም በሌላ ስፍራ ደግሞ። አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። 8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። (Hebrews 5:5–6)
ንጉሳችን በተሻለ ኪዳን፤ በተሻለ ዙፋን፤ በተሻለ መቅደስ፤ በተሻለ ክህነት እጅ ወዳል ሰራው ቤተ መቅደስ ገብቷል እንደዚሁም በአብ ቀኝ ዙፋን ተቀምጧል። መዳን ተመረቀ! አዲስ መንገድ ተከፈተ! ይህንን ነው
እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል። አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና 19-20 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤ (Hebrews 10:12–14፤ 19-22)
መንፈስ ቅዱስንም ከአብ ዘንድ ተቀብሎ ወደ ምድር አፍሶልናል። ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ክርስቶስ የጀመረውን ሥራ በምድር ይቀጥላል (ጰራቅሊጦስ) ደግሞም በሰማያዊ ሥፍራ እውነት የሆነውን በቤተክርስቲያን እውን እንዲሆን ያደርጋል።ከዚህ የተነሳ፦
 
ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነናል
ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። 4 ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። (Colossians 3:3–4)
አሁን ሞተናል…አዎን በሥጋ እያለን ሞተናል። ይህ ማለት የአሁኑ ኑሯችን ምትሃት ነው ለማለት አይደለም። እጅግ ረቂቅ በሆነ መልኩ ሕይወታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከመተሳሰሩ የተነሳ፤ የክርስቶስ እውነታዎች በእኛም እውነት ሆነዋል። ታያላችሁ? እርሱ በመስቀል እደሞተ፤ እኛም ተሰቅለናል፤ እንደ ተቀበረ በጥምቀት ተቀብረን በአዲስ ሕይወት ተነስተናል፤ እርሱ በአባቱ ዘንድ እንደተመለሰ እኛም ከእርሱ ጋር ተሰውረናል። ውጤቱ በዚህች ምድር ላይ ስንኖር እንደ መጻተኛ መስቀሉን ተሸክመን እንኖራለን ማለት ነው። አሁን ከክርስቶስ የተነሳ ሞተናል። አንድ ቀን እርሱን ስናየው እርሱን ስንመስል ይህ አሁን በክርስቶስ እውነት የሆነው የዚያኔ ክቡሩን ሥጋ ስንመስል ሙሉ በሙሉ እውነት ይሆናል። እስከዚያ ድረስ ግን በዚህ ውጥረት ውስጥ አለን። ውጥረቱ የሚገለጠው “ራሳችንን በመካድና መስቀሉን በመሸከም ደቀ/መዝሙር በመሆን ነው። ሞተናል ማለት አሁን በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ተጸእኖ ሥር ውስጥ እንኖራለን ማለት ነው በመንፈስ ቅዱስ የሥጋን ምኞት እንገድላለን። በመንፈስ እንመላለሳለን ደግሞም እንኖራለን። ሁለቱንም ገጽታዎች ሐዋርያው በአንድ ላይ ያቀርብልናል። አሁን ሞተናል፤ ተነስተናል በክርስቶስ ተሰውረናል (ቁጥ.3) አንድ ቀን ደግሞ በክብር እንገለጣለን (ቁጥ. 4)፤ እስከዚያስ?  ….. ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም (ቁጥ 1–2)”
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለናል
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። 3 በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።
 
እዚህ ጋር ተመለከታችሁ? ልጆች ነን ይለናል ደግሞም ገና ሲገለጥ ደግሞ እርሱን እንመስላለን። ይህንን ነው ውጥረት ያልነው። ነን….ደግሞ እንሆናለን። ልዩነቱን ን ተመልከቱ፤ አሁን ልጆች በመሆናችንና ደግሞ ወደፊት በሙላት ሲገለጥ በምንሆነው መካከል ሐላፊነታችን ምንድር ነው? ልክ ሐዋርያው ጳውሎስ ሐሳባችሁን በሰማይ ይሁን እንዳለን..ዮሐንስ ደግሞ እንዲህ ይለናል “ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።አሁን በሕይወታችን ልጅነታችን የምንገልጠው በመንፈስ ቅዱስ ሐይል በመታዘዝ ነው! መታዘዝ ያልሆነውን ለመሆን ሳይሆን በክርስቶስ የሆነውን ለመሆን ነው። መታዘዝ ለመዳን ሳይሆን በርግጥ ስለዳንን የተገባ ህይወት ነው። መቼም አንባቢዪ ይህንን ይረዳል ብዬ ባምንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በትንሳኤ አካል ስንወርስ፤ ትዕዛዛት ሥፍራ የላቸውም። ስንቶቻችሁ አሁን ልባችሁን እንዲመታ እያዘዛችሁት ነው? ርግጥ ነው ይህንን ስታነቡ አይናችሁን እያዘዛችሁት ነው። ግን ደግሞ ሳንባችንን እያዘዝነው አይደለም። እነደዚሁ ሁሉ ይህ የአሁን ኑሯችን በመታዘዝ ልጅነታችንን የምንገልጥበት ሕይወት ሲሆን፤ መጪው ዓለም ውስጥ የምንወርሰው የትንሳኤ አካል ግን ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ የተመራ ከመሆኑ የተነሳ በባሕሪያችን እንዲሁ ጽድቅን እያደረግን እንኖራለን። ለዚህ ነው
“ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ…” 1 ቆሮ 15:45
የመጀመሪያው ሰውነታችን ራሳችን የምናንቀሳቅሰው ሕይወት፤ ከእግዚአብሔር ተለይቶ መኖር የሚችል ማንነት ሲሆን በሁለተኛው አዳም በክርስቶስ የምናገኘው ሰውነት ግን መንፈስ ቅዱስ የሚያንቀሳቅሰው ሕይወት ነው መንፈሳዊ (πνευματικόν– ፕኑማቲኳን) አካል ይነሣል ይህን ቃል –ፕኑማቲኳን-  ባለፈው ጹሑፌ ላይ “ስለመንፈሳዊ በረከቶች…” ስንነጋገር መንፈሳዊ የሚለው የበረከቱ ምንጭ ማን እደሆን ለማሳየት እንጂ ቁሳዊ ባልሆኑ በረከቶች ተባርከናል ለማለት እንዳልሆነ ነግሬያችሁ ነበር። ይህም እነዚህ በረከቶች ከመንፈስ ቅዱስ የመነጩ በረከቶች እንደሆኑ ማመልከቱ ነው። አሁንም ይሄው ቃል መንፈሳዊ አካል ሲል….የምንለብሰው ሰውነት ቁሳዊ አለመሆኑን መናገሩ አይደለም። በፍጹም! ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ ደ/መዛሙርቱን እንዲነኩትና አጥንትና ሥጋ እንዳለው እንዲያረጋግጡት ገፋፍቷቸው ነበር። ምክኒያቱም የክርስቶስ ትንሳኤ አካላዊ ነበርና ነው) ቅዱሳን ክርስቶስ ሲመለስ ማንም ወንድሙን እወቅ ብሎ አያስተምርም። ይህ ሁሉ ይቀራል። ሁላችን በባህሪያችን እግዚአብሔርን ማስደሰት ተገጥሞልን አዲስ ሕይወትን “ሀ” ብለን እንጀመራለን። እስከዚያ ቀንድ ድረስ ግን አሁን በመንፈስ ቅዱስ በሆነ መታዘዝ መዳናችንን እንገልጣለን።
እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።  ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
በሞት ትንሳኤ ይህ የሚበሰብሰው የሚሻር ከሆነ፤ ታድያ ይህ የአሁኑ ሕይወት ምን ፋይዳ አለው? ይህንን ክፍል ሲዘጋ እንዲህ ብሎ ይጨርሳል
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ። 1 Co 15:58
በዚህ በአሁኑ ሰውነታችንና ወደ ፊት በምንለብሰው ሰውነት መካከል ልዩነት እንዳለ ሁሉ፤ ግንኙነትም አለው። በዚህ ሥጋ የምንዘራውን በሌላ መልኩ እናጭዳለን (ገላ 6)። ስለዚህ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አንዘራም። ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት እንድናጭድ።፡ስለዚህ በክርስቶስ የተወደዳችሁ ቅዱሳን መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ቀን ይልቅ አሁን ወደ እኛ ስለቀረበ የመዳንን ተስፋ እንደ ጋሻ፤ መዳናችንን እንደ ራስ ቁር፤ የሰላሙን ወንጌል የሚያበስሩ እግሮች ተጫምተን እንጠብቅ!
  • ድነናል (Eph 2:8) ነገር ግን ገና ደግሞ እንድናለን (Rom. 5:9)
  • ተቀድሰናል  (1Cor 6:11) ነገር ግን ገና ደግሞ እንቀደሳለን (1Thess. 5:23-24)
  • እንደ ልጆች ተቀብሎናል (Rom 8:15), ነገር ግን ገና ደግሞ ልጆች እንሆናለን (Rom 8:23)
  • አዲሱን ሰው ለብሰናል (Col. 3:9-11), ነገር ግን ገና ደግሞ አዲሱን ሰው እንለብሳለን (Eph. 4:21-24)
  • ተዋጅተናል (Eph. 1:7) ነገር ግን ገና ደግሞ እንዋጃለን (Rom 8:23)

