
የመምሰል ጥሪ! (Virtue Formation)
- እንደ የዋህ ሕፃን ቀጥተኛ፣
- እንደምታጠባ እናት አፍቃሪ፣
- እንደ ባለሥልጣን አባት መካሪ
የምንባብ ክፍል 1 ተሰ 1:2-2፡13
መግቢያ
ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚገነባው እንዴት ነው? ሲጀመር፣ “መንፈሳዊነት” ምን ማለት ነው? “መንፈሳዊ” የሚባሉ ተግዳሮት የትኞቹ ናቸው? ከሆኑ ለምን? ካልሆኑስ ለምን? ለምሳሌ ያህል “ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ስትወስዱ፣ መንፈሳዊ ተግዳሮት ነው? ከሆነ ለምን? ክላሆነስ ለምን? ሥራችሁ ገበታ ቁጭ ብላችሁ “Clock-In” ስታደርጉ መንፈሳዊ ነው? ጳውሎስ ለምንድር ነው “ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና።” የመንፈሳዊነትን ትርጓሜ የሚሰጠን ማን ነው? የትኛው ቤተ እምነት? ብዙ አሉን። የየትኛውስ አስተማሪ? ብዙ አሉን። ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ አያሌ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን አይታለች። ነገር ግን ቆም ብለን፣ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምን እያደረጉ ይመስለናል? አዲስ ኪዳን ቅመማቅመም፣ እኛ ደግሞ ምርጥ ሼፍ የሆንን እንዳይመስለን ልንቆጠብ ያስፈልጋል። አዲስ ኪዳን የሚናገረው በሙሉ፣ ጳውሎስ በደብዳቤያቱ የሚጽፈው በሙሉ ስለ መንፈሳዊነት ነው። ሥሉስ አምላክ በዘመናት መካከል በብዙ ጎዳና መንገድ የቀመውና ያዘጋጀው፣ በዘመን መጨረሻ በልጁ ያበሰለው ሕይወት ነው። ስለዚህ የእኛ ተቀዳሚ ምና አድማጭ መሆን ነው። አሊያ በራሳችን አይን ጠቢባን እንዳንሆን እግዚአብሔር ይጠብቀን። ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ አንዳንድ ቃሎችና አገላለጾች በቅዱሳት መጻሕፍት አውድ ሥር አዎንታዊ ዕሳቤ ይኖራቸውና፤ በዘመናችን አውድ ሲዛመዱ ግን አሉታዊ እንደምታ ያላቸው ቃሎችና አገላለጾች አሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ “መምሰል” የሚለው ቃል ነው።
ዘንድሮ መምሰል አሉታዊ ድምጽ አለው። ራስህን ሁን! ራስህን ተቀበል። ለየት እንድትል ግላዊ ማንነትህን ከስት (Personal Branding)። የተኮረጀ ብዙ እቃዎች አሉ በተለይ በቻይና የተመረቱ (Issue of Originality vs. imitation)። ሆኖም ርካሽ ኮፒ እንዳለ ሁሉ ርካሽ–ኦሪጂናልም አለ። መንፈሳዊነት የሚወረስ እውነታ ነው። የኢየሱስ ሕይወት ነው። የሚቀሰም ሕይወት ነው። ጌታውን ለረጅም ዓመታት ሲከተልና ሲመስል የኖረ ደቀ-መዝሙር፣ ለጋ የሆነውን ደቀ-መዝሙር “ተመልከት ኢየሱስን፣ ተመልከት የኢየሱስን ሕይወት፣ ተመልክተኝ እንዴት በፈተና እንደምጸና፣ ተመልክተኝ በስድብና በንቀት ውስጥ ውርደት ክብሬ እንደሆነ። እየኝ ሚስቴን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን በመስዋዕትነት እንዴት እንደምወዳት፣ ተመልከቺኝ ባሌን እንዴት በአክብሮት እንደምወደው፣ እይ ልጆቼን በጌታ ፍርሃት እንደማሳድግ…ተመልከት ኢየሱስን!
