
009-010: በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንሆን ዘንድ – ኤፌ. 1:4 (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)
ክፍል ሁለት፦ [የምንባርከው] የመጀመሪያ ምክኒያት ስለመረጠንና ልጆቹ እንሆን ዘንድ አስቀድሞ ስለወሰነን ነው (ኤፌሶን 1:4-6)
1.1 ቅዱሳን እንድሆን ዘንድ መርጦናልና (1፡4)
[sz-ytvideo url=”https://www.youtube.com/watch?v=ONkZUWC39lg” theme=”dark” cover=”local” responsive=”y” autoplay=”n” loop=”n” fullscreen=”y” disablekeyboard=”n” disableiframe=”n” disablerelated=”n” delayed=”n” schemaorg=”n” /]
እግዚአብሔርን የምንባርክበት የመጀመሪያ ምክንያት፡- አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና[καθὼς ἐξελέξατο ἡμᾶς ἐν αὐτῷ πρὸ καταβολῆς κόσμου]
- ከቁጥ.4-14 ድረስ ለምን እ/ር እንደሚባረክ ምክኒያቱን ይሰጣል።
- ምርጫ ከብሉይ ጀምሮ የተገለጠ የእ/ር አሰራር ነው::
- ግለሰቦችን፡- አብርሃም (Neh. 9:7); አሮን Ps. 105:26; ዳዊት 1 Kings 11:34; Ps. 78:70 የኤሊ አባት 1 Sam 2:28
- ያዕቆብ/እሥራኤል Isa 41:8; 44:1-2; Deut. 7:7; 10:15; 14:2 (ርስቱ ይሆን ዘንድ)
- ክርስቶስ የተመረጠ ልጅ ነው (Luke 9:35): ከላይ ላሉት ሰዎች መዳንን ይወርሱ ዘንድ የመረጣቸው ሲሆኑ ክርስቶስ ግን መዳንን ያመጣ ዘንድ የተመረጠ ነው።
- ምርጫምርጥ የሆኑ ሰዎች ገንዘቡ ማድረጉን አያሳይም። ዓላማውም ለእ/ር ክብር ነው
- እሥራኤልን በአብርሃም ሲመርጣት ዓላማው ክብር ታመጣለት ዘንድ ነበር (Is. 60:21; 61:3; Jer. 13:11)
- ይህ የክብሩ መገለጥ መካከለኛ ከመሆኑ የተነሳ ፍርዱን ሲያመጣ እንኳ በፍርዱ ውስጥ ሰዎችን ወደ ንስሓ ለመጥራትም ጭምር ነው (Ex. 7:5; Amos 4:6)
- የተመረጥነው በእርሱ ነው፦
- ይህ የሚያሳየን በመጀመሪያ ዓለም ወደ መሆን ሳይመጣም ክርስቶስ አስቀድሞ ነበረ፤ ቅድመ-ሕላዌ። አብ የመምረጥን ሥራ ሲሰራ ወልድም በዚህ ሥራ ተሳትፏል። ያለ ክርስቶስ አብ ይህንን ሥራ አልሰራም። ሆኖም ግን አገላለጹ ‘በኩል የሚለውን ያንጸባርቃል።
- ፍጥረት በክርስቶስ በኩል እንደተፈጠረ ሁሉ (col 1:16; John 1:3)
- John 17: 24 “አለም ሳይፈጠር በፊት የተወደደ ልጅ ነበር”
- ጴጥሮስም ይህንን እውነታ አለምን በልጁ በኩል እንዴት እንደሚያድን አስቀድሞ እውቀቱ ይናገራል። 1 Pet: 1:20
- መዝሙረኛውም ሲናገር 74:2
- 13:8
- ይህ የሚያሳየን በመጀመሪያ ዓለም ወደ መሆን ሳይመጣም ክርስቶስ አስቀድሞ ነበረ፤ ቅድመ-ሕላዌ። አብ የመምረጥን ሥራ ሲሰራ ወልድም በዚህ ሥራ ተሳትፏል። ያለ ክርስቶስ አብ ይህንን ሥራ አልሰራም። ሆኖም ግን አገላለጹ ‘በኩል የሚለውን ያንጸባርቃል።
የምክኒያት 1 ዓላማ 1፦ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን[εἶναι ἡμᾶς ἁγίους καὶ ἀμώμους κατενώπιον αὐτοῦ]
- የምርጫ ዓላማ ቅድስና ነው። (κατενώπιον αὐτοῦ) ይህ በብሉይ ከግብጽ የዋጀውን ህዝብ ለምን እንደዋጀው ሲናገር እርሱ ቅዱስ እንደሆን ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ እንደ ነበር ነው ( 11:44; 1Pet 1:16; Eph. 4:1) የጳውሎስም ሐዋርያዊ አገልግሎት በክርስቶስ ሰዎችን ያለነቀፋ አድርጎ ማቅረብ ነው። Col. 1:21
- ቤተክርስቲያን ያለነውር ሆና ትቀርብ ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል ( 5:27)
- ከዚህ የተነሳ ምንም እንኳ ሐዋሩያው ቅዱሳን በቅድስና እየጨመሩ እንደሚሐኢዱና እለት እለት የለውጥ ሒደት እንደሚካሐድ፤ ገና ወደ ፊት ሙሉ በሙሉ እንደሚልቀደሱ ቢያስተምርም፤ አሁን ግን ይህ ስያሜ አማኞች ገንዘባቸው ሆኗል። የዚህም ምክኒያት አማኞች ያደረጉት ሳይሆን የእ/ር ምርጫ ነው። ምርጦች ስለሆንን ሳይሆን ሐጥያተኛውን ስለመረጠ። 1:1, 15, 18; 2:19; 3:8, 18; 4:12; 5:3; 6:18
[ይቀጥላል]
ምክኒያት 1 ዓላማ 2፦ [በ]ፍቅር [በ]ክርስቶስ ኢየሱስ ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን [ἐν ἀγάπῃ, 5 προορίσας ἡμᾶς εἰς υἱοθεσίαν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ εἰς αὐτόν]