 

ቅኝታችን ታድያ ምን ይመስላል?

ክራር-ነክ ሙዚቃ መሳሪያዎች በየጊዜው ይቃኛሉ። ይህም በሁለት ጥግ እያንዳንዱ ክሮች ትክክለኛ ቅኝታቸውን እስኪይዙ ድረስ መወጠር አለባቸው። አሊያ ዜማቸው ጥዑም አለመሆን ብቻ ሳይሆን የዜማን መርህ ስለሚጣረስ ዜማ መደርደር አይችሉም። አንዷ ክር በግማሽ ወይም በሙሉ ኖታ ወጣ ወይ ወረድ ብትል፤ ዜማው ስለሚበላሽ ተጨዋቹ መሳሪያውን መቃኘት አሊያም ቅኝት የሚያውቅ ሰው መጥራት አለበት። ልክ እንዲሁ ወንጌላችንም በክርስቶስ መምጣትና ዳግም መምጣት ተወጥሮ የተቃኘ ቃል ነው። ከዚህ ውጥረት የተነሳ መዳናችን፤ ተስፋችን፤ ልጅነታችን፤ በረከታችን፤ አላማችን፤ ቅድስናችን..ወዘተ ልክ እንደ እያንዳንዱ የክራር ክሮች ቅኝት ይዘዋል። ክርስቶስ ከሰማያዊ ሥፍራ ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይህንን ታላቅ የማዳን ዜማ በዓለም ዙሪያ ላሉ ህዝቦችና በአየሩ ላይ ላሉ አለቆች ብዙ ገጽታ ያለውን ጥበብ ይደረድራል። ይህ ግን በጥሩ መልክ የተቃነች ከሆነ ብቻ ነው። 

ይህን ሚዛናዊነት ካለመጠበቅ የተነሳ፤ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ውስጥ ጽንፈኛ እንቅስቃሴዎች ሲነሱ አይታለች። ይህ ማለት፤ በአንድ እጅ በእውነት ድነናል በሌላ መልኩ ደግሞ ገና ሙሉ በሙሉ መዳናችን አንድ ቀን እንደሚገለጥ በሚዛን አለመያዝ ነው። በአዲስ ኪዳን እነዚህ ሁለት ጽነፈኝነቶች በቅዱሳት መጻሕፍት ለትምህርታችን ተጽፈውልናል። ለምሳሌ ያህል የተሰሎንቄን ቤተክርስቲያንና የቆሮንቶስን ቤተክርስቲያን እንደ ናሙና አድርገን እንውሰድ።

በሽሽት ላይ ያለችው ቤተክርስቲያን! (Under-Realized Soteriology)

ይህ ጽንፈኛነት የመነጨው ገና ወደ ፊት በሚሆነው መዳን ላይ ትልቅ አጽንዖት ከማድረግ የተነሳ ነው። አጉልታ ገና የሚሆነውን ትጠባበቃለች እንጂ አሁን በክርስቶስ ከሙታን በመነሳት የተመረቀው መዳን ላይ ግን አትኩሮት አታደርግም። ይህች ቤተክርስቲያን “ኢየሱስ ይመጣል!!!” የሚለውን መልዕክት ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከመደጋገሙ የተነሳ አማኞቿ እጅና እግራቸውን ሰብስበው በፍርሃት ይጠባበቃሉ።  ይህ ማለት የክርስቶስ ዳግም ምጻዓት ላይ ትልቅ አትኩሮት ይሰጣል፤ ነገር ግን አሁን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠንን የትንሳኤውን ጉልበት ላይ እፍር የማለት ስሜት የሚሰማት ቤተክርስቲያን ናት። በሃይል የምትናጠቅ አትምስልም። ከአጋንንት ጋር ባላት ግብግብ ወደ መሃል ገብታ በእ/ር ሐይል በወንጌሉ ቃል ጉልበት ከመፋለም ይልቅ ዳር ይዛ “ማራናት የምትል” ቤተክርስቲያን ናት። አንድ ቀን ቆይ ትላለች። በተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን ውስጥ ግልጽ ሆኖ የሚታየው ችግር የጌታ መምጫ ደርሷል ተብለው፤ የአሁኑን ኑሯቸውን ያጓጓሉ አማኞች የሚኖሩባት ከተማ ነበረች። ከዚህ የተነሳ ሊሆን ይችላል እንዳንዶች ጌታ ሊመጣ ነው ብለው ሥራቸውን አቁመው በድጎማ መኖር የጀመሩና ከሥራ ፈትነታቸው የተነሳ ደግሞ በሰው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ያስቸገሩ ያሉባትም ቤተክርስቲያን ናት። ይህች ቤተክርስቲያን ጥግ ይዛ የክርስቶስ መምጫ የምትጠባበቅ ነች።
ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት። የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ፥ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን።  ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤
የዚህ ዓይነቷ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቶ አሁን በግርማው ቀኝ ተቀምጦ እየሰራ እንደሆን ያልገባት ቤተክርስቲያን ናት። ለዚህች የሚሰበክላት ኢየሱስ በክብር አሁን መቀመጡን ነው። መምጣቱን የምትጠባበቀው ሸሽቶ በመቀመጥ ሳይሆን ጉባኤው በአደባባይ የክርስቶስ ምስክር በመሆን ነው።
ለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።
ለዚህች አይነቷ ጽንፈኛ ቤተክርስቲያን በሥቃይ ማለፍ፤ በመከራና በውርደት ማለፍ ልክ እንደ ክርስትና ማረጋገጫ ምልክት ትወስዳለች። የተቀደደ ጫማና የተቦጫጨቀ ልብስ የሌለው እውነተኛ አማኝ አይደለም። ቃል አጋኖዬ መቼም ግልጽ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ሐዋርያው ጳውሎስ ሮሜ ምዕራፍ ሠባትን ብቻ ሳይሆን ምዕራፍ ስምንትንም የጻፈው እርሱ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነው።  
 