ጌታን መከተል ማለት አንዱ የመምሰል ጥሪ
ችግሩ ሌሎችን መምሰላችን ሳይሆን፣ ሳንሆን መምሰላችን ነው። ስንለወጥ መኮረጃችን ነው። ውስጣችንና ውጪያችን ሲገለበጥ የተለያየ ፊት ያሏቸው መሆናቸው ነው! (“ነገር ግን ወንጌልን በዐደራ ለመቀበል እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ እንደ ቈጠራቸው ሰዎች ሆነን እንናገራለን። ይህንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን እንጂ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት ብለን አይደለም። የሽንገላ ቃል ከቶ እንዳልተናገርን ወይም ሥሥትን ለመሸፈን ብለን አስመሳዮች እንዳልሆንን ታውቃላችሁ፤ ለዚህም እግዚአብሔር ምስክራችን ነው።”)
- “ስለመስላችሁ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን”
- (1:6) “ደግሞ ስለ እናንተ ስንል በመካከላችሁ እንዴት እንደኖርን ታውቃላችሁ። እናንተ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ”
- የይሁዳ አማኞችን መምሰላቸው (2:14)
- “ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን በይሁዳ የሚገኙትን የእግዚአብሔርን አብያተ ክርስቲያናት መስላችኋል፤”
- 2 ተስ 3:7, 9 “የእኛን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደሚገባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና። ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ ሥራ ፈቶች አልነበርንም…ይህን ያደረግነው ምሳሌነታችንን እንድትከተሉ ብለን እንጂ የሚያስፈልገንን ነገር ከእናንተ ለማግኘት ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።”
- የአዲስ ኪዳን ምስክርነት
- 1 ቆሮ 4፡16 “ይህን የምጽፍላችሁ እንደ ተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ብዬ አይደለም። ምንም እንኳ በዐሥር ሺህ የሚቈጠሩ ሞግዚቶች በክርስቶስ ቢኖሯችሁም፣ ብዙ አባቶች ግን የሏችሁም፤ በወንጌል አማካይነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወልጄአችኋለሁና። ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።”
- 1 ቆሮ 11:1 “እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ።”
- ፊል 3፡17-18 “ወንድሞች ሆይ፤ የእኔን አርኣያነት በመከተል ከሌሎች ጋር ተባበሩ፤ እኛ በሰጠናችሁ ምሳሌነት መሠረት የሚኖሩትንም አስተውሉ። ምክንያቱም ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደ ነገርኋችሁ፣ አሁንም እንደ ገና፣ ያውም በእንባ እነግራችለሁ፤ ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ።
- 1 ጢሞ 4:12 “ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።”
- 2 ጢሞ 1:13 “ከእኔ የሰማኸውን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር፣ የጤናማ ትምህርት ምሳሌ አድርገህ ያዝ። የተሰጠህን መልካሙን ዐደራ፣ በእኛ ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።”
