
የብሉይ ነቢያት ጥሪ፣ መልክዕክት እና መጻሕፍት
ይህ ትምህርት ከጥቂት ወራት በፊት “የነቢያት ጥሪ፤ መልዕክት እና መጻሕፍት” በሚል ርዕስ ስለ ብሉይ ትንቢት መጻሕፍት ወደ 4.5 ሰዓት የፈጀ ትምህርት ለዴንቨር የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት LIVE ያስተማርሁት ነበር። አስቀድሜ ይህንን ትምህርት እንዳስተምር የጋበዘኝን ፓስተር ኤርሚያስ አማኑኤልን ከልብ እያመሰገንሁ ሌሎችም ትምህርቱን ማዳመጥ እንዲችሉ በማሰብ እንደገና ተቀድቶ፤ አሁን ከጥናት ጹሑፍ ጋር በአንድ ላይ ተቀናብሯል።
❝እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ። ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ልታውቁ ይገባችኋል፤ በመጽሐፍ ያለው የትንቢት ቃል ሁሉ ማንም ሰው በገዛ ራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤ ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም❞
2 ጴጥሮስ 1:19-21)
There are 28 clips in this playlist, about 3.5hrs of video.