ዘራፍ ዘራፍ የምትለዋ ቤተክርስቲያን! (Over-Realized Soteriology)

በአንጻሩ ደግሞ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አለች። አቤት! አቤት! ይህች ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ የምትል ሁከት የበዛባት ቤት ነች። ይህች ቤተክርስቲያን ደግሞ አሁን በክርስቶስ በተሰጠን በረከቶች ላይ ትልቅ አጽኖኦት ከማድረጓ የተነሳ ዘላለማዊ ርስቷን አሁን ያደረገች፤ ክርስቶስን መጠባበቅ የዘነጋችና ገና ኢየሱስ ሲገለጥ በሙላት የምንወርሰውን አሁን ሙሉ በሙሉ እንደወረስን አድርጋ የምታጋንን ነች። ከዚህ የተነሳ አንዳንዶች እንደመልአክ ሆነናል ቢሉና ሙታን ትንሳኤ አሁን አሁን ሆኗል የሚል አማኖች ቢሞሉባት አያስገርምም፡፤ ገና የሚሆነው ለእርሷ አሁን ነውና። የዓለም ሀብት ትወርሳለህ…የረገጥከውን ትወርሳለህ….ሕንጻው ያንተነው…ብሩና ወርቁ ያንተ ነው…ሳታጠና ፈተና ታልፋለህ…ሳትሰራ ወርቅ በወርቅ ትሆናለህ….የንጉስ ልጅ ስለሆንህ ኮትና ሱሪህ ከምን እንደተሰራ እያወራህ የመንፈሳዊነትህን ልክ ትገልጣለህ። ለዚህች አይነቷ ቤተክርስትያን ለመከራ ሥፍራ የላትም። በህመም ማለፍ ሽንፈት ነው። የንጉስ ልጅ ነህና እንደ ንጉስ ትንቀባረራለህ ባይ ናት። ይህንን የሐዋርያውን ምጸት እስኪ ስሙልኝ?
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? አሁን ጠግባችኋል፤ አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል፤ ያለ እኛ ነግሣችኋል፤ እኛ ደግሞ ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ ብትነግሡ መልካም ይሆን ነበር። 1 Co 4:7–8
ይህች ቤተክርስቲያን ጌታ በመካከሏ ከሰራው አስደናቂ ማዳን ልቧ ከመሸፈቷ የተነሳ ሚዛናዊነቷን አጣች። ጌታ ከመካከሏ ለጥቂት ጊዜ በሃይልና በብዙ የጸጋ ሥጦታ ስለሞላት ያገለገላትን ሐዋርያና መንፈሳዊ አባቷን በንቀት ዓይን መመልከት ጀመረች። የጳውሎስና የጓደኞቹ በመከራና በሕመም ማለፍ እንደ መንፈሳዊ ግለት መቀዝቀዝ መለኪያ አድርጋ አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ከመጡት ዘራፍ በሚሉ ሐዋርያ ሳይሆኑ ሐዋርያት በሆኑ አዳዲስ መሪዎች የጳውሎስን ሐዋርያነት ማናናቅ የጀመረች ትመስላለች።
ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና። እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን።  እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥ እንንከራተታለን፥  በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤  እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።  እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም።   በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።   እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።
ይህ አሁን ያለንበትን ዘመን ይመስላል። የእምነት-ቃል እንቅስቃሴ በይፋ ከጀመረ ከአንድ ሰው እድሜ በታች ነው። የዚህ አስተምህሮት ትልቅ አባት አድርገው የሚቆጠሩት ከሞቱ ጥቂት ዓመት ጊዜው ነው። የዚህ እንቅስቃሴ አራማጅ የሆኑት ጥቂቶች ግን የክርስቲያኑን ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት ከመሆኑ የተነሳ የዛሬ 30 ዓመት ይህ ትምህርት የትም አይደርስም ብለው ብዙዎች ቢገምቱም አሁን ትልቅ ሥር ሰዶ መፍትሔ ከየት እንደሚመጣለት የማይታወቅ ችግር ሆኗል። የዚህ እንቅስቃሴ ትልቅ ስህተት ይህ ከላይ ያየነው ጽንፈኝነት ነው። በአሁኑ ላይ ጥልቅ ትኩረት ከመስጠታቸው የተነሳ ብልጽግና እንጂ ክርስቶስ የማይሰበክበት መድረኮች ሆነዋል። ለምሳሌ ያህል ከመሰረታዊ ትምህርታቸው መካከል ሦስቱ (1) “በቃል ነገሮችን ካለመሆን ወደ መሆን ታመጣለህ” የሚለው እጅግ አሰቃቂ አነጋገር ነው (ምክኒያቱም ምንም ቢደባበስና ከአውዱ የተለየ ጥቅስ ከማምረው እውነት ለማስመሰል ቢሞክሩም ይህ የመለኮትን ሥራ መሻማት ነው።፡እግዚአብሔር ብቻ ነው ተናግሮ የሌለውን ወደ መሆን የሚያመጣው። በኢሳያስ መጽሐፍ ያህዌህ ራሱን ከጣኦታትና ከአሕዛብ አማልክት የለየው በዚህ ሐይሉ ነው “እነዚህን ሁሉ በቃሉ የፈጠረ ማን ነው?”)።   በመጽሀፍ ቅዱስ መለኪያ ይሁን በቤተክርስቲያን ታሪክ ማስረጃ፤ ይህ እንቅስቃሴ የተወገዘና ከየትኛውም ቤተእምነት ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ያወገዙት አስተምሕሮት ነው። በርግጥ ይህ አስተምህሮት ሥር ከመስደዱ የተነሳ እውነት ቢመስልም ጠለቅ ብሎ ላየው ግን ቅዱሳት መጻህፍትን የሚጣረስ ብዙ ነገር አለው። (2) ሌላው ለዚህ አስተምሕሮት መሰረት የሆነው አዋጅ ቃላቸው “እግዚአብሔር በእምነት የሌለውን አድርጎ ይናገራል…ስለዚህ አንተም በእምነት የሌለውን ነገር አድርገህ ተናገር” ባዮች ናቸው። በርግጥ እግዚአብሔር ያምናልን? ማንን ያምናል? እኔና እናንተ ሁሉን ቻዩ አምላክ በክርስቶስ በፈጸማው የማዳን ሥራ ላይ አምነን ድነናል። ከእርሱ በላይ የሚምልበት ማንም ስለሌለ በራሱ አልማለምን? እምነት መታመንና ማመንን ገንዘቡ ያደረገ እንደሆን ነው መጽሀፍ ቅዱሳዊ የሚሆነው። ዝም ብሎ ማመን የኒው ኤጅ ትምህርት ነው። መኪና መኪና መኪና በል መኪና ታገኛለህ። አጋንንታዊ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ነው “በአየሩ ላይ ቃል እንዝራ…ቃላችን ሀይል አለው…ቃላችን አካባቢው ላይ ተጽ ዕኖ ያመጣል” የሚለውን ፉከራ የሰጡን። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በወንጌላት ላይ በክርስቶስ እግር ሥር ተደፍተን “ቃል ብቻ ተናገር ብላቴናዬም ይፈወሳል” እንድንል ያደፋፍሩናል። መልሳችን ያለው ሥጋ በሆነው ቃል እንጂ፤ በሥጋ ለባሽ ቃል አይደለም። እነርሱ ግን “እኔ ቃል እናገራለሁ” እንድንል ያደፋፍሩናል። (3) በመጨረሻ ሌላው የዚህ እንቅስቃሴ ጽንፈኝነት እግዚአብሔር የሰጣቸው ተስፋ ቃሎች በሙሉ አሁን በሙሉ ይሆናሉ ባዮች ናቸው። ከላይ እንዳየነው ለነዚህ ሰዎች ገና ሊገለጥ ባለው መዳን ላይ አላተኮሩም። ልክ በሽሽት ላይ ያለችው ቤተክርስቲያን አሁን የተመረቀውን መዳን ጆሮ ዳባ ብላ ገና የሚመጣውን ብቻ እንዳጎላች፤ ይህች ደግሞ በአንጻሩ ሊገለጥ ያለውን ታላቅ መዳን ችላ ብላ አይኗን ያተኮረችው አሁን በሚሆነው ነገር ላይ ነው። እግዚአብሔር በዚህች ምድር ሳለን ሁሉ እንዲኖረን ይፈልጋል የሚለው መፎክራቸው ይህንኑ ጽንፈኝነታቸውን ያረጋግጥልናል። ለነርሱ ሰው ሁሉ ሐብታም መሆን ይችላል…ይህንም ከቅዱስ ቃሉ ጥቅስ ይፈልጋሉ….ሁላችን እንፈወሳለን….ሁላችን ጥሩ ትሩ ቤቶችና ሥራዎች እንይዛለን። ለምሳሌ ከ ዘዳ 28 ወስደው የሚሰብኩት በረከትና መርገም በትንሹ ብሉይ ኪዳናዊ አሊያም አዲስ ኪዳንን ጨርሶ ያልተረዳ እምነት ነው፡፡ (One of the most respected pentecostal, biblical scholar and assembly of God ordained minister, Gordon D. Fee, whom I respect so much and from whom learned a lot comments on this movement that the movement hardly understand the New testament to begin with. I fully concur with his comment. The problem is that many Christians who follow their teachings do not know at all that this movement is not a historic Christianity to begin with leave alone, to be biblical and are not acknowledged as such.)

