የቅዱሳት መጻሕፍት ትራኬ

እግዚአብሔርና ኪዳናቱ

 
[በጉባዔ ስላሴ ካቀረብኩት የኪዳን ተከታታይ ትምህርት]
 

የቃል-ኪዳናቱ ዓላማ በቃል-ኪዳኑ-ቀመር: “አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ”

☑️ የኪዳኑ ቀመር በአብርሃም ኪዳን
“በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ። ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።” (ዘፍ 17:7-8)

☑️ የኪዳኑ ቀመር በእሥራኤላውያን ኪዳን
“የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ መሆኔንም ታውቃላችሁ።” (ዘጸ 6:7)
“በመካከላችሁ እመላለሳለሁ፤ አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።” (ዘሌ 25:38)
☑️ የኪዳኑ ቀመር በአዲስ ኪዳን
“እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰዎች መካከል ነው፤ እርሱ ከእነርሱ ጋር ይኖራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ይኖራል፤ አምላካቸውም ይሆናል…ድል የሚነሣ ይህን ሁሉ ይወርሳል፤ እኔም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።”(ራዕ 21:2-3, 7)

እግዚአብሔር፣ ኪዳናቱ እና የትድግናው ትርክት 

በቃል-ኪዳን ውል እና በኮንትራት ውል መካከል ያለው ልዩነት

“ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ጽኑ ፍቅርህን የምትገልጥ አንተ ነህ፤ በላይ በሰማይ፣ በታችም በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ ከቶ የለም፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ ጠብቀሃል፤ በአፍህ ተናገርህ፤ ይህንኑም በዛሬው ዕለት በእጅህ ፈጸምኸው” (1ኛ ነገ 8:23-24)
 
“እርሱም በሙሴ ፊት እንዲህ እያለ እያወጀ አለፈ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሩኅሩኅ ቸር አምላክ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣ ፍቅርን ለሺዎች የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል በደለኛውን ግን ሳይቀጣ ዝም ብሎ አይተውም፤ በአባቶች ኀጢአት ልጆችን የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ይቀጣል።” (34:6-7)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.