- ቲቶ 2:7 “በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስ ተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣ የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገር አሳይ፤”
- 1 ጴጥ 5፡3 ሽማግሌዎች፣ እረኞች)…[ስትመሩ] በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን።”
፩ – አርአያዊ መሪነትና አገልግሎት በሚያፈራው የታማኝነት ፍሬ ይገለጣል [Faithful] (1:2-10)
- የምሥጋናው ቀጥተኛ ምክንያት (1:3) – የተሰሎንቄ አማኞች እምነት፣ ፍቅርና ተስፋ
- የምሥጋናው መሠረታዊ ምክንያት (1:4) – የተሰሎንቄ ሰዎች በእግዚአብሔር መወደድና መመረጥ
- የምስጋናው ተጨማሪ ምክንያት (1፡6-10)
- የተሰሎንቄ አማኞች አርአያዊ ሕይወታቸው (1፡6-7)
- የተሰሎንቄ አማኞች የተመሰከረ ሕይወታቸው (1፡8)
- የተሰሎንቄ አማኞች የተለወጠ ሕይወታቸው (1፡9-10)
፪ – አርአያዊ መሪነትና አገልግሎት በሐቀኝነት መመላለስ ነው (2:3 – 7)
2፡3-7“የምናቀርበው ልመና ከስሕተት ወይም ከክፉ ዐላማ ወይም እናንተን ለማታለል ከመፈለግ የመነጨ አይደለም። ነገር ግን ወንጌልን በዐደራ ለመቀበል እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ እንደ ቈጠራቸው ሰዎች ሆነን እንናገራለን። ይህንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን እንጂ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት ብለን አይደለም። የሽንገላ ቃል ከቶ እንዳልተናገርን ወይም ሥሥትን ለመሸፈን ብለን አስመሳዮች እንዳልሆንን ታውቃላችሁ፤ ለዚህም እግዚአብሔር ምስክራችን ነው። ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ከማንም፣ ከሰው የሚገኝ ክብር አልፈለግንም። የክርስቶስ ሐዋርያት እንደ መሆናችን መጠን ሸክም በሆንባችሁ ነበር…2:10 “በእናንተ በምታምኑት መካከል ሳለን እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅ እንዲሁም ያለ ነቀፋ ሆነን እንደኖርን እናንተም እግዚአብሔርም ምስክሮች ናችሁ።”
- መዘንጋት የሌለብን ወንጌል የሚለተላለፈው በህያዋን ምስክሮች ነው። ሂሳብ አይደለም፣ ስሌትን ማስተማር፣ ባይሎጂም አይደለም።
- በመልክተኛውና በመልክቱ መካከል ቅርብ ግንኙነት አለ (close connection between the messenger and the message)
- አቀባዩን ማቆሸሽ መልእክቱን ማቆሸሽ ነው፣ መልክተኛውን ማጠልሸት መልክቱንም ማጠልሸት ነው። መልክተኛው መልክት አይደለም። ኢየሱስ ብቻ መልክተኛውም (ከዮናስ የሚልቅ በዚህ አለ) መልክትም (በመጀመሪያ ቃል ነበር) ነው።
- ለዚህን ነው ጳውሎስ ስለ ራሱና ስለ አገልግሎቱ ምካቴ የሚሰጠው ስለ መልእክቱ ግድ ስለ ሚለው ነው። ነቀፌታን መመከት አስፈላጊነቱ ይህ ነው።
- በውጪ ያሉት (የተሰሎንቄ ኗሪዎች) በጳውሎስ ላይ የሰነዘሩት የማጠልሸት ዘመቻ ነበር።
፫ – አርአያዊ መሪነትና አገልግሎት ሌሎችን ይንከባከባል (2:7 – 10
- ለቀረበበት ክስ ምላሽ – ጳውሎስ ሦስት የቤተሰብ ዘይቤያት ይጠቀማል። አካሔዱ በወንጌል ንጽህና እንደሆነ ለማስገንዘብ
- ሕጻን
- የምታጠባ እናት
- አባት
-
[1] ሕጻን ዘይቤ –
