
«በእኔ ኑሩ፣ በፍቅሬ ኑሩ!» (ዮሐ. 15:9-17)
በቨርጂንያ በምትገኘዋ ‘የቃል ኪዳን ወንጌል ቤተ ክርስቲያን’ በዘመን መለወጫ ዋዜማ (12/31/2020) የተካፈልኩት ቃል ነው። በዚህ በያዝነው ዓመት የቤተ ክርስቲያን ልሳን የፍቅር እንዲሆን፣ የእርሱን ፍቅር ተረድተን ከግንዱ ጋር የምንጣበቅበት፣ ብዙ የምናፈራበት ይሁንልን። ከግንዱ ጋር የተጣበቀ እንጂ «ከውጪ ተለጣፊ ቅርንጫፍ» ፍሬ አያፈራም። ይህንን አብ ይቆርጠዋል። ግን በእርሱ የሚኖሩትን ፍሬ እንዲያፈሩ አብ ይገርዛቸዋል። ውድ ወዳጆቼ፣ ከእርሱ ጋር እንጣበቅ፣ በእርሱ እንኑር። እናፈራለንና። አሊያ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናል። ሆኖም ግን በእርሱ መኖር ማለት ምን ማለት ነው? በእርሱ መኖራችንስ እንዴት እናውቃለን? የምናፈራውስ ፍሬ ምን ይሆን? የመሳሰሉትን ተመልክተናል። አጠቃላይ ፍሰቱ እንደሚከተለው ነው
▶️ 15:9-11 ኢየሱስን በመታዘዝ እንኑር
▶️ 15:12-17 እርስ በርሳችን በመስዋዕትነት በመዋደድ እንኑር