መስቀልና ዙፋንን ያማጠነች ቤተክርስቲያን! (Realized Soteriology)

የነዚህ የሁለቱን አይነት ቤተክርስቲያን ጽንፈኝነት አስወግደን የፊልጵስዩስ አይነቷን እንድንሆን እግዚአብሄር ይርዳን። ይህም ለክርስቶስ ወንጌል ታማኞችና ሕይወታቸው ከወንጌሉ አንጻር የሚኖሩ እንሆን ዘንድ ነው። ይህ ይቀረኛል። ይህንን እጠማለሁ። በዚህ ልገሰጽና ልመከር፤ እወዳለሁ። የማንንም አይነት ሞዴል ቤተክርስቲያን አንድንከተል አልተጠራንም። ወንጌልን የምታንጸባርቅ ቤተክርስቲያን ያቺ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ናት
ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።  በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤  ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤  በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት፥ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና። (Php 1:27–30.)
የወንጌልን ሕይወት የምታንጸባርቅ ቤተክርስቲያን፤ ይህም መስቀልና ዙፋን በመድረኳ ላይ የሚታወጅባት፤ በመዝሙሯ የሚሰማባት፤ በምዕመኗ መውጣትና መግባት ላይ የመስቀሉን ውርደትና የትንሳኤውን ሐይል መዓዛ የሚሸተትባት እስከሆነች ድረስ ድህነቷና ብልጽግናዋ ለጌታ ፈቃድ አሳልፈን እንሰጣለን። ድሃዋን ቤተከርስቲያን “ለመስቀሉና ለመንግስቱ ታማኝ” ስለሆነች ሌላ አልጨምርብህም ተብላለች። በብልጽግናና በታዋቂነቷ ግን አለሁ አለሁ ያለችው ሎዶቂያ ግን ተገስጻለች። ስለዚህ ዋናው ብልጽግና ወይ ድሃነት አይደለም። ሕመም ወይም ጤንነት አይደለም። ከፍታ ወይም ዝቅታ አይደለም። በርግጥ እምነት ከነዚህ ሁሉ በላይ ያረገ ነው። እምነት በክርስቶስ ማንነት፤ ሥራና ቃል ላይ አነጣጥሮ የሰውን ሁለንተና የሚዳሥ እንጂ፤ በዚህና በዚያ ላይ ያተኮረ አይደለም። በርግጥ በመስቀልና በትንሳኤ የተመጣጠነ ሕይወት ይህንን ይመስላል፦

 

“አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤  በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።  አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም።  ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥  በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤  ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤  ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው” (2 ቆሮ 6:1–10)

“ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤  እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤  የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።  የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።  ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።  ነገር ግን። አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤  ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።  በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።  ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።  የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው(2 ቆሮ 4:7–18)