- “2፡7 እኛምበመካከላችሁበየዋህነት [በሕፃንነት] ተመላለስን።”
- ቅንነት፣ ንጽህና የዋህነት ያመልክታል – ተንኮለኞች፣ ጠመዝማዞች አልነበርንም።
- የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ወይም አርአያ የሚሆኑ አማኞች ሁሉ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ነበር አለ፦ የምናደርገውን የምናደርገው ለምንድር ነው? ልባችንን መመርመር አለብን። ለዝና ለስም እና ታዋቂነት? ለግል ጥቅም? ለከንቱ ውዳሴ ነው? ወይስ “ታማኝ ሆኖ ለመገኘት” ሰዎችን በመሸንገል በማቆለጳጰስ የግል ፍላጎታችንን ለማርካት አይሁን። ጳውሎስ ምካቴ ሲያቀርብ፣ “በመካከላችሁ እንደ ሕፃን ነበርን” ይላል።
- ስለዚህ አገልግሎታችንና ሕይወታችን አር አያ እንዲሆንና በጌታም ፊት ዋጋ እንዲኖረው፣ አካሔዳችን ሁሉ የወንጌልን ንጽህና ያንጸባርቅ
-
[2] የምታጠባ–እናት
- “ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ከማንም፣ ከሰው የሚገኝ ክብር አልፈለግንም። የክርስቶስ ሐዋርያት እንደ መሆናችን መጠን ሸክም በሆንባችሁ ነበር፤ ነገር ግን እናት ልጅዋን እንደምትንከባከብ እኛም በመካከላችሁ በየዋህነት ተመላለስን”
- ለተሰሎንቄአውያን እናት ብቻ ሳይሆን – የምታጠባ እናት ሆኗል። ሰጪ ፍቅሩን ያቀልማል። መጋቢ እንጂ ተመጋቢ አልነበረም። አገልግሎታችን በፍቅር የተቃኘ ሊሆን ይገባል።
-
[3] የአባት ዘይቤ – 2:11 “
አባት ለገዛ ልጆቹ እንደሚሆን እኛም ለእያንዳንዳችሁ የቱን ያህል እንደሆንን ታውቃላችሁና፤ ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ አበረታታናችሁ፤ አጽናናችሁ፤ አጥብቀንም ለመንናችሁ።”- ሕፃን = ንጹህ ዓላማን፣ እናት = ፍቅር እንዳመለከተ፣ አባት ደግሞ ሥልጣንን ያመልክታል።
- በጳውሎስ ዘመን አባቶች የነበራቸው ሥልጣን ፍጹም ነበር።አርጣጣሊስ “አባት በቤቱ ላይ እንደ አምላክ ነው…እንደ ንጉሥ ነው” ይላል።
- ጳውሎስ እንደ አባት ሥልጣኑን ለገዛ ጥቅሙ አልተጠቀመም “ለእያንዳንዳችሁ የቱን ያህል እንደሆንን ታውቃላችሁና”
- አገልጋይነት ሥልጣን (1) አምባገነን ሥልጣን (Dictatorial leadership) አይደለም – ሥልጣኑ ሌሎችን ለማነጽ እንጂ በሌሎች ላይ ለመስልጠን አይደለም (2) የብዙኀን ሥልጣንም (Egalitarian leadership) አይደለም – 5፡12-13)።
መዝጊያና ተዛምዶ
በውጪ ባሉት ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ምስክርነት ምንድር ነው? አስመሳዮች ናቸው? አጭበርባሪዎች ናቸው? ሰው ተጠቃሚዎች ወይ ራስ ተጠቅም ናቸው? ገንዘብ ወዳጆች ናቸው? ዘረኞች ናቸው? What they say about us either diminish our testimony about Christ or increases our effectiveness in our mission.
- ወንጌልን በተመለከተ የአገራችን ዘዬ “ስለ ሰው ቀድጄ ልልበሰው” አይሰራም። በአንጻሩ ደግሞ “ሰው ምን ይለኛል?” በሚል ይሉኝታ ም አይደለም።
- ይልቁንስ በውጪ ባሉት ዘንድ፣ ለቤተ ክርስቲያን ስለ ስሟ ልንጠነቀቅላት የሚያስፈልገው፣ ለመልእክቷ ስለምንጠነቀቅ ነው። ይኽም ራስን በመከላከልና መልክታችንን እንዳይነቀፍ በመከላከል ልዩነት አለ። እያታለልን፣ እየሰረቅን፣ እየዋሸን…ወዘተ ምካቴ ማቅረብ አታለን ወንጌልን ከማስነቀፍ የባሰ ክፉ ነው።

