ኦሪትና ሥነ-አፈታታዊ መርሆው
ይህ በዴንቨር የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ለደቀ መዛሙርት ሥልጠና በሥነ-አፈታት ክፍለ ግዜያቸው የቀረብኩት ትምህርት ነው።
ክፍል 1፡ የሲናው ሕግ እንዴት ይነበብ፤ እንዴትስ ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት ይዛመድ?
- ▶️ በኦሪት-ኪዳን እና በአዲስ-ኪዳን መካከል ያሉት ሥነ-አፈታታዊና አፈጻጸማዊ ውጥረቶች (The Relationship between Law and Gospel: A Hermeneutical Problem) ይህ ‘የሲናው ኪዳን መመሪያ ለክርስቲያናዊ ሕይወት’ በሚል ርዕስ ለዴንቨር ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በሥነ-አፈታት ክፍለ ግዜያቸው ብቅ ብዬ ካስተማርኩት የወሰድኩት የመጀመሪያው ክፍል ነው።
- ▶️ አዲሱ-አመለካከት እና የሕግ ሥልሳዊ-ክፍፍል አመለካከት (The New Perspective and the Tripartite Distinction of the Law) በዚህ ቪዲዮ በኦሪት-ኪዳንና በአዲስ ኪዳን መካከል ላለው ውጥረት እልባት ለመስጠት ከቀረቡት አመለካከቶች መካከል የሉተራንን፣ የተሐድሶአውያንን፣ የአዲሱን-አመለካከት በአጭሩ ተመልክተናል። በተለይ ኦሪትን
- ምግባራዊ (የሞራል ሕግ)
- ማኅበራዊ እና
- ሥርዓታዊ እያለ በሦስት የሚከፍለውን አመለካከት ተመልክተናል።
- ይህ ሥልሳዊ አመለካከት ምን ያህል ለአዲስ ኪዳን ታማኝ ነው?
ክፍል 2፡ አዲሱ-አመለካከት እና የሕግ ሥልሳዊ-ክፍፍል አመለካከት [The New Perspective and the Tripartite Distinction of the Law]
ክፍል 3፡ ኦሪትና ነገረ-መለኮታዊ መሠረቱ
ክፍል አራት፡ ሕግና አዲስ ኪዳን ተዛምዷዊ መርሆ [የኪዳኑን ሕግጋት እንዴ ወደ ሕይወታችን ማዛመድ እንችላለን?]
-
የሕጉ ታሪካዊ ዳራ ምንድር ነው?
- ► 1. 1. ይህ ሕግ ከአምስቱ መደቦች በትኛው ውስጥ ይመደባል?
- ► 1. ወንጀል ነክ ሕጎች
- ► 2. ማኅበራዊ ሕጎች
- ► 3. ቤተሰብ-ተኮር ሕጎች
- ► 4. ሥርዓት ነክ ሕጎች
- ► 5. ርህራሄ-ነክ እና ፍትህ-ነክ ሕጎች
- ► 1. 1. ይህ ሕግ ከአምስቱ መደቦች በትኛው ውስጥ ይመደባል?
-
- ► 1. 2. ሕጉ ከተሰጠበት ታሪካዊ ዳራ አንጻር:- መሠረታዊ ሕግ ነው (አሥርቱ ቃሎች) ወይስ ተዛምዶአዊ ሕግ (ፍርዶች፤ ተፈጻሚነቱ በአንድ አውድ ሥር የሆነ)? አውዳዊ ከሆነ የትኛውን መሠረታዊ ሕግ ጋር ይዛመዳል? ሕጉ የተሰጠው፣ ምን ለመከልከል ነው? ምን ለመፍቀድ ነው? ማንን ለመጥቀም? ማንን ለመከልከል? የትኛውን ተግባር/ሥነ ምግባር ይከለክላል? ወይስ ያበረታታል? ምን መቀጮ ያስከትላል? ምን ዓይነት መዘዝ አለው?
2. የሕጉ ነገረ መለኮታዊ መርሆ ምንድር ነው?
► 1. ስለ እግዚአብሄር ባሕርይ ምን ይናገራል?
► 2. ከክርስቶስ አፈጻጸም ጋር እንዴት ይታያል?
► 3. የሕጉ የፍቅር መርሆ መንድር ነው?
3. ከአዲስ ኪዳን አጠቃላይ አስተምህሮ አንጻር እና ከዘመናችን ዳራ ዐውዳዊ አፈጻጸሙ ምን ይመስላል?