ይህንን ስል አንድ ነገር ግን ለአንባቢዬ ግልጽ እንዲሆን እወዳለሁ። አሁን በዚህች ምድር ስንኖር የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሐይል አይሰራም እያልኩ አለመሆኔን እንድታስተውሉ ነው። ጌታ በድንቅ በዓለማችን በሥራ ላይ ነው። በመንፈሳዊ ሥጦታዎች ሙሉ በሙሉ መሥራት አምናለሁ! በርግጥ መንፈስ ቅዱስ የሰጠንን ሥጦታ ከማርገብገብ ወደ ኋላ እንድንል ለአፍታ አልወድም፤ ከማንም እነዚህ ሥጦታዎች ከመፋፋም እንዲቀዘቅዝ ምኞቴም አይደለም። ራሴን እንደ ካሪዝማቲክ አማኝ እቆጥራለሁና (ካሪዝማታ – በአዲስ ኪዳን ግሪክ ጸጋ ከሚለው ቃል የተወረሰ ሲሆን፤ የፕኑማቲኳን ትርጉሙን ከላይ ጠቅሼያለሁ)። ጌታ በፈውስ ስጦታ አሁን ይሠራል፤ በትንቢት ሥጦታ ምሪትን ይሠጣል (ምሪት የሚለው ይሰመርልኝ)፤ አንዱ መንፈስ የጥበብን ቃል፤ የእውቀትን ቃል፤ ታምራት ማድረግን፤ መናፍስት መለየትን፤ የጸሎት ልሳናትን መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደ ለአንዳንዶቻችን ያድለናል። (የማይተረጎመው የጸሎት-ልሳን ከሌሎች ሥጦታዎች ለየት የሚያደርገው፤ ዓላማው ጉባኤን ለማነጽ ስላልሆነ፤ በጉባኤ መካከል ያለአንዳች ገደብ አማኙ እንዲጠቀመው በግልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ይከለክላል (1ቆሮ 14:4-28 – የሚተረጉም ባይኖር ግን በማኅበር መካከል ዝም ይበልና ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር)። በልሳናት የሚጸልይ ራሱን ብቻ ያንጻልና…ትንቢት የሚናገር ወይም አምስት ትርጉም የሚሰጥ ቃላት በጉባኤ የሚናገር ግን አካሉን ያንጻል። እናስታውስ ስጦታ በአካል ውስጥ የራስ ጥቅም መሙያ አይደለም (ጴጥ 4፡ 10-11)መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን ወልድን እንድንመስል በሐይል በሥራ ላይ ነው። ሆኖም ግን እነዚህ ስጦታዎች አማኙ ሲፈልግ መዘዝ እያደረገ ዘራፍ የሚልበት አለመሆኑንና አማኙ መከራንና መስቀሉን ከመሸከም ሕይወት፤ እንዲሁም በተለያዩ መከራዎችና ሥቃዮች እንዳያልፍ መታወቂያ ካርድ አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ በታላቅ ሕመም እንደነበር ለገላትያ ቤተክርስቲያን ነግሮአቸው እንደነበር ለናሙና ያህል ማየት እንችላለን። መንፈሳዊ ሥጦታዎች መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን እርስ በርስ እንድንተናነጽና እንድናድግ የሚጠቀምበት መሳሪያዎች ናቸው እንጂ የቅዱሳት መጻሕፍት ምትክ አይደሉም። ለምሳሌ ያህል በክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያልተገለጠ መለኮታዊ ባህርይ ተገለጠልኝ የሚል ነብይ ቢነሳ ያንን የአዲስ ኪዳን ነብይ ጥሪ አለመሆኑን አበክረን መናገር ይኖርብናል። የመለኮት ሙላት ሁሉ በክርስቶስ ተገልጧልና; ዛሬ በክርስቶስ ያልተገለጠ ማንነት ተገለጠ ቢል፤ ወይ እግዚአብሔር አይለወጥም የሚለውን ቀደን መጣል አለብን አሊያም ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለውን መፎክር መተው አለብን። ምክኒያቱም እግዚአብሔርን ያለክርስቶስ ማወቅ፤ የክርስቶስን ሙላት መካድ ነውና። ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን ገጾች የነብያትን አገግሎት ከሐዋርያት-ሥራ እንደዚሁም ከሌሎች ክፍሎች ሥንቃኝ፤ የነብይ ቃል ለአማኖች ምሪትን፤ ለቤተክርስቲያን አቅጣጫን ለመስጠት እንጂ ከዚህ በፊት ያልተገለጠ ትምህርትና እግዚአብሔር ማን እንደሆነ መተረኪያ አልነበረም;። የአጋቦስ ትንቢት፤ ለአንጾኪያ ቤተክርስቲያን እርዳታ ትሰበስብና በኢየስሩሳሌም ላሉት ቅዱሳን ርዳት እንዲልኩ ምሪትን ለመስጠት ነበር። ለሀዋርያው፡ጳውሎስ የመጡለት ትንቢቶችና ራዕዮች ሁሉም ለአሕዛብ ሚሽንና እስከ ሮም ድረስ ላለው ክርስቶስን የመመስከር ተግዳሮቱ ምሪት እንጂ ትንቢቶች አዳዲስ አስተምሕሮት መቀበያ አልነበረም። የቆላስያስ ቤተክርስቲያን የገባችበት አደጋ፤ ራዕይ አየሁና መልአክ ተገለጠልን እያሉ አማኞችን በክርስቶስ ከመጣው-መገለጥና ለመዳን እንዲሁም ለመለወጥ የክርስቶስን በነጠላ በቂነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት አይናቸውን ዘወር ስላደረጉ በታላቅ ግሳጼ ሲጽፍላቸው፤
የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።  ማንም በሚያባብል ቃል እንዳያስታችሁ ይህን እላለሁ…እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።  ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።  እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።  በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።   ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል…ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ። እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም” Col 2:6–19.

መልዕክቱ ግልጽ ነው፤ መንፈሳዊ ሥጦታ ማለት በክርስቶስ ከመጣው የወንጌል ሙላት አይኖችን ዘወር የሚያደርግ ከሆነ፤ ይህ አዲስ ኪዳን የማያውቀው ስጦታ ነው። እንዲህ አይነት አቋም ቤተክርስቲያን ካልያዘች ወንጌል፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የማናውቀው ገጽታ ይዞ እናገኛለን። የሞርሞን መስራች ለምን ይመስላችኋል የሳተው? የጆሴፍ ስሚዝ መፎክር “ወደ ጥንታዊቱ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እንመለስ” ባይ ነበር። በሞተ ጊዜ ትምሕርተ እግዚአብሄርን፤ ትምሕርተ ክርስቶስን፤ ትምሕርተ ሥነ-ፍጥረትን፤ ትምሕርተ-ቤተክርስቲያንን፤ የቤተሰብ መዋቅር…በሙሉ አዲስ በተቀበለው መገለጦችና ራዕያት ከመበራረዛቸው የተነሳ የሞርሞን ኢየሱስ የኛ ጌታ አይደለም። ተቀበልሁ ብሎ የጻፋቸውን መገለጦች አትመው አሁን እርሱ ታላቅ ነብይ በመባል፤ ጹሑፉም ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ሥልጣን ያለው ሆኗል። ታድያ እኛስ መንፈሳዊ ሥጦታዎች በምን ረገድ እንደሚሰሩና ምንነታቸውን ካልተረዳን ሞርሞን የወደቁበት ሥህተት የእኛ የማይሆንበት ምን ምክኒያት አለ? እኛስ ሰዎች አይደለንምን? ከወዴት እንደወደቅን ማሰብስ መንፈሳዊነት አይደለምን? አሠራሩ ያው ነውና። በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በትምህርቴ ላይ እንዳሰፈርሁት መንፈሳዊ ሥጦታዎች አሁን ክርስቶስ ሃይላትንና ሥልጣናትን ድል አድርጎ በአባቱ ቀኝ ድል አድራጊ ሆኖ መቀመጡን፤ መንግሥቱ በሓይል መመረቋን፤ ማወጂያ መሳሪያ መሆኑን ከኤፌ 4 ላይ አይተናል “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል። እርሱም አንዳንዶቹንአድርጎ ሠጠ

