Video Posts,  ምጋቤ መልእክታት

 የምጋቤ መልእክታት አጠቃላይ ጭብጦች

  1. ከቀርጤስ ባህል አርነት ያልወጡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና እውነተኛ የወንጌል ባለ ዐደራነት (ቲቶ)
  2. የኤፊሶን የህግ መምህራንና በ እግዚአብሔር ቤት የመኖር ዓላማ (1 ጢሞቴዎስ)
  3. የታምኝነት ጥሪና የማፈግፈግ አደጋ (2 ጢሞቴዎስ)

ጢሞቴዎስ

  • በእናቱ አይሁዳዊ በአባቱ ደግሞ ግሪክ ነው (ሐዋ 16:1)
  • ያልተገረዘ በመሆኑ በአይሁድ ዘንድ ለነበረው ተልእኮ እንቅፋት እንዳይሆን ጳውሎስ ይገርዘዋል
  • 1ኛ እና 2ኛ ጢሞቴዎስ በሚጻፉ ሰዓት፣ የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር

ቲቶ

  • እንዲሁ የጳውሎስ ቅርብ የወንጌል ባልንጀራ ነበር (ቲቶ 1:4)
  • ግሪካዊ በመሆኑ፣ አይሁድ ክርስቲያኖች እንዲገረዝ ግድ በማለታቸው፣ ጳውሎስ ይቃወማል
  • ጢሞቴዎስና ቲቶ፣ የጳውሎስን የወንጌል ስትራቴጂ ማሳያ ናቸው።

ቲቶ በቀርጤስ

  • ቲቶ ከጳውሎስ ጋር አብሮ ከመጓዙ በፊት በቀርጤስ ይኖር ነበር
  • ቀርጤስ ከግሪክ ደሴት ሁሉ ስመ ጥር ደሴትና እውቅ ወደብ ነበረች። እንዲሁም የቀርጤስ ንጉሥ በተረት-መሰል ዝናው ታዋቂ ነበር (260-1100 ቅልክ.)
  • ከሁሉ በላይ፣ የቀርጤስ ሰዎች በአጭበርባሪነታቸውና በስንፍናቸው የታወቁ እንደ ነበሩ የግሪኩ የ7ኛው ክፍለ ዘመን ጸሐፊ የነበረው ኤፒመነንደስ (Epimenides) ይገልጻቸዋል። ጳውሎስም ይጠቅሰዋል።

በኤፌሶንና በቀርጤስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ትልቅ ችግር ነበር

  • አንዳንድ “የሕግ መምህራን” ነን የሚሉ አማኞችን እያማለሉ “በተረትና በአይሁድ ትውልድ” ምርምር ሰለባ እንዲሆኑ ምክንያት ሆነዋል (1 ጢሞ 1:6–7) ።
  • “መምህራን ነን” ቢሉም ግን መምህር ለመሆን የሚያስፈልገውን መመዘኛ ያሟሉም (6-7)
  • ይህ ትምህርት የወንጌልን ይዘትና ቅርጽ የሚበርዝ፣ ከሰይጣንና ከስግብግብነት የመነጨ ነው (1 ጢሞ 1:4; 6:3–5; 2 ጢሞ 2:14–16, 23; 3:13; ቲቶ 1:10, 14; 3:9)

ይህ እንግዳ ትምህርትከሚከለክላቸው መካከል

  • ትዳርን ይከለክላል፣
  • የተወሰኑ ምግቦችን ርኹስ ያደርጋል፣
  • “በእውቀት\ግኖሲስ” አንድ ሰው ከምድራዊ ሰውነት መጥቆ፣ ሙታን ትንሳኤ ሊደርስ ይችላል (2 ጢሞ 2:18)

