
የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ
እነዚህ በተከታታይ ለ8 ሳምንታት ‹የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ› በሚል ርዕስ ለካንሳስ የክርስቲያኖች ሕብረት ቤተ ክርስቲያን ላሉ የማቴቴስ ተማሪዎች ያቀረብኩት ነው።
ማቴዎስ የፍጻሜ መጽሐፍ ነው። ማቴዎስ ኢየሱስን የእሥራኤልን ጥሪ፣ ተሥፋና ተልዕኮ ተላበሶ እንደ ተወለደ ያቀርብልናል። ስለዚህ ኢየሱስ እውነተኛ እሥራኤል ነው። የእሥራኤልን መሢሃዊ ዘር ወርሷል፣ የተለያዩ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችንና ጥብብቆሽን ወደ ፍጻሜ አድርሷል። ይኽም፣ ማቴዎስ “እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ” የሚለውን ቀመር 11 ጊዜ በመደጋገም የወንጌሉን ትኩረት ያሳየናል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ ነው (2:2)፣ የተሰቀለውም የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ ነው (27፡54)። ሲወለድ፣ ሲጠመቅና በክብር ሲለወጥ “ልጄ እርሱ ነው” ተብሏል – ይኽም የዳዊት ተስፋ ፍጻሜ መሆኑ ነው። ምድራዊ አገልግሎቱ ያተኮረው በጠፉት የእስራኤል በጎች ላይ ነበር (10:6)። የአወላለዱ ሁናቴ እንደ ኢሳ 7:14 ከድንግል የተጸነሰ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔርን መገኘት የሚያማክል “አማኑኤል ነው” (12:6; 26፡29; 28፡20)። በተጨማሪም ማቴዎስ ኢየሱስን የኢሳያሱ ሥቅዩ ባሪያ እንደሆን ያሳያል (20፡28)። የኢየሱስ የፈውስ አገልግሎት የባርያው አገልግሎት ነው (8፡17)፣ የደረሰበት ተቃውሞ በባርያው ላይ ይደርሳል የተባለው ተቃውሞ ነው (12፡17-21)። በተጨማሪ፣ ኢየሱስ እሥራኤልን ማንነትና ተስፋ መላበሱን የሚያሳየን ማስረጃ፣ የኢየሱስ ትምህርት የብሉይ መጻሕፍትን ሙሉ ሥልጣን ታሳቢ ማድረጉ ነው – የመጣው ሕግና ነቢያትን ለመሻር ሳይሆን ለመፈጸም ነው (5፡17-48)።
ምዕራፍ 1፡ የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ (መቅድም)
ምዕራፍ 2፡ የእሥራኤል ትራኬና ኢየሱስ
አዲስ ኪዳንን ታሪካዊ ዳራ ከእሥራኤል ትራኬ እና ከክርስቶስ ትራኬ ጋር ያለውን ዝምድና ያስገነዝባል።
ምዕራፍ 3፡ አይሁድ በፋርስና በግሪክ ዘመነ መንግሥት
የአይሁድን የሁለተኛውን መቅደስ ታሪክ ከዘመነ ፋርስ አንስቶ እስከ ግሪክ እንዲሁም እስከ ዘመነ ሮም ድረስ ይዳስሳል። እንዲሁም በሐዝሞናውያን ሥርወ-መንግሥት የአይሁድን የምዕተ-ዓመት የራስ አገዛዝ ያስቃኛል። በተጨማሪም፣ በእያንዳንዱ ክፍለ-ዘመን የተከናወኑትን አውራ ክዋኔዎችን ያቀልማል። ለምሳሌ ያኽል፣ በዘመነ-ፋርስ፣ የምኹራብ፣ የአባቶች ትውፊትና የአረማይስጥ ቋንቋ መዳበር፣ በዘመን ግሪክ፣ የግሪክ ባህል ንቅናቄ መስፋፋት (ሔለናዊነት)፣ የሰብዓ-ሊቃናት የብሉይ ኪዳን ትርጉም መጻፍ ወዘተ…
እርማት፡ 49/50 – 100 ዓ.ም. የሚለው በ44/45 – 100 ዓ.ም ተብሎ ይታረም፡፡
ምዕራፍ 4፡ የአይሁድ ትእምርታዊው ዓለም (ተጽእኖ ፈጣሪ መጻሕፍት፣ እንቅስቃሴዎችና ሰዎች)
ምዕራፍ 8፡ 2 ቆሮንቶስ
ምዕራፍ 9፡ 1 እና 2 ተሰሎንቄ
ምዕራፍ 10፡ አራቱ የእሥር መልእክታት


ምዕራፍ 6፡ ሮሜ 6:1-23
ምዕራፍ 7፡ 1 ቆሮንቶስ