ስለዚህ ትንቢት ተናጋሪው ሲናገር፤ ትንቢቱ በምሪት መስጠት ላይ ይወሰን እንጂ በትንቢት በክርስቶስ የተሰጠውን አስተርዕዮ አይጋፋ። በመንፈስ ቅዱስ የጥበብ ቃል የሚናገር፤ በበሰሉት መካከል የምንናገረው ጥበብ ከሰማይ ዱብ ያለ ሳይሆን አግዚአብሄር አስቀድሞ ለክብራችን የወሰነውን የክርስቶስን ሚስጢር ምን እንደሆነ አስቀድሞ ይማር። በፈውስ ሥጦታ የሚያገለግል ደግሞ አካሉን ያገልግል፤ በመካከላችን በህመም ለሚማቅቁ መለኮታዊ ጉብኝት ያግኙ እንጂ ይህንን ስጦታ አስተማሪ ለመሆን በመሞከር አያዳፍን። ምክኒያቱም አስተማሪዎች ከሁሉ በላይ በልዩ አለንጋ ይገረፋሉና ነው። አስተማሪ ከመሆን በፊት ጥሩ ተማሪ/ ደ/መዝሙር መሆን ምርጫ የለወም። ኢየሱስ ለሦስት ዓመት ተኩል ያሕል ደቀመዛሙርቱን ለሊት-ተቀን አስተምሮ፤ ከዚያም ለ40 ቀናት እያለፈ እያለፈ ከትንሳኤው በኋላ ተገልጦ ይልቅ ካስተማራቸው፤ እኔ ማን ነኝ ታድያ ሳልማር ለማስተማር መሞከር ያለብኝ? ትውስ አይላችሁም ፈሪሳውያን “እነዚህ ሳይማሩ መጽሐፍትን እንዴት አወቁ?”…ጥያቄያቸውንም ራሳቸው በራሳችው ሲመልሱ “ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው!” ብለዋል። ሳይማሩ ማለታቸው ከፈሪሳውያን ትምህርት ቤት በዶክትሬት ያልተመረቁ ማለታቸው ሲሆን ከኢየሱስ ጋር መሆናቸውን መጦቆማቸው ደግሞ፤ ያ አሳች ብለን የሰቀልነው እርሱ አስተምሯቸዋልና ነው። ምንም እንኳ ከፈሪሳውያን ትምሕርት ቤት ባይመረቁም፤ በክርስቶስ እውነተኛው መምህር እግር ሥር ግን ለሶስት ዓመት ሠልጥነው ተመርቀዋል። በአንጻሩ ደግሞ ቅዱስ ቃሉን ለማስተማር ጸጋ የሰጠን አንዳንዶች ደግሞ ትንቢትና የመገለጥን ቃል ለመናገር ያልተሰጠንን ለመውሰድ ስንሞክር ከቅዱስ ቃሉ እንዳንወጣ በተሰጠን እናገልግል። አሁንም አላማው ሌላውን ለማገልገል እንጂ ታዋቂ ለመሆን አይደለም። ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ሥርዓት ይዞ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ መሰማራት ይችል ዘንድ በክርስቶስ የመጣው በቅዱሳት መሳሕፍት ጠጠርዞ የቀረበልን የወንጌል አስተርዕዮ በመካከላችን አዛዥ ይሁን!

ስለዚህ እነዚህን ጽንፈኝነቶች አስወግደን በመስቀልና በዙፋን መካከል ቆመን እርስ በርሳችን እየተመካከርን፤ እየተናነጽን፤ እየተገሳሰስን የምንሰብከው ክርስቶስን ይሁን (ቆላ 1፡ 28-29)። በዚህ ዘመን ያለች በቤተክርስቲያን ሊሰበክላት የሚያስፈልገው “ፍጻሜ ገንዘቧ” መሆኑን ነው።፡በርግጥ አይናችን ለዘላለማዊ ርስታችን ታውሯልና ሐዋርያው ለኤፌሶን የጸለየላት ያ ታላቅ ጸሎት ለእኛም ያስፈልገናል “ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው” ብድራታችንን ትኩር ብለን ማየት ተስኖናል። ተስፋችን በሚገለጠው ክብር ላይ ሳይሆን ተስፋችን አሁን እግዚአብሄር በሚያደርገው ጊዜያዊ ትርፍ ነገር ላይ አርፎብናል። በእርግጥ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሁሉ ለማስተካከል ታጥቀው የተነሱትን እያንጓጠጥን ‘የሥህተት አስተማሪ’ የሚል ስያሜ ብንሰጣቸውም፤ እውነት ግን በልጆቿዋ ትጸድቃለች። ሆኖም ግን ጴጥሮስስ እንዲህ አላለምን ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ (1 Pe 1:13) ኧረ የቤተክርስቲያን የ2000 ዓመት ቆይታዋንም መመልከት በራሳችን ዓይን ጠቢባን እንዳንሆን ትህትናን ያላብሰናል…ታሪክም ይዳኛልና!

ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ታድያ እንዴት እንኑርን?

“ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነውእኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል” (2 Peter 3:9–14)”ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።  የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል። ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤ ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን። ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ” (2 Peter 3:9–14)

English Version

And this is eternal life, that they know you the only true God, and Jesus Christ whom you have sent.” (John 17:3)
 
God has not sent an angel or another sinless human being to save us.
 
“…God is love. In this the love of God was made manifest among us, that God sent his only Son into the world, so that we might live through him. In this is love, not that we have loved God but that he loved us and sent his Son to be the propitiation for our sins.(1 John 4:8–10)
 
If that were the case, salvation would  have been simply a rescue mission and not a personal knowledge of God. Rather, God sent his own begotten Son, who himself is divine. Anselm of Canterbury, one of the most renowned church father of the 11th century, in his ‘Cur Deus Homo (why God became a man)’  writes:

“The redemption of man could not be effected by any other, whether by an angel or a man, than the person of God. If anyone other than God were to redeem us from eternal death, the redeemed would be rightly judged to be his servant. Therefore it is not redemption for the redeemed will serve other than God himself (as they do now)”

He is saying, as long as the root of human sinfulness is rebelliousness, exchanging the rule of God to the rule of another lesser being, namely satanic or creature-ly rule, salvation would not be true salvation if it is not brought about by God himself, for we would still be under this agent whom we call savior who is not God. Therefore, in order for salvation to be true and biblical, it has to entail first redemption from God’s wrath and from its consequences, namely sin and death (the from aspect) and second glorification to sonship (the to aspect). In redemption, Christ rescues us from God’s wrath by offering himself as a ransom sacrifice. In glorification, he bring us into personal union (participation and communion into the divine life, 2 Pet 1:2; John 1:2-3) by giving us his own Spirit that of sonship, so that we may be adopted into the family of God. Therefore the indwelling of the Holy Spirit is a present-foretaste of our eternal inheritance. That is why scripture calls him ‘ἀρραβὼν  arrabonguarantee of our inheritance until we acquire possession of it, to the praise of his glory. Eph. 1:14’
 
Thus, salvation is not merely a rescue mission from eternal punishment, nonetheless that is an important aspect of our salvation, that is accurately reflected in one of the sub category of what it means to be saved namely, redemption. The Son of God came into this world for a mission. This mission is the source of our salvation, eternal life, a personal intimate knowledge of the father, through the Son, in/by the Holy Spirit and we experience this in the reverse order  (Eph. 2: 18 (Watch the reverse order in this text as we are on the receiving end))

Therefore, the mission of the Son as described in John 17 includes

  • Manifesting the being of the Father to his disciples, thus to us….