1 ጢሞቴዎስ

  • መክፈቻ (1: 1– 2)
  • ለጢሞቴዎስ በግል የተሰጠ አደራ፡ በኤፌሶን ስላሉ የሐሰት መምህራን  (1: 3– 20)
  • ለጉባኤው የተሰጠ መመሪያበእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው አንድነትና ሥርዐት  (2: 1– 3: 16)
    • ስለ ጸሎት (2: 1– 8)
    • በአምልኮ ሰዓት ወንዶችና ሴቶች (2: 9– 15)
    • የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መመዘኛ (3: 1– 13) ሽማግሌዎች (3: 1– 7) ዲያቆናት(3: 8– 13)
  • ለጢሞቴዎስ በግል የተሰጠ ተጨማሪ አደራ (4: 1– 6: 2a)
    • ስለ መጨረሻው ዘመን የስህተት መንገድ (4: 1– 5)
    • መልካም የክርስቶስ አገልጋይ ስለመሆን (4: 6– 16)
    • በቤተኡ ውስጥ ስላሉ ስለተለያዩ የእድሜ ክልል ባሉ ሰዎች እንዴት መያዝ እንዳለባቸው
    • የመጨረሻ የወንጌል ዐደራ (6: 2b– 19)
  • መዝጊያና ስንብት(6: 20– 21)

2ኛ ጢሞቴዎስ

  • መግቢያ/ሠላምታ –    [1:1 – 1:5]
  • የደብዳቤው ይዘት መግቢያ፡ በግል የቀረበለት ማበረታቻ [1:6 – 18]
    • መከራን የመቀበል ጥሪ          [1:6 – 14]
    • ታማኝ ሆኖ የመገኘት ግዴታ    [1:15 – 18]
  • የደብዳቤው ይዘት እምብርት፡ እንዴት ማገልገል እንዳለበት [2:1 – 4:8]
    • እውነተኛ አገግሎት፤ ወንጌል እና ታማኝነት [2፡1-26]
    • ሦስት የአገልግሎት ዘይቤዎች [2:1 – 7]
      • ወታደር (2:4)
      • ስፖርተኛና (2:5)
      • ገበሬ (2:6)
    • ወንጌል እና የሚጠይቀው ታማኝነት [2:8 – 13]
    • ሦስት ተጨማሪ የአገልግሎት ሚናዎች [2:14 – 26]
      • ትጉ ሰራተኛ (2:14–19)
      • የተሰናዳ ዕቃ (2:20-21)
      • የጌታው አገልጋይ (2:22-26)
    • ተጨማሪ ማበረታቻ ቃሎች [3:1 – 4:8]
      • የኋለኛው ዘመን ክህደት (3:1 – 9)
      • የመጽናት ግዴታ (3:10 – 17)
    • የደብዳቤው ይዘት መዝጊያ፡ ቃሉን ስበክ [4:1 – 8]
  • የመዝጊያ ስንብት [4:9 – 22]

የምጋቤ መልእክታት አጠቃላይ ነገረ-መለኮታዊ መልእክት

  • እውነተኛ አስተምህሮ ትኹረት
    • ጤናማ ሊሆን ይገባዋል (1 ጢሞ 1:9-10) – በቁስል የተመታ ጋር ይነጻጸራል (2 ጢሞ 2:17-18)
    • እውነት ሊሆን ይገባል (1 ጢሞ 3:15; 2 ጢሞ 2:15)
    • ከወንጌል ጋር የሚስማማ
    • ከኢየሱስ ትምህርት ጋር የሚስማማ
    • ከብሉይ ኪዳን ጋር ሥሙር ነው
    • በአደራ የተሰጠ በአደራ የሚጠበቅ ነው
  • እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር (1 ጢሞ 3፡16)
    • እውነትን በመልካም ሥራና በመልካም ኑሮ የሚገልጥ (1 ጢሞ 4: 7, 15; 2 ጢሞ 3: 16; ቲቶ 2: 12)
  • ቤተ ክርስቲያን (1 ጢሞ 3:15)
    • ዘይቤ ፩ – ቤተ/ያን የእውነት አምድና መሰረት
    • ዘይቤ – ቤተ/ያን የእግዚአብሔር ቤተሰብ
    • ቤተ/ያን አደረጃጀቷና አገልግሎቷ
      • የቃሉ አገልግሎት (እውነት አእማድ)
      • የእንክብካቤ አገልግሎት (ቤተሰብ)
      • የጸሎት አገልግሎት
  • ስለ እግዚአብሔር አብስለ ኢየሱስስለ መንፈስ ቅዱስ እንዲሁም ስለ ድነት ያስተምራል (God & Salvation)
  • ስለ ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮና ስለ ዘመን ፍጻሜ (Mission & Last Days)

Leave a Reply

Your email address will not be published.