“I have manifested your name to the people whom you gave me out of the world. Yours they were, and you gave them to me, and they have kept your word.” (John 17:6)
“I made known to them your name, and I will continue to make it known, that the love with which you have loved me may be in them, and I in them.” (John 17:26)

  • Manifesting the life giving and sanctifying Words of the Father from the Son->Apostles->us…

For I have given them the words that you gave me, and they have received them and have come to know in truth that I came from you; and they have believed that you sent me. (John 17:7–8)
Sanctify them in the truth; your word is truth. (John 17:17)

  • Manifesting the Glory of both the father and the son by uniting us in Him through the personal presence of the Spirit (the role of the Spirit is reflected in John 14)

that they may all be one, just as you, Father, are in me, and I in you, that they also may be in us, so that the world may believe that you have sent me. The glory that you have given me I have given to them, that they may be one even as we are one, (John 17:21–22)

Salvation is a relational knowledge of God. In salvation, we are being elevated from our sinful status to a status of glory. The status of our glory was accomplished by the Son leaving the glory he had with the father eternally, which was intrinsic to his own person. He did this in order to do his father’s bidding to a lowly/ impoverished status that was foreign to his own person (John 17:19, Phil 2:9-11) and having accomplished His mission through the ignominious death on the cross, he was glorified in order to glorify the father by glorifying us.

“I glorified you on earth, having accomplished the work that you gave me to do.”“Father, the hour has come; glorify your Son that the Son may glorify you. ..and now, Father, glorify me in your own presence with the glory that I had with you before the world existed. (John 17:5)

Therefore, He prays that we may be one with the father and the son, that is personal union with the Triune God, and to see the glory of the Son.

Father, I desire that they also, whom you have given me, may be with me where I am, to see my glory that you have given me because you loved me before the foundation of the world.

 
In summary salvation is a personal-knowledge of the Triune God, an intimate union with the Father and the Son through his personal word (message) that he left us through the apostles and the personal indwelling presence of the Holy Spirit abiding in us.
 
Therefore, Eternal Life is knowing God, and Knowing God is what it means to have salvation. Those who are saved, do know God, and those who are not, do not. This is a salvation that you do not find in any other religious systems, but in biblical Christianity.

 

01: Salvation is 3D: Three-dimensional

First, salvation is a grand all encompassing reality.  Have you heard a comment as if salvation is merely the first initial deposit in our relationship with God? That is a common unfortunate misconception. Scripture however, presents salvation as God’s project for his creation, supremely for his image bearers. Therefore it has three dimensions and a fourth aspect. Salvation is a past event, present reality and future inheritance. These occur in light of Eternity, thus, salvation is Eternal.
Conventionally salvation is seen in its narrower sense. That is a one-time-past act of God by which we are made to be believers. This however is a description of justification (Rom 3:28; 5:1) rather than a full orbit description of what it means to be saved. In justification God declares us righteous before his royal court as if sin has never existed in us (Therefore, since we have been justified by faith, we have peace with God through our Lord Jesus Christ.). We have received righteousness as free gift as opposed to condemnation and death that were rightly deserved, Rom. 5:17; Rom 3:21; 9:30; 10:3–10; 2 Cor. 5:21; Phil. 3:9). It is a judicial act, that was done once for all (at least we protestant believe this, even though some of us would like to say a bit more of its future dimension). Our case before God’s holy court had not been adjourned for a future date (this would be the Catholic view) but it ended in Aquital. We are free! We are declared righteous on the basis of Christ’s scarifies on our behalf. As you can see however, this is only a past time event that occurred when we first believed in Christ. The word salvation, however, is described in several biblical metaphors such as: justification, divine calling, sanctification, regeneration, conversion, adoption, reconciliation, redemption, propitiation, expiation, glorification (Rom 8:30 “…he also called, and those whom he called he also justified, and those whom he justified he also glorified.”). etc. Every one of these capture something of what it means to be saved. Therefore Salvation is past, present and Future reality. See the following text describing the tenses of salvation.

When we were dead in our trespasses, made us alive together with Christ—by grace you have been saved (past)

Since, therefore, we have now been justified by his blood, much more shall we be saved by him from the wrath of God. Romans 5:9(future)

So then let us not sleep, as others do, but let us keep awake and be sober. For those who sleep, sleep at night, and those who get drunk, are drunk at night. But since we belong to the day, let us be sober, having put on the breastplate of faith and love, and for a helmet the hope of salvation. 1 Thessalonians 5:6–8(future)

Blessed be the God and Father of our Lord Jesus Christ! According to his great mercy, he has caused us to be born again to a living hope through the resurrection of Jesus Christ from the dead,  to an inheritance that is imperishable, undefiled, and unfading, kept in heaven for you, who by God’s power are being guarded through faith for a salvation ready to be revealed in the last time. 1 Peter 1:3–5  (future)

For the word of the cross is folly to those who are perishing, but to us who are being saved it is the power of God.1 Corinthians 1:18 (Present Continuous) [/column][column]

 

02: We Are already but not yet fully Saved….

Second, the New Testament describes our salvation with the following tension. On the one hand we already are that one day we will be. On the other hand we are not yet fully that which one day we will be. Many people make awful mistakes, not knowing the tension between what we are already and what we are fully yet to be. The church has seen such movements through out her history that misunderstood this tension, thus developed an imbalanced doctrines/ movements. The difference between these two tensions is a progressive work of God through the Holy Spirit transforming us to the image of the Son, Jesus Christ our Lord. But why? It is because Christ, the messiah, has already come, and he is yet to come the second time. Thus, already but not yet. See this:
 
Now John’s disciples and the Pharisees were fasting. And people came and said to him, “Why do John’s disciples and the disciples of the Pharisees fast, but your disciples do not fast?”  And Jesus said to them, “Can the wedding guests fast while the bridegroom is with them? As long as they have the bridegroom with them, they cannot fast.  The days will come when the bridegroom is taken away from them, and then they will fast in that day. No one sews a piece of unshrunk cloth on an old garment. If he does, the patch tears away from it, the new from the old, and a worse tear is made. And no one puts new wine into old wineskins. If he does, the wine will burst the skins—and the wine is destroyed, and so are the skins. But new wine is for fresh wineskins.” Mark 2:18-22

That is why this tension exists. Many of the so called Word-Faith movement preachers and their faithful followers have missed this New Testament tension. They say Jesus has come that we may be fully restored and have life to its fullest, thus prosperity. However, the problem is many read scripture in doses and never in context, thus they don’t seem to catch the fatal error of this movement. Contrarily, the NT stands at a radical middle position, why? It is because when Christ was personal present on earth, he inaugurated both the Kingdom and the new covenant in their real sense but not in their consummated sense. We still yet to experience death, but we have already overcome death (John 5:24). We are not under the power of sin already, but we do still sin and sin is yet to be removed completely from God’s people. The day will come when the bridegroom is taken away, then they will fast. This happened at the ascension of Jesus Christ the Lord of Glory when he was taken up to the right hand of Glory. That is to say, now we are living in this tension in which we are saved in its real sense, because He has already come and finished the work, but, he has yet to return one more time to fully consummate our salvation and render all powers nothing, (i.e. death, sin and Satan).

See what kind of love the Father has given to us, that we should be called children of God; and so we are (already). …Beloved, we are God’s children now, and what we will be has not yet appeared; but we know that when he appears we shall be like him, because we shall see him as he is.1 John 3:1–2 (ESV)
Because of this reality, we hold two realities in tension. The believer is in a lifelong struggle with the flesh (Romans 8:13). Let us look at two tensions in the New Testament. First the tension between ‘what we are made to be already and what we are obligated to be‘. Second, what we are now already and what we fully yet will be .

Law and Grace; Flesh and Spirit

Have you struggle with this paradox. We say “I know God asks me to obey him, but I am praying for God to give me strength” . ‘Actually, he is waiting for us to obey him!”, however, this is not legalism. In scripture, both legalism and libertinism or nominal Christianity (christian in name only) are condemned. These two groups were present in the church of Galatia. Some wanted to return to the legalism of Judaism, that highly prized itself in the works of the Law -Nomism, (Gal 3-4) and those that use the freedom that is in Christ as an opportunity for the flesh, antinomism (what Dietrich Bonhoeffer calls “cheap grace”) (Gal 5:13-15; Rom 6:1). Therefore, there is a tension between to obey but not to reduce it to legalism, and to celebrate our freedom in Christ but not to reduce it to mere easy believism, as if what we believe has no bearing in our lives whatsoever. Scripture presents salvation as freedom from slavery of sin to the freedom of belonging to Christ, to be slaves for Christ. The solution is life in the Spirit that is neither legalism nor easy-believism.  A friend of mine told me a story. He said at one time a lady refused to accept the Lord as her personal savior. So my friend’s friend, ask her to read the prayer at the back of the tracts. After she has done reading it, he declared her ‘saved’, while she was insisting for him to vanish out of her house. Therefore salvation is not signing a petition or merely “just pray after me this prayer” magic prayer. Therefore salvation is also described as a process of sanctification by which we actively participate with the Holy Spirit. This participation is our responsibility to obey Christ. That is why our christian progress is not a simple vertical line, going up. Rather It is a vertical line that is going up, alright, but falls up and down. For instance, take a look at this tension.

Therefore, my beloved, as you have always obeyed, so now, not only as in my presence but much more in my absence, work out your own salvation with fear and trembling, for it is God who works in you, both to will and to work for his good pleasure. (Philippians 2:12–13)

 If God is fully at work in us, to both will and to do (nothing is left) but why are we asked to work-out our own salvation with fear and trembling? How can these two go together? Please see the word ‘for’. It is causal. We are to workout our salvation precisely because he is working in us both to will and to do. In this sense, there is a tension between what is ours fully through grace in God’s sovereignty but what is yet to be ours fully through our obedience, which is our responsibility. Did you see that tension? How can you ask someone to do that which is done? How can you command someone to love, as though love is something to command? Here however, we see that God being 100% in charge and in control of our salvation-process (thus it is not 50/50%), but that does not mean we are excused from responsibility. We too are responsible 100%, but notice that we are not in charge. The two are not contradictory in God’s sight, though they seem so from our perspective. This is the tension you should be aware. Now that I mention it, you know exactly what I am talking about.
This tension is beautifully presented by Paul as follow:

“But by the grace of God I am what I am, and his grace toward me was not in vain. On the contrary, I worked harder than any of them, though it was not I, but the grace of God that is with me.”

Paul worked harder, it was his responsibility to do that his master order him to do, but yet it was not him, but God’s grace.

One more:

Your boasting is not good. Do you not know that a little leaven leavens the whole lump? Cleanse out the old leaven that you may be a new lump, as you really are unleavened {new lump}. For Christ, our Passover lamb, has been sacrificed. Let us therefore celebrate the festival, not with the old leaven, the leaven of malice and evil, but with the unleavened bread of sincerity and truth. 1 Corinthians 5:6–8

 God is commanding us to do that very thing that he is working in us through his grace. There is a real mirroring, that is going on from divine and human perspectives. We are imitating his inner working. Therefore, obedience is participating in (both our and our brothers’/sisters’) sanctification process. Remember there is no individualistic salvation. Salvation is communal. We need the body of Christ to grow. If you understand this paradox, that is the Christian experience. We strive for holiness for he is striving in us, yet the glory goes to him. Nevertheless, we are not mere robots. Our obedience is real. Our choices are real. They are not mere phantoms, or vapors. We are obeying him in the real sense of the word! Yet it is him and not us! Talk about paradox. We just have to live with it. He is wise.

 

To be and Yet to be: living in the tension

The other tension that we see in the NT is the tension between what we already and truly are but not yet completely. I believe in God’s healing power. I believe in the gifts of healing operating in the church today. I am a charismatic for heaven sake, (you should have seen me when someone prayed for me back in the days, oh sweet heaven. I used to storm the place! yes I am now embarrassed and came to learn as I mature, gifts are not all that central, Jesus is and they are unequally distributed anyways as the Spirit wills.) However, this is where the Word-Faith movement has failed us once again, in their heavy emphasis in the now at the expense of the hope of our future. No matter what, we are yet to die. Our hope is not in this life. Our hope is not riches, driving Cadillac, living in expensive house. It is not healing per se. Our hope is a physical resurrection hope in the new heaven and earth, our home of righteousness (2Pet 3:13)! That does not mean we don’t get this benefits now. I believe in God’s powerful presence among his people. (How many times one is healed, he would be sick on more time and die, unless Christ returns. All of those people that Jesus had healed or raised from the dead, 100% of them died again. So we should quite the imbalance by focusing on this worldly restoration, which hardly understand the New Testament at all.)They say “since Jesus paid for it, therefore you should have it fully”. If these preachers were correct, then I ask you “why do you still sin, If Jesus had paid the penalty for your sins?” Yes Jesus had paid the penalty in full, but we still do commit grievous sin. Is that because we don’t have faith? Or is that because we are not yet fully that which one day we will be? So there is a tension, not to commit sin, if we do John tells us that we have not seen him nor known him. But this same John knows what Jesus taught about the “not-yet”. Thus he says, “if we say we have no sin, we deceive ourselves…. if we say we have not sinned, his word is not in us…little children I am writing to you so that you may not sin…. but if anyone does sin, we have an advocate…” This tension that the New Testament presents helps us avoid these two extremes. We recognize God is at work with us, and divine healing is among us already,  but that does not mean we fully receive that which was ours until Christ returns. But we are receiving it now in measure. This is neither pessimistic nor optimistic. Someone said “pessimistic is atheistic, because God is in charge. Optimistic is naive for we live in a fallen world.” But we are Christians who are receiving the benefits of our salvation in the Spirit already and yet we await our Lord in the heavens, crying “Maranatha, Lord come!” He stills saves, and heals, but not always. Some of us will be resuced from sickness, persecution, poverty, some of us go through them faithfully to the end. (2 Corinthians 4:7-18; 1 Corinthians 7:29-31; 1 Corinthians 4:8-16 ) We all are yet to be completely healed on the day of resurrection. So I end showing you this tension from scripture, in case you are not convinced.
  • We have been saved (Eph 2:8) but we are yet to be saved (Rom. 5:9)
  • We have been sanctified (1Cor 6:11) but we are yet to be sanctified (1Thess. 5:23-24)
  • We are adopted as sons already (Rom 8:15), but we are yet to be sons (Rom 8:23)
  • We have clothed with he new man (Col. 3:9-11), yet we are to be clothed the new man (Eph. 4:21-24)
  • We have been redeemed, (Eph. 1:7) but we are yet to be redeemed (Rom 8:23)

 

                                    Not yet
Eternity Past               Now             Eternity
                       FutureProgressive

Living in light of the End

 Since all these things are thus to be dissolved, what sort of people ought you to be in lives of holiness and godliness, waiting for and hastening the coming of the day of God, because of which the heavens will be set on fire and dissolved, and the heavenly bodies will melt as they burn! But according to his promise we are waiting for new heavens and a new earth in which righteousness dwells. (2 Peter 3:11–13)

Leave a Reply

Your email address will not